@kidaneweld4: ✍️እኒህ አባት አስተምረው ያልመለሱት መክረው ያላስተካከሉት ሰይጣንን ብቻ ነው። በርሳቸው ትምህርት ከጭነቀቱ ያልተጽናና ከኀዘኑ ያልተረጋጋ ማንም ማን የለም። ✍️አሸናፊ እግዚአብሔር በዚህ ዘመን እርሳቸውን ባያሰቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆን ገሞራንም በመሰልን ነበር። ብቻ እግዚአብሔር ይመስገን። ሁሉም ኦርቶዶክሳዊ ሰው እርሳቸው ካስተማሩት ትምህርት ዕለት ዕለት አንዳንድ ትምህርት ቢማር በሽተኛው ተለውጦ ጤነኛ፣ ክፉው ተለውጦ ደግ፣ ሌባው ተለውጦ ንጹሕ፣ ዘማዊው ተለውጦ ሕጋዊ፣ ኀጥኡ ተለውጦ ተነሳሒ መሆኑ አያጠራጥርም። ✍️የፈጣሪያችን መኖር የሚረጋገጠው ሁሉም እንደ ፈረስ ጆሮ እንደ ጦር ጉረሮ ተካክሎ በበደለበት በዚህ ዘመን ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገበረ ኪዳንን በማስገኘቱ ነው። ✍️ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ የአባ እንጦንስ ምንኩስና፣ የአባ መቃርስ ትሕትና፣ የአባ ጳውሊ ብሕትውና፣ የአባ ሚሳኤል ንጽሕና፣ የአባ አርሳንዮስ ጽሙና የሚነበብባቸው ሕያው መጽሐፈ መነኮሳት ናቸው። ✍️ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ ሲበዛ አማኝ ሲበዛ ታማኝም ናቸው፤ ከዚህም በተጨማሪ የሚኖሩትን የሚያስተምሩ የሚያስተምሩትን የሚኖሩ እውነተኛ መምህርም ናቸው። ✍️ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ ሕብረታዊ እንጂ ግላዊ ባለመሆናቸው ምክንያት የግሌ የሚሉት የባንክ አካውንት፣ ቋሚ ንብረት፣ የፌስቡክ፣ የቴሌግራም፣ የቲክቶክ፣ የዩቲዩብና በጠቅላላው የማሕበራዊ ሚዲያ ድኅረ ገጽ የሌላቸው የሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን እውነተኛ አባትም ናቸው። ✍️ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማን በቆብ የወለዱ መነኮሳት፣ በሃይማኖት የወለዱ መምህራን፣ በእውቀት የወለዱ ልዩ ልዩ የትምህርት ተቋማትና በሥጋ የወለዱ እናት አባት ሊመሰገኑ የሚገባቸው የሀገርም ሆነ የቤተክርስቲያን ባለውለታዎች ናቸው። ✍️ለርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ ሠፈር የላቸውም፤ በሠፈር አያምኑም፤ የተለየ ዘር የላቸውም በተለየ ዘርም አያምኑም፤ በጣም ከፍ ሲል የዓለም ዝቅ ሲልም የመላዋ ኢትዮጵያ መምህር ናቸው። በተሳሳተ መንገድ ተረድተው እኒህን ታላቅ የዘመናችን በረከት የሆኑ አባት ስማቸውን የሚያጎድፉ አሠራራቸውንም የሚነቅፉ አካላት እርሳቸውን ከመንቀፍ ወጥተው ቢችሉ ቢያግዟቸው ካልቻሉ ዝም ቢሏቸው ባይ ነኝ። የልጅነት ምክሬ ነው። ✍️በሥራ እንጂ በወሬ፣ በእውነት እንጂ በትምክህት፣ በጸሎት እንጂ በጉልበት፣ በአምልኮ እግዚአብሔር እንጂ በአምልኮ ጣኦት፣ የማይመኩ እኒህ አባት መምህርነታቸው ከሐዋርያት፣ ሊቀነታቸው ከነ ዮሐንስ አፈወርቅና ከነ ቅዱስ ቄርሎስ መናኔ ዓለምነታቸው ከፍጹማን መነኮሳት፣ ጸሓፊነታቸው ከመንፈሳውያን ደራስያን ያመሳስላቸዋል። ✍️ ለምን ይህ ተጻፈ፦ ሰሞኑን በቅዱስ ሲኖዶስ ለጵጵስና ታጭተዋል የሚል ዜና በማኅበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር ተመልክቻለሁ፤ ነገሩ መልካም ነው ምክንያቱም ለእርሳቸው ያልተገባ ጵጵስና ለማን ሊገባ ይችላል? በፍጹም። ነገር ግን እንደ ቀድሞው አትሮንስ ዘርግቶ ጉባኤ አስፍቶ ደቀመዛሙርትን አብዝቶ፣ ሕዝብ ሰብስቦ ማስተማሩና ብዙ አቅዶ መሥራቱ ላይገኝ ስለሚችል ነገሩ ያስፈራኛል፤ ሆኖም ግን እርሳቸውም ሆነ የትምህርት አባታቸው ሊቀ ሊቃውንት የኔታ ዕዝራ ሐዲስ ወደዚህ የጵጵስና መዓርግ ከመጡ መዓርገ ክህነቱ ወደ ቀደመው ልዕልና ይመለሳል የሚል ተስፋ አለኝ። አምላከ አበው ቅዱስ እግዚአብሔር የወደደውን ያድርግ። "ከብቸኛው ዕንቍ የተገኘ ብቸኛው እንቍ" 👉ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ የርዕሰ አድባራት ወገዳማት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ አንድነት ገዳም የአራቱ ጉባኤያት ምሥክር ጉባኤ ቤት መምህር 🥰
ዲ/ን ኪዳነ ወልድ
Region: ET
Thursday 03 September 2026 10:52:49 GMT
Music
Download
Comments
ye_lij_magna :
ይህንን ሳላይ አትዉሰደኝ አምላኬ
2026-09-04 03:12:56
197
Geze Lekulu :
እስካሁን ስለሆነውም ለወደፊት ስለሚሆነውም ስለማይሆነውም ስላልሆነውም ባለቤቱ ክብርና ምስጋና አምሎኮትና ውዳሴ ለሱ ይሁንና🙏የሚበጀንን ያቃልና የሱን ፈቃድ እንጠብቅ ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱም ይሁንልን 🙏🙏🙏አሜን አሜን አሜን ።
2026-09-03 17:48:32
71
China mulu :
አንዳች የምጨምረዉ ነገር የለኝም ብጨምር ከዚህ ንግግር የተሻለ አንደበት የለኝም የምለዉ ነገር ቢኖር እንደአቅሜ ለሁለቱም አባቶቸ እድሜና ጤና የድንግል ማርያም ልጅ አብዝቶ ይስጣቸዉ።
2026-09-04 20:15:45
19
K/weld :
እንደኔ ግን ጳጳስነቱን ባይቀበሉ ምክንያቱም የፖለቲካው መቆሸሽ ለርሳቼው ፈታኝ እና እና ከባድ ስለሚሆንባቸው እንደሁ ባሉቀት ቁስላችንን ቢያክሙልን ባይ ነኝ ።
2026-09-03 20:51:57
13
Ethio talk :
የእኔ እዚህ የመገኘቴ ምስጢር እርሳቸው ናቸው በረከታቸው በሁላችን ይሁን🥰🙏
2026-09-03 11:03:42
33
tado :
2026-09-03 19:54:14
5
Fikri የሰንበት ተማሪዋ1 :
እኔም እቡና ላይ ያላቸው አስተምሮ ቅር አሰኝቶኛል
2026-09-03 12:36:59
5
አዲናስ !!! :
አምላክ ይቅር ሊለን ሲፈልግ ንፁሃንን ያስነሳል
አሜን ሊምረን ነው መሰል
2026-09-03 14:27:06
11
Lion💪 :
እኔ እኮ ምን ልትሉ ነው ብየ መደንገጤ🤭 ፈጣሪ የወደደውን ያድርግ🙏
2026-09-03 13:39:29
5
t.g :
መድሀኒአለም አይሳሳትም ትክክለኛውን ያደርጋል እውነት እንደኔ በስስት የሚወዳቸው ያለ አይመስለኝም ነበር
2026-09-04 19:33:18
11
Fekadu M. :
ሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ሐዲስ በትዳር ነው በምንኩስና ነው የሚኖሩ? ለማወቅ ያክል ነው ስለድፍረቴ ይቅር በሉኝ🙏
2026-09-04 10:30:42
7
ኦ ሰው :
እንዳትሞክሩት ቢያንሰ 1 አመት ይመከሩን ይገጽሱን ከእነሩሱ ብዙ ነገር አለ ን ያልጨረሰነው እንቃወማለን ምረጫው ላይ አሰንገኛለን እንቃወማለን ተባበሩ ጎበዝ
2026-09-03 17:52:02
5
abrhamyheyis :
እግዚአብሔር የወደደውን ስለሚያደርግ አይጸጽተን
2026-09-04 08:15:10
5
Ati :
እውነት ነው የኔ አባት በርሳቸው ትምህርት ከሰንት ነገር ዳንኩኝ ፈጣሪ እረጅም እድሜ ጤና ይሰጥልን የኛ ዘመን ሀዋርያ 🙏🙏🙏🙏
2026-09-03 20:35:06
10
abeba :
እግዚያብሄር መንገዱ ብዙነው ሲያስነሳም በምክንያት ነው የሚሆነውን ሁሉ ለምረት ለድነት ያርግልን እኛግን በእውነት በመፍራት በፊቱ እንበርክክ እንፀልይ አቤቱ ይቅር በለን።
2026-09-04 18:30:24
6
Love inside :
የዘመናችን ድንቅ አባት 🥰🥰🥰🥰 የአገልግሎት ዘመናቸውን ይባርክልን🥰🥰
2026-09-04 17:17:37
5
Tsegaye Mengesh :
እግዚአብሔር ይመስገን
2026-09-03 17:26:28
5
ሃሌ ሃሌሉያ⚓ :
በህይወት ያሉ አባቶችን ሸፈን አርጓቸው። ቀለል አርጉ ውዳሴውንም። ሰው እራሱ እያየ አምላኩን ያመስግን ስለነሱ እንጂ ፈተና አትጫኑባቸው። አይደረግም እረፉ
2026-09-03 21:43:03
5
Kidus :
ፈጣሪ የወደደውን ያድርግ
2026-09-03 11:32:29
8
Hani_ባፍሎና ዲኮር :
እግዚአብሔር ይሁን ያለው ነው የሚሆነው መታገስ ጥሩ ነው
2026-09-03 16:41:29
10
ሐዋርያዊ :
እረ ውሸት ነው ወንድሜ ከአባቴ ከመምህሬ ላቀ ሊቃውንት እዝራ ጀምሮ አልፈልግም ብለዋል
2026-09-03 11:50:40
7
bekiካራ28 :
እኔም ጳጳስ ቢሆኑልን ብዬ እመኛለው 🥰🥰🥰
2026-09-04 05:03:43
8
siku recorder🇪🇹💎 :
ባረገው አቡነ ናትናኤል ከአመታት በፊት ነበር ሲጠይቋቸው የነበረው
2026-09-04 11:05:19
1
ሰላም ለኪ ጎንደር :
ቢሆኑ የሚገባቸው ናቸው
2026-09-04 17:44:08
2
mami sa&ma :
አምላኬሆይ አተ ታውቃለህ🥺
2026-09-04 14:58:08
3
To see more videos from user @kidaneweld4, please go to the Tikwm
homepage.