@mamy6776635780437: *_<<ተግሣጽ ገንዘብን የመውደድ ጣጣው>> ክፍል 2)_* ...ባለጻጋ ለመሆን ከመሻት በላይ አእምሮን ማጣት የለም ወይም ከዚህ በላይግራ የሚያጋባ ሕይወት ከቶ የለም፤ ከዚህም በላይ ዕብደት የለም፡፡ ስለዚህ ከዚህ ባርነት ራሳችንን ነጻ ለማውጣት ልንፈቅድ ይገባል፡፡ ምንድን ነው? ወደዚህ ዓለም መምጣታችሁ ለዚህ ነውን? ሰው ሆናችሁ መፈጠራችሁ ወርቅን ታከማቹ ዘንድ ነውን? ነገር ግን እናንተን በአርአያውና በአምሳሉ መፍጠሩ ይህን ትፈጽሙ ዘንድ አልነበረም፤ ይልቁኑ እርሱን ደስ ታሰኙትና የሚመጣውን ዓለም ወርሳችሁ ከመላእክት ማኅበር ትቀላቀሉ ዘንድ ነው፡፡ ስለ ምን ታዲያ ከዚህ ኅብረትና እጅግ ከሚያዋርድ ምናምንቴ ከሆነ ፍቅረ ንዋይ ራሳችሁን ማራቅ እንዴት ተሣናችሁ? መንፈሳዊውን ልደት እንደ አንተ የፈጸመ፤ በራብ ሲማቅቅ እያየኸው አንተ ጠግበህ በቊንጣ ትታመማለህ፤ ወንድምህ ተራቁቶ አንተ በልብስ ላይ ልብስን ታከማቻለህ፡፡ እንዲሞቅህም በአንዱ ላይ አንዱን ትደርባለህ፡፡ ነገር ግን የደሃውን ከልብስ የተራቆተ ሰውነት ከማልበስ በላይ ምን በጎ ነገር አለ? እንዲያ አድርጋችሁ እንደሆነ ድሆች ብልን እንዴት አድርገው አራግፈው ማስወግድ እንደሚቻሉ ያውቁበታልና የማይጠፋ ሰማያዊ ልብስ አድርገው በሰማያት ያቆዩላችኋል፤ ከጭንቅ ሁሉ ይታደጓችኋል፤ የሚመጣውን ዓለም ሕይወት እንድትወርሱ ያበቁአችኋል፡፡ ስለዚህ ልብሶችህ በብል ተበልተው እንዳይጠፉ ከፈለግህ ለድሃው ወገንህ ስጣቸው፡፡ ከምድራዊው መዝገብህ ይልቅ የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነት እጅግ የከበረና ማንም ከማይቀርበው ብርሃን ውስጥ እንደሚኖር ልብ በል። ይህ ሰውነት ልብሶቻችን እንዳይጠፉ አድርጎ ማቆየት ብቻ አይደለም በእነርሱ ምትክ ብርሃንን እንድንጎናጸፍ ያደርገናል፡፡ ብዙን ጊዜ ከመዝገብህ ጋር ልብሶችህ በመሠረቃቸው ያልተጠበቀ ጉዳት ይደርስብሃል፤ በደኅንነት የተጠበቀው ሰማያዊ ስፍራ ግን ሞት እንኳ የሚደርስበት አይደለም፡፡ ለዚያ ሰማያዊ መዝገብ በር ወይም ቊልፍ ወይም ትጉሃን የሆኑ ጠባቂዎች አያስፈልጉትም ወይም ይህንን የመሰለ ጥበቃ አያስፈልገውም፡፡ በዚያ ሀብታችን ሁሉ ከወንበዴዎች የራቀና ከጠባቂው እግር ሥር ያለ ነው በሰማያዊው ስፍራ ያለው መዝገባችን የሚጠበቀው እንዲህ ነው፡፡ *ይቀጥላል* .... (ዮሐንስ ወንጌል በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - ድርሳን ስድሳ ዮሐ. 9፥39 በተረጎመበት ድርሳኑ ገጽ 84-87 - ዲያቆን ሽመልስ መርጊያ እንደተረጎመው) #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ፀንታ_ለዘለዓለም_ትኑር

ወለተ ስላሴ
ወለተ ስላሴ
Open In TikTok:
Region: SA
Wednesday 02 September 2026 22:58:32 GMT
252
62
2
1

Music

Download

Comments

df.df7185
ጓል ተምቤን ዓብይይ ዓዲ🍋🍋🍋 :
🙏🙏🙏
2026-09-03 00:14:29
0
y646479
ብቸኛዋ :
🥰🥰
2026-09-03 00:56:41
0
To see more videos from user @mamy6776635780437, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About