@teraraw79: #እንኳን ንሐሴ 28 ለሚከበረው የፃዲቁ አቡነ አብሳዲ ዘዞዝ አምባ ቅዱስ ጊወርጊስ የመታሰቢያ ቀንናቸው በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን። # የፃዲቁ አቡነ አብሳዲ ዘዞዝ አምባ ገዳም መገኛ የት ነው? #የፃዲቁ አቡነ አብሳዲ ዘዞዝ አምባ ገዳም የተገደመው መቸ ነው? #ዞዝ አምባ ቅዱስ ጊወርጊስን ቤ/ትያንን ከተደበቀበት አግኝቶ ስራ ያስጀመረው ማነው? #ዞዝ አምባ ቅዱስ ጊወርጊስን የሰራው ማን ነው? #ከዚህ በላይ የተጠየቁትን ጥያቄዎች መልስ የያዘ ፅሁፍ ነው አንብባችሁ ለሌሎች አጋሩ። ቀን 27/12/2018 ዓ.ም 📚❗️❗❗📖 አስገራሚዎቹን የቅዱስ ላሊበላ ፍልፍል ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን ከአለት በመፈልፈል ያነፃቸው ከ11ዱ የዛጉዬ ነገስታት አንዱ የሆነው ቅዱስ ንጉስ ላሊበላ / በ1101 – 1197 ዓ.ም/ ነው፡፡ እነዚህ በአሰራር ጥበባቸው ዓለምን ያስደመሙና በመንፈሳዊ መዓዛ የተሞሉ አብያተ ክርስቲያናት፤ ከኢትዮጵያዊያን የጥበብ መኩሪያ እና ሃብትነት ባሻገር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በ1978 ዓ.ም የአለም ቅርስ ሆነው ተመዝግበዋል(getu temesgen)። 🌻🌻🌻 ነገር ግን ቅዱስ ላሊበላ ከአነፃቸው መካከል ቀደምት የሆነው ሰፊ ታሪክና ድንቅ የአሰራር ጥበብን የተላበሰው ይህ የዞዝ አምባ ቅዱስ ጊወርጊስ ፍልፍል አለት ውቅር ቤተክርስቲያን ዛሬ ትንሽ እህትና ወንድሞቹ ማለትም ግሸን ማርያም፣አክሱም ፅዮን፣ ላስታ ላሊበላ፣ዋልድባ ሌሎችም የተባበሩት መግስታት የትምህርት፣የሳይንስ እና የባህል የጥበብ ማእከል ሆነው በአለም ቅርስ (ዮኔስኮ) ሲመዘገቡ ዞዝ አምባ ቅዱስ ጊወርጊስ ግን ባለቤት አቶ ተዘንግቷል ❗። ☝☝☝አለም ወደ ማርያም ፣ አክሱም ፅዮን ወደ ቅዱስ ላሊበላ ሲጎርፍ ወደ ዞዝ አምባ አቡነ አብሳዲ ገዳም የሚመጡት ግን በጣት የሚቆጠሩ ሆነዋል። ለምን ቢሉ❓❓❓ ❌ ልማት (መንገድ) አለመኖር ❌ የእንግዳ ማረፍያ ሆቴሎች አለመኖር ❌ የዞንና የወረዳ የባህል እና ቱሪዝም ቡድን ገዳሙን የማስተዋወቅና የማስተባበር አቅም ማጣት ዋና ዋና ተጠቃሽ ችግሮች ናቸው። |central idea| 🚕🚕🚕🚕🚕 ደብረ ዞዝ አምባ🚍🚍🚓🚓🚓 ዞዝ አምባ ቅዱስ ጊዮርጊስ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሚገኝ ጥንታዊ፣ቀዳማዊና ግሩም ድንቅ ታሪካዊ ቦታ ነው። 🚶📚 ዞዝ አምባ ቅዱስ-ጊዮርጊስ ገዳም ከዞኑ ዋና ከተማ ከጎንደር በአርባያ በኩል 130 ኪ.ሜ 📚 ከክልሉ ዋና ከተማ ባሕር ዳር በአዲስ ዘመን - እብናት መስመር 180 ኪ.ሜ ገደማ 🚕🚕ከኢትዮጲያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ 747 ኪ.ሜ ከምትርቀው የምስራቅ በለሳ ወረዳ ዋና ከተማ ጉሃላ 9 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ እጅግ አስደናቂ ፍልፍል አለት ውቅር ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ 📚 ዞዝ አምባ ቅዱስ ጊወርጊስ ፍልፍል አለት ውቅር ቤተክርስቲያን ከተደበቀበት አግንተው አገልግሎት እንዲጀምር አስተዋፆ ያደረጉ ፃዲቁ አቡነ አውሳዲ ከደብረ መንኩር መተው በዚሁ በደብረ ዞዝ አምባ ገዳም መኖር ከጀመሩ ብዙ አመታት ቦኀላ ነው። ዞዝ አምባ ዘ-አቡነ አብሳዲ ገዳም በ11ኛ መቶ ክፍለ ዘመን ተጀምሮ በአጼ ይስሃቅ (1414-1429 ዓ/ም) ዘመነ መንግስት አቡነ አብሳዲ በተባሉ አባት እና በንጉሡ ፈቃድ በገዳምነት አገልግሎት እንዲሰጥ መደረጉ ይነገራል፡፡ የገዳሙ አባቶች እንደሚያሰረዱት ብፁእ አቡነ እብሳዲ የተባሉ አባት ደብረመንኩር ከተባለች ቦታ እየጸለዩ እያሉ በእግዚአብሔር አምላክ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ ወደ ዞዝ አምባ እንዲሄዱ ስለታዘዙ ትዕዛዛቸውን ጠብቀው 444 መነኮሳትን አስከትለው ጉዞ ሲጀምሩ ዕጽዋት ሁሉ አብረዋቸው ለመጓዝ ተነሱ፡፡ በዚህ ጊዜ ዕጽዋቶችን “ፅንአ በበመካንኮ” ብለው ሲያወግዟቸው እጽዋቶች ባሉበት ሲቆሙ ሁለት ዋርካዎች ግን ከፊትና ከኋላ ጥላ በመሆን ተከተሏቸው፡፡ እንዲህ በመንፈስ ቅዱስ እየተመሩ ከተጓዙ በኋላ ዞዝ አምባ ሲደርሱ ከተራራው ስር ከሁለቱ ዋርካዎች እንዷ ፀድቃ ስትቀር ይህች ቦታ ናት ብለው ጸሎት አደረሱ፡፡ ጸድቃ የመቅርቷ ምልክትም ቦታው ላይ መድረሳቸውን ለማሳየት ነበር ይላሉ፡፡ ወደ ተራራውም ተጠጉ ፤ ወደ ተራራውም ወጡ፡፡ የተራራውን ጉዞ ጨርሰው ከተራራው አናት ሜዳ ላይ ሲደርሱ በአራቱም ማዕዘን ሲጎበኙ በደቡብ ግሸን ማርያምን፣ በምስራቅ ቅዱስ ላልይበላን፣ በምዕራብ ዋልድባን፣ በሰሜን አክሱም ፅዮንን በመንፈስ ቅዱስ አይተው 444 መነኮሳትን እንደያዙ ፀሎት ከፈጸሙ በኋላ ወደ ሰሜኑ ክፍል ለመጓዝ ሲነሱ ከፊት ስትመራ የነበረችው ዋርካ ተራራው ላይ ፀድቃ ቀረች፡፡ አቡነ እብሳዲ አራቱ ቅዱሳኖች ሚታዩባት ይች ቅዱስ ቦታ በመሆኗ ይች የዘላለም ማረፊየ ናት ብለው ከደበረ መንኩር የአመጧትን የኪዳነ ምህረት ታቦት ከተራራው አናት ላይ መሠረቱ፡፡ በዚህች ቦታ ብፁአ አቡነ አብሳዲ በፀሎት ላይ እያሉ የእግዚአብሔር መላክ መጥቶ በሰው ዕጅ ያልተሰራች በመንፈስ ቅዱሰ እጅ የተሠራች ከእግርህ ሥር አንዲት ቤተክርስቲያን አለችና አገልግሎት እንድትጀምር አድርግ አላችው፡፡ አቡነ አብሳዲም ጸሎታቸውን እንደጨረሱ እንደ ንግስት ኢሌኒ እጣን በሚያጥኑበት ጊዜ ወደ ሰማይ ዘልቆ ተመልሶ ወደ ዞዝ አምባ ጊዎርጊስ ውቅር ቤተክርስቲያን ሲሰግድ ተመለከቱ፡፡ አቡኑ ጭሱን ተከትለው ሲወርዱ ታሪካዊውን ህንጻ በአጋምና በግመሮ ዛፎች ተሸፍኖ አገኙት፡፡ የአጋምና የግመሮውን ደን በ444 መነኮሳት ካስመነጠሩ በኋላ ወደ አስደናቂው የቋጥኝ ፍልፍል አለት ህንጻ ሲገቡ ህንጻውን ማን እንደሠራውና መቼ እንደተመሠረተ የሚገልጽ የፅሁፍ መረጃ አገኙ፡፡ በዚህ አስደናቂና ማራኪ በሆነ ፍልፍል ውቅር ቤተክርስቲያን ህንጻ ውስጥ የተገኘው የጽሁፍ ማስረጃም ቅዱስ ላሊበላ ከኢየሩሳሌም ወደ ወሎ ሲጓዙ በነበረበት ወቅት እንዳነጹት ያስረዳል፡፡ የፃዲቁ በረከታቸው ምልጃና ተራዳኣይነታቸው ከህዝበ ክርስቲያኑ ጋር ይሁን። አሜን ....................................... ....................................... ...................................... ....Con't..... 👄ይድረስ ....ለበለሳ ልጆች ለዞዛምቤዎች..🌻🌻 👄👄👄👄👄👄👄🌻🌻🌻
Getasew dessie alemu
Region: ET
Friday 04 September 2026 22:10:48 GMT
Music
Download
Comments
HEAVEN @21163 :
ትዝታየን ቀሰቀስከው እንኳን አብሮ አደረሰን።
2026-09-05 05:51:52
1
bewket tadese :
🙏🙏🙏🙏በጣም አመሰግናለሁ እንኳን አደራችሁ አብነ አባውሳዴ ትዝ ትዝ
2026-09-05 09:09:46
1
TG የጎንደር ባህላዊ አልባሳት :
enate kidanemihret anich tebkign yezozabewu giwergis hegerachn Selam adrgiln🙏🙏🙏
2026-09-05 20:00:01
1
abrish :
ዋው ደስ ሲል ጌች የመቸ ነው
2026-09-05 03:47:25
0
banechey ebabu :
ዞዝአምባ አገሪ ዘድሮ በሰዉአገር አሳለፈሁት በጣምናፈቀኝ@ ፈጣሪየዛሪአመት በሰላም አድርሰን በጣምእናመሰግናለን ሰላሳየህን🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-09-05 14:53:05
1
# አዛኘን ❤@ :
እንደዛ 3 ዓመት ሞላኝ አባውሳዴ ናፈቀኝ ቦታውን ስላሳየኸኝ ለማንኛውም አመሰግናለሁ ብሮ
2026-09-05 11:18:07
1
tazeb gizachwe :
በጣም ነው ደስ የሚል ወንድሜ
2026-09-05 08:17:00
1
Blen :
እናቴ ኪዳነ ምህረት አባ አብሳዲ ደጃችሁ ናፈቀኝ ለምጣት አበቂኝ እናቴ
2026-09-10 08:14:53
0
የበለሰዋ ቆንጆ :
ሀገሬናፈቀኘ
2026-09-05 07:03:56
1
ሁሉም ያልፋል :
ደጁ ናፈቀኝ አባቴ
2026-09-11 19:15:34
0
መኖር ደጉ :
አገሬን አሳየህኝ ወንድሜ
2026-09-10 14:22:53
0
ያጣ መልክየለውም :
አሜንንንንንንን
2026-09-19 17:28:34
0
hany :
ናፈቀኝ 🥰🥰
2026-09-09 05:20:21
0
ህብረ ስርዓት :
በለሳ ነው ??
2026-09-06 11:03:18
1
love peace :
ተባረክ
2026-09-05 18:06:11
1
ዓውደግዕዝ ወትምህርተቅኔ እመምህር ዮሐንስ :
ድንቅ ኒፋቂ ሕይወት🙏🙏🙏🙏
2026-09-05 02:23:52
1
2127@SOL :
❤️❤️❤️❤️❤️❤️
2026-09-05 07:13:48
1
ፍቅር ከዞዛዓባ እናትዋ ጎንደር 💪💚 :
አሜን አሜን አሜን
2026-09-05 13:32:07
1
ሰርዲዮን :
ማንም እኮ ለማንሳት ደፍሮ አያውቅም እሱ ይሁን
2026-09-06 16:17:25
0
prist :
በዚህ ደስ የሚል ገዳም እልፍ መነኮሳት ይኖራሉ ብየ ተስፋ አደርጋለሁ
2026-09-07 02:09:30
1
የማርያም ልጅ D ✟ :
ለደጁ ያብቃን🙏
2026-09-11 06:42:32
0
አዲስ ዘመን ሃና :
አረ ትዝታታየ
2026-09-07 17:10:21
0
122327❤@❤@ :
ጌችየ አምንብለናል🙏🙏🙏🙏
2026-09-08 15:56:13
0
@mss :
የኔ አባት የቤትህ ትዝታ አለብአ።።
2026-09-07 06:00:10
0
Believe in yourself :
አይ ዞዝ አምባ ኪዳነምህረት
2026-09-05 07:29:18
0
To see more videos from user @teraraw79, please go to the Tikwm
homepage.