@useful.talks: አዲስ አበባ ጦርኋይሎች አካባቢ ዛሬ ረፋድ ላይ፣ ቡና አብሮኝ የጠጣ ወዳጄን ተሰናብቼ ዜብራውን ስሻገር ነው አይኔ በዚህ ጫማ ላይ ያረፈው ‎ ‎"ጋሼ ጫማህኮ ለቋል" ‎ ‎"አውቃለሁ። ምን እንዳደርግ ነው የምትነግረኝ። ችግራችንን ድህነታችንን ጉድለታችንን የሚናገር ሰው አላጣንም። ጫማህኮ ተቀደደ የሚሉ ብዙ ጎረቤቶች ብዙ ጓደኞች አሉኝ። ፊትህ ጠቆረ ከሳህ የሚል ጉድለት የሚናገር መች አጣን"  አለኝ። ‎ ‎ዜብራውን ተሻግረን በአንድ የመንገድ ጥግ ቆመናል። ሸሚዙ አንገት አካባቢ አልቆ ትልቁን ሰው አጎሳቅሎታል። በመታጠብ ብዛት ወደ ስስ አሮጌ ጨርቅነት የተቀየረ ሸሚዙና የለቀቀ ጫማው ከፊቱ ግርጣት ጋር ተደምሮ ያላየሁትን ኑሮውን ያሳየኛል። ሱሪው ብቻ ነው ትንሽ የሚሻለው። ‎ ‎"ይቅርታ ከደበረህ እኔ ጫማው መልቀቁን ካላየህ ብዬ ነው የነገርኩህ" ‎ ‎"አላጠፋህም። አንድ ጫማ አራት ሺህና ከዚያ በላይ በሆነበት ጊዜ የጫማዬ መቀደድ ከገረመህ ግን ተሳስተሃል። ጎረምሳ ልጅ አለኝ። ቢያንስ እሱ የኔን ያህል አልኖረምና እሱ ጫማ እንዲያደርግ እኔ ያለኝን ማድረግ አለብኝ። ለልጄኮ ጫማ ገዛሁ" ብሎ እውነተኛ ፈገግታ ፈገግ አለ። ‎ ‎" ልጄ ነው ከኔ መቅደም ያለበት። እሱ የተቀደደ ጫማ ቢያደርግ ጓደኞቹ ይስቁበታል። ምክንያቱም የኔን ድህነት አይረዱትም። ቢስቁበት ልጄ በልጅ አዕምሮው ይሸማቀቅና ይጎዳብኛል። ልጄኮ ወደዚህ ዓለም በራሱ ምርጫ አልመጣም በኔ ምርጫ እንጂ። ታዲያ እኔ የነተበ ሸሚዝ ለብሼ ልጄን ሰልባጅም ቢሆን ገዝቼ ባላለብስ የቱጋ ነው አባትነቴ።"  ዕምባ በአይኑ ሞልቶ ነበር። ግን ጥርሱን ነክሶ ላለማልቀስ ጨከነ ‎ ‎"ሚስቴን አሟታል። ግን እሷም ከእኔ ጋር ተጣላች። ለምን እንደተጣላች ታውቃለህ? ብሎ በስሱ ሐዘን የቀላቀለ ፈገግታ ፈገግ አለና መልሶ አንገት ደፋ። አንገቱን ሲደፋ ዓይኑ ላይ ያረገዛቸው ዕምባዎች ቁልቁል ፈሰሱ። ‎ ‎"ለማይተወኝ ህመም መድሃኒት መግዣ ተብሎ የሚወጣው ብር ልጄ በጓደኞቹ ፊት አንገት ከሚደፋ ጫማ ይገዛበት አለች። አልስማማም ስል ብትገዛም አልውጥም በማለቷ ተጣላን። እኔ የምድነው ለልጄ ይህ ሲደረግ ነው ብላኝ ምን ላድርግ ገዛሁለት" ‎ ‎ከዚህ በላይ ለመስማት አቅም ሳጣ እምባዬን ለመደበቅ ታገልኩ። ጫማህ አልቋል ልብስህ ተቀዷል ጠቁረሃል ከስተሃል ብለን አስተያየት ከምንሰጣቸው ሰዎች ጀርባ ያለውን ሕይወት አናውቅምና ጉድለትን ለመቁጠርና ይህኮ የለህም ሰዎችን ለማለት አልከበደንም አልኩ ለራሴ። ‎#usefultalks #share

Useful Talks 🇪🇹
Useful Talks 🇪🇹
Open In TikTok:
Region: ET
Thursday 03 September 2026 20:35:00 GMT
17003
445
26
36

Music

Download

Comments

mamakiya0418
ያልተኖረ ልጅነት :
ጥሩ ትምርህት ነው
2026-09-04 08:30:40
1
gizachewerkihunme
G.E1221 :
አባትነትን በትክክል ለሆነው ከባድ ነው
2026-09-04 06:08:10
2
haveaniceday592
ጥሩቀን አይምሽ !!!!!!! :
የምር ያሳዝናል
2026-09-04 08:49:16
0
deva8454
łêǰ̣Ďèvã✝️☦️ :
betam leb yemineka nw
2026-09-04 08:40:41
0
user3142837227135
bad boy :
ከዛ አንተ ምን አደረግህ ወንድሜ ትተኸው ሔድህ እ?
2026-09-04 08:26:41
0
user10620952729257
Nolawit💕 :
አባትነት ❤❤❤❤
2026-09-04 08:46:54
0
user9618518465454
አሜን ይሁን :
ይሄ የሚኖር ነገር ነው እኔም የኔ መጥቆር አለማማር አያሳስበኝም ልጆቸ አምሮባቸው ሳይ ግን ያኔ እደሰታለሁ
2026-09-04 08:16:56
0
8harumoy
𝖒𝖆𝖒𝖆 𝓶𝓪𝔂 𝓰𝓸𝓸𝓭𝓷𝓼𝓼 :
እንደኔ ያለቀሰ
2026-09-04 08:15:38
0
engineeringdiscipline
የብዕር ጠብታ ናፋቂው ✍️✍️ :
አባትነት 😥😥
2026-09-04 07:42:27
0
0938103072adhu.love5
ትምኒተይ ስሚሩ ሂወተይ መቒሩ :
እናመስግናለን ቡዙ ያስተምራል
2026-09-04 06:57:29
0
keratopher
ቱቱ :
ደህናነን ስንል እኮ የሁልጊዜ ውሸታችን ነው
2026-09-04 06:36:01
0
baylu.tewelde
baylutewelde :
መሳጭ ታሪክ ነው
2026-09-04 06:18:36
0
adane2145
𝑎𝑑𝑎𝑛𝑒 :
በጣም አሰተማሪ ታሪክነው በጣም ያሳዝናል ?????????
2026-09-04 06:08:59
0
ataklti2314
Ashenafi :
ተከታይህ ነኝ አስተማሪ ፅሁፎችህ ቀጥልበት ❤
2026-09-04 06:28:42
0
zkalay.zkalay1232
@kinfe 1232 :
ትልቅ መልእክትነው ምናልባት ምን ኣይነት ሂወት እንዳለን የማያውቁ(የማይረዱ) ሰዎች ቡዙ ኣሉ ነገርግን በየኣንኣንዱ ጓዳ ያለ ችግር የሚያውቅ(የሚረዳ)ከዚውጣውረድ የሚጋፈጥ ቤተሰብ ነው...ስለ ሓሳብህ እናመሰግናለን።
2026-09-04 07:32:45
0
malede.tegegne
Eyezelelachhu🤟 :
የሚገርም ትምህርት ነው እናት ለአባቶቻችን ለኛ የሚከፍሉትን ዋጋ ማወቅ አለብን 🙏
2026-09-04 05:34:06
0
wenidiyha
wendiyha :
በጣም ልብየሚነካነው😌😌😌😌😌😌
2026-09-03 21:11:42
0
kulushinebikeder
LIFE IS SHORT :
እህህህህህህህህ ያማል እኮ🙏🙏🙏🙏
2026-09-04 08:50:07
0
tesfawmekete
tesfawmekete :
ምን ይደርግ ችግርነው በዚህግዜ ጫማለመቀየር ይከብዳል ስራ ሲኖርነው እኮ ሰው ሰርቶ የሚለብሰው እዚህ የንሮውድነት እዚህ ጦርነት ርፈጣሪ ይርዳን
2026-09-04 05:03:02
0
semache0
semache0 :
አመሰግናለሁ ተምሬበታለሁ
2026-09-04 06:36:08
1
user5215166814715
አንድ ለእናቱ 💚💝❤️♨️💢💯🦅 :
🙏
2026-09-04 07:54:22
0
714359265a
ትዝ አለኝ የጥንቱ 🌍🚣🏽‍♂️💿📺🎵 :
😥😥😡😡😡😡
2026-09-04 03:11:33
0
user1331300261983
እየሱስ ጌታ ነው! :
!!!
2026-09-04 05:54:16
0
To see more videos from user @useful.talks, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About