@adugnakuma: አዲስ አበባ ጦርኋይሎች አካባቢ ዛሬ ረፋድ ላይ፣ ቡና አብሮኝ የጠጣ ወዳጄን ተሰናብቼ ዜብራውን ስሻገር ነው አይኔ በዚህ ጫማ ላይ ያረፈው "ጋሼ ጫማህኮ ለቋል" "አውቃለሁ። ምን እንዳደርግ ነው የምትነግረኝ። ችግራችንን ድህነታችንን ጉድለታችንን የሚናገር ሰው አላጣንም። ጫማህኮ ተቀደደ የሚሉ ብዙ ጎረቤቶች ብዙ ጓደኞች አሉኝ። ፊትህ ጠቆረ ከሳህ የሚል ጉድለት የሚናገር መች አጣን" አለኝ። ዜብራውን ተሻግረን በአንድ የመንገድ ጥግ ቆመናል። ሸሚዙ አንገት አካባቢ አልቆ ትልቁን ሰው አጎሳቅሎታል። በመታጠብ ብዛት ወደ ስስ አሮጌ ጨርቅነት የተቀየረ ሸሚዙና የለቀቀ ጫማው ከፊቱ ግርጣት ጋር ተደምሮ ያላየሁትን ኑሮውን ያሳየኛል። ሱሪው ብቻ ነው ትንሽ የሚሻለው። "ይቅርታ ከደበረህ እኔ ጫማው መልቀቁን ካላየህ ብዬ ነው የነገርኩህ" "አላጠፋህም። አንድ ጫማ አራት ሺህና ከዚያ በላይ በሆነበት ጊዜ የጫማዬ መቀደድ ከገረመህ ግን ተሳስተሃል። ጎረምሳ ልጅ አለኝ። ቢያንስ እሱ የኔን ያህል አልኖረምና እሱ ጫማ እንዲያደርግ እኔ ያለኝን ማድረግ አለብኝ። ለልጄኮ ጫማ ገዛሁ" ብሎ እውነተኛ ፈገግታ ፈገግ አለ። " ልጄ ነው ከኔ መቅደም ያለበት። እሱ የተቀደደ ጫማ ቢያደርግ ጓደኞቹ ይስቁበታል። ምክንያቱም የኔን ድህነት አይረዱትም። ቢስቁበት ልጄ በልጅ አዕምሮው ይሸማቀቅና ይጎዳብኛል። ልጄኮ ወደዚህ ዓለም በራሱ ምርጫ አልመጣም በኔ ምርጫ እንጂ። ታዲያ እኔ የነተበ ሸሚዝ ለብሼ ልጄን ሰልባጅም ቢሆን ገዝቼ ባላለብስ የቱጋ ነው አባትነቴ።" ዕምባ በአይኑ ሞልቶ ነበር። ግን ጥርሱን ነክሶ ላለማልቀስ ጨከነ "ሚስቴን አሟታል። ግን እሷም ከእኔ ጋር ተጣላች። ለምን እንደተጣላች ታውቃለህ? ብሎ በስሱ ሐዘን የቀላቀለ ፈገግታ ፈገግ አለና መልሶ አንገት ደፋ። አንገቱን ሲደፋ ዓይኑ ላይ ያረገዛቸው ዕምባዎች ቁልቁል ፈሰሱ። "ለማይተወኝ ህመም መድሃኒት መግዣ ተብሎ የሚወጣው ብር ልጄ በጓደኞቹ ፊት አንገት ከሚደፋ ጫማ ይገዛበት አለች። አልስማማም ስል ብትገዛም አልውጥም በማለቷ ተጣላን። እኔ የምድነው ለልጄ ይህ ሲደረግ ነው ብላኝ ምን ላድርግ ገዛሁለት" ከዚህ በላይ ለመስማት አቅም ሳጣ እምባዬን ለመደበቅ ታገልኩ። ጫማህ አልቋል ልብስህ ተቀዷል ጠቁረሃል ከስተሃል ብለን አስተያየት ከምንሰጣቸው ሰዎች ጀርባ ያለውን ሕይወት አናውቅምና ጉድለትን ለመቁጠርና ይህኮ የለህም ሰዎችን ለማለት አልከበደንም አልኩ ለራሴ። ••••𝔸𝕕𝕦𝕘𝕟𝕒•••• #አጫጭር_ታሪኮች #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #creatorsearchinsights
🇦 🇩 🇦
Region: ET
Friday 04 September 2026 18:48:02 GMT
Music
Download
Comments
selam habtwled :
በትክክል ከሳቁ ጥርሶች ጀርባ ብዙ ህመሞች አሉ ጎሽ ለልጇ ሲባል ተወጋች አይደለም የሚባለው ለልጅ ሲባል ዝቅ ይባላል
2026-09-04 19:08:49
0
Temu 21 23 :
🙏🙏🙏
2026-09-04 18:57:10
0
To see more videos from user @adugnakuma, please go to the Tikwm
homepage.