@m9947626: በሰው ተስፋ መቁረጥህ የሕይወትህ ማብቂያ ሳይሆን፣ ትክክለኛውን መጠጊያህን የምታውቅበት መልካም አጋጣሚ ነው! ሰዎች ዛሬ አሞግሰውህ ነገ ሊረሱህ ይችላሉ፤ ዛሬ ወደደውህ ነገ ሊተዉህ ይችላሉ። የሰው ልጅ ፍቅርና ተስፋ እንደ አየር ሁኔታ ተለዋዋጭ ነው። ነገር ግን የማይቀየረው፣ የማይለወጠውና ፈጽሞ የማይጥልህ አንድ አምላክ ብቻ ነው! በሕይወትህ ውስጥ የሚገጥሙህ ፈተናዎች፣ ብቸኝነትህና የልብህ ሕመም ለሰው የማይነገር ሊሆን ይችላል፤ ፈጣሪ ግን የልብህን ሕመም ያውቃል፣ የታነቀውን እምባህን ያያል። ፊትህን ወደ እርሱ ስትመልስና ተስፋህን በሰው ላይ ሳይሆን በእርሱ ላይ ስታደርግ፣ በሕይወትህ ውስጥ የሚከሰተውን ሰላምና እረፍት ታያለህ። ማንም ሰው ቢተውህ፣ ሁኔታዎች ሁሉ ቢጨልሙብህ እንኳን አትዘን፤ ምክንያቱም ሰማይንና ምድርን የፈጠረ አምላክ ከእኔ ጋር ነው ብለህ በሙሉ እምነት ተመላለስ! 🕊️✨🙏 #ተስፋ #ኦርቶዶክስተዋህዶ #እምነት #ምስጋና #ethiopianorthodox
ፍቅር ከክርስቶስ ትህትና ከማርያም
Region: SA
Thursday 03 September 2026 21:55:49 GMT
Music
Download
Comments
There are no more comments for this video.
To see more videos from user @m9947626, please go to the Tikwm
homepage.