@viewer_1221: የተወሰኑ መጽሐፍትን አንብቤያለሁ። መጀመሪያቸውን አውቃለሁ። መጨረሻቸውንም አውቃለሁ። አንዳንዶቹ ደስ አሰኝተውኛል። አንዳንዶቹ አሳዝነውኛል። አንዳንዶቹ እንድጠራጠር አደርገውኛል። ግን አንድ መጽሐፍ አለ፤ ገጹን በገጽ ባነብም እስካሁን መጨረስ ያቃተኝ። ርዕሱም “ሰው” ነው። ይህ መጽሐፍ እንግዳ ነው። አንድ ገጹን በሌላው ገጽ መግለጽ አይቻልም። ዛሬ ያነበባችሁት ሰው ነገ ላይ ሌላ ታሪክ ይዞ ይታያችኋል። ትናንት የታመነ ሰው ዛሬ ለምን እንደሚርቅ አላውቅም። ትናንት የራቀ ሰው ዛሬ ለምን በፍቅር እንደሚቀርብ አይረዳችሁም። አንድ ሰው በአንደኛው ገጽ መልካም ነው። በሌላ ገጽ ግን እንደዚያ አይደለም። ያንኑ ሰው አንድ ቀን ሲያግዛችሁ ታያላችሁ፤ ሌላ ቀን ሲያሳዝናችሁ ታገኙታላችሁ። ትናንት ተስፋ ሲሰጥ የሰማችሁት አፍ ነገር ግን ነገ ደግሞ ከእናንተ ለመለያየት ምክንያት ሲፈልግ ታዩታላችሁ። ሰው እንዲህ ያለ መጽሐፍ ነው። አንዳንዴ እያነበባችሁት ይገባችኋል : ግራ ያጋባችኋል: አይገባችሁም ቀላል ይመስላችኋል መልሶ ደግሞ ይከብዳችኋል። ሰው በፊቱ የሚያሳየው አንድ ሰው ነው፤ በውስጡ የሚኖረው ግን ሌላ ሰው ወይም ብዙ አይነት ሰው ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ሰውን በአንድ ቃል መግለጽ ከባድ ነው። መልካም ነው ብላችሁ አትደምድሙ። መጥፎ ነው ብላችሁም አትዝጉት። ምክንያቱም ሰው ከሁለቱም የተሠራ ነው። በውስጡ ቸርነት አለ። በውስጡ ራስ ወዳድነትም አለ። ይቅር ማለት ይችላል። በተመሳሳይ ጊዜ መበቀልም ይችላል። በአንድ ሰው ላይ ሕይወቱን ሊያሳልፍ ይችላል። እና በአንድ ቃል ከዚያ ሰው ሊለይም ይችላል። ሰው ምን ያህል ውስብስብ ነው? ራሱን የሚያውቅ ይመስለኛል። ግን አንድ ቀን ራሱ ያልጠበቀውን ነገር ከራሱ ውስጥ ያገኛል። “እኔ እንዲህ አላደርግም” ያለውን ነገር ያደርጋል። “እኔ እንዲህ አልሆንም” ያለው ሰው ይሆናል። ከዚያም ራሱን ተመልክቶ ይገረማል። ምክንያቱም ሰው ሌሎችን ለመረዳት ከመሞከሩ በፊት ራሱን ለመረዳት የሚያስቸግረው ፍጡር ነው። የሚወደውን ሰው ለምን እንደሚጎዳ ራሱም አያውቅም። የሚያስፈልገውን ሰው ለምን እንደሚያርቅ ራሱም አያውቅም። አንዳንዴ የሚፈልገውን ነገር ሲያገኝ አይጠብቀውም። የጠፋውን ነገር ግን ከጠፋ በኋላ ዋጋውን ይረዳል። ምናልባት የሰው ትልቁ ችግር ይህ ይሆናል። በእጁ ያለውን ለመስማት ጊዜ ይወስድበታል፤ ከእጁ የወጣውን ግን በአንድ ሌሊት ሊረዳው ይችላል። አንድ ሰው ሲሄድ በሩን በእጁ ዘግቶ ሊሄድ ይችላል። ግን የሄደው ሰው ትዝታ በውስጡ በሩን አይዘጋም። እዚያ ይቀራል። በአንድ የሙዚቃ ድምፅ። በአንድ መንገድ። በአንድ ሽታ። በአንድ ቀን። በአንድ የተረሳ ቃል። እና ያኔ ያለፈው የሚመስለው ነገር እንደገና ይመጣል። ይህ ሰው ነው። ያለፈውን እያወቀ ነገን የሚፈራ። ነገን እያለመ ዛሬውን የሚያባክን። የሚወደውን እያወቀ ለመናገር የሚዘገይ። የሚያሳዝነውን እያወቀ ይቅርታ ለመጠየቅ የሚኮራ። እና አንዳንዴ የራሱን ልብ ለመስማት ከሌሎች ድምፅ በላይ የሚያስፈልገው፣ የራሱ ዝምታ ነው። ሰውን ማንበብ ማለት እሱን ማወቅ ብቻ አይደለም። የሚያሳየውን እና የሚደብቀውን ሁለቱንም መቀበል ነው። የተሳሳተበትን ገጽ ብቻ አይቶ መጽሐፉን አለመጣል ነው። የተሻለውን ገጽ ብቻ አይቶም ሙሉ መጽሐፉን አለመወሰን ነው። ምክንያቱም ሁላችንም ገና ያልተነበበ ገጽ አለን። ሁላችንም ለራሳችን እንኳን ያልነገርነው ምስጢር አለን። ሁላችንም ሌሎች የማያውቁት ትግል አለን። ሰው ከሁለቱም በላይ ነው። እሱ ታሪክ ነው። ትዝታ ነው። ስህተት ነው። ትምህርት ነው። ተስፋ ነው። ፍርሃት ነው። ፍቅር ነው። እና አንዳንዴ ራሱ የማያውቀው ምስጢር ነው። ምናልባት ስለዚህ ነው ይህን መጽሐፍ መጨረስ ያቃተኝ። የመጨረሻ ገጽ የለውም። አንድ ሰው የሚያበቃበት ቦታ ላይ ሌላ ሰው ይጀምራል። አንድ ሕይወት ሲዘጋ ሌላ ታሪክ ይከፈታል። እና እስከ መጨረሻው ገጽ ድረስ እያነበብን የምንሄደው ሌሎችን ብቻ አይደለም። ራሳችንንም ነው። ምክንያቱም ሰው የማይጨረስ መጽሐፍ ነው። አንብቤው መጨረስ ያቃተኝ መጽሐፍ ርዕስ “ሰው” ነው። ገጹን በገጽ ስታነቡት፣ ምናልባት የሌላውን ሰው እያነበባችሁ አይደለም፤ የራሳችሁንም ታሪክ እያነበባችሁ ነው❤️ ይህ የእኔ እይታ ነው ✍️ መልካም ቀን ቀጣይ ሌሎች እይታዎች እንዲደርስዎት የእኔ እይታን ፔጅ Follow, Like, Share, Repost እና Copy Link በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ! #foryou #fyp #viral #fypシ #viralvideo

የእኔ እይታ
የእኔ እይታ
Open In TikTok:
Region: SO
Thursday 03 September 2026 06:25:14 GMT
4340
216
21
63

Music

Download

Comments

teion2127
ጽዮን የዘብሩ ገብርኤል ልጅ 🌷🌼🌻19 አባቴ :
እኛ ስወች ችግር ነን
2026-09-03 18:40:30
1
mesibelay4
እማ መኖርሽ የሚያኖረኝ እምዋ❤እማ❤ :
በጣም😭😭😭😭😭😭😭
2026-09-03 22:35:36
0
tegst.lakwu
Tegst Lakwu :
በትክክል 🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-09-03 15:46:31
0
good.morning7748
Good morning :
እወትነ ነው 🙏🙏🙏🙏🙏🙏👍👍👍👍👍
2026-09-03 14:10:57
0
user9923284918831
ስደተኛ ጓል ሂዋን :
በትክክክል🥰🥰🥰🥰
2026-09-03 07:01:29
1
zibabe.mohammed
የልቤ ንጉስ :
እዉነት ነዉ
2026-09-03 07:54:50
1
user7480178379796
ተስፋየ በእግዛብሔር ነው 💝 ⛪ 🎂 :
እወነት ነው
2026-09-03 14:49:30
0
mesi88679
Mesi :
እውነት ነው 🥰🥰🥰
2026-09-03 08:41:10
1
user20619584583955
አይንየ 💫 💫🅺🅴 ሬማ :
በትክክል🙏
2026-09-03 07:44:15
1
yefatwork6
Yefatwork :
በትክክል
2026-09-03 13:21:03
0
gsgfd4.gsgfd444
ሞሚና ሁሴን :
👌👌👌👌
2026-09-03 08:06:31
1
hewan2572
Hewan👑 :
🥰🥰🥰
2026-09-03 06:39:05
1
jy.services55
የረድኤት እናት :
💝💝💝💝💝💝💝💝💝💝💝💝
2026-09-03 19:45:43
0
waris.fikru
waris fikru :
👍👍👍👍👍👍
2026-09-03 17:22:34
0
yismachewu
Yismachew Jesus Love Me :
🥰🥰🥰
2026-09-03 15:03:54
0
user9838408011315
addisa :
🥰🥰🥰🥰🥰
2026-09-03 14:56:49
0
sheikprince001
S A. B B💙💙🦋🦋 :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-09-03 10:47:52
0
desta.gidey.1214
desta gidey 1214 :
💯💯
2026-09-03 11:35:49
1
ati_2024
አቲካ💞 :
👌👌👌👌
2026-09-03 19:59:44
0
To see more videos from user @viewer_1221, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About