@alemjesus0: ❤️ሐዋ. ሥራ 9:1-25 1 ሳውል ግን የጌታን ደቀ መዛሙርት እንዲገድላቸው ገና እየዛተ ወደ ሊቀ ካህናት ሄደ፥ 2 በዚህ መንገድ ያሉትንም ሰዎች ወንዶችንም ሴቶችንም ቢያገኝ፥ እያሰረ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጣቸው ዘንድ በደማስቆ ላሉት ምኵራቦች ደብዳቤ ከእርሱ ለመነ። 3 ሲሄድም ወደ ደማስቆ በቀረበ ጊዜ ድንገት በእርሱ ዙሪያ ከሰማይ ብርሃን አንጸባረቀ፤ 4 በምድርም ላይ ወድቆ ሳለ፦ “ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ?” የሚለውን ድምፅ ሰማ። 5 ጌታ ሆይ፥ ማን ነህ? አለው። እርሱም አለው፦ “አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ፤ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል።” 6 እየተንቀጠቀጠና እየተደነቀ፦ “ጌታ ሆይ፥ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ?” አለው። ጌታም አለው፦ “ተነሥተህ ወደ ከተማ ግባና ታደርገው ዘንድ የሚያስፈልግህን ይነግሩሃል።” 7 ከእርሱም ጋር በመንገድ የሄዱ ሰዎች ድምፁን እየሰሙ ማንን ግን ሳያዩ እንደ ዲዳዎች ቁሙ። 8 ሳውልም ከምድር ተነሣ፥ አይኖቹም በተከፈቱ ጊዜ ምንም አላየም፤ እጁንም ይዘው እየመሩ ወደ ደማስቆ አገቡት። 9 ሳያይም ሦስት ቀን ኖረ፤ አልበላምም አልጠጣምም። 10 በደማስቆም ሐናንያ የሚሉት አንድ ደቀ መዝሙር ነበረ፥ ጌታም በራእይ፦ “ሐናንያ ሆይ፥” አለው። እርሱም፦ “ጌታ ሆይ፥ እነሆኝ፡” አለ። 11 ጌታም አለው፦ “ተነሥተህ ቅን ወደ ሚባለው መንገድ ሂድ፥ በይሁዳ ቤትም ሳውል የሚሉትን አንድ የጠርሴስ ሰው ፈልግ፤ 12 እነሆ፥ እርሱ ይጸልያልና፤ ሐናንያ የሚሉትም ሰው ገብቶ ደግሞ እንዲያይ እጁን ሲጭንበት አይቶአል።” 13 ሐናንያም መልሶ፦ “ጌታ ሆይ፥ በኢየሩሳሌም በቅዱሳንህ ላይ ስንት ክፉ እንዳደረገ ስለዚህ ሰው ከብዙዎች ሰምቼአለሁ፤ 14 በዚህም ስምህን የሚጠሩትን ሁሉ ለማሰር ከካህናት አለቆች ሥልጣን አለው፡” አለ። 15 ጌታም አለው፦ “ይህ በአሕዛብም በነገሥታትም በእስራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ ነውና ሂድ፤ 16 ስለ ስሜ ስንት መከራ ሊቀበል እንዲያስፈልገው እኔ አመለክተዋለሁና።” 17 ሐናንያም ሄዶ ወደ ቤቱ ገባ፥ እጁንም ጭኖበት፦ “ወንድሜ ሳውል ሆይ፥ ጌታ፥ እርሱም በመጣህበት መንገድ የታየህ ኢየሱስ ነው፥ ደግሞ ታይ ዘንድና መንፈስ ቅዱስ ይሞላብህ ዘንድ ላከኝ፡” አለ። 18 ወዲያውም እንደ ቅርፊት ያለ ከዓይኑ ወደቀ፥ ያን ጊዜም ደግሞ አየ፤ ተነሥቶም ተጠመቀ፥ 19 መብልም በልቶ በረታ። በደማስቆም ካሉት ደቀ መዛሙርት ጋር ጥቂት ቀን ኖረ። 20 ወዲያውም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ በምኵራቦቹ ሰበከ። 21 የሰሙትም ሁሉ ተገረሙና፦ “ይህ በኢየሩሳሌም ይህን ስም የሚጠሩትን ያጠፋ አይደለምን? ስለዚህስ ታስረው ወደ ካህናት አለቆች ይወስዳቸው ዘንድ ወደዚህ አልመጣምን?” አሉ። 22 ሳውል ግን እየበረታ ሄደ፥ በደማስቆም ለተቀመጡት አይሁድ ይህ ክርስቶስ እንደ ሆነ አስረድቶ መልስ ያሳጣቸው ነበር። 23 ብዙ ቀንም ሲሞላ አይሁድ ሊገድሉት ተማከሩ፤ 24 ሳውል ግን አሳባቸውን አወቀ። ይገድሉትም ዘንድ በሌሊትና በቀን የከተማይቱን በር ሁሉ ይጠብቁ ነበር፤ 25 ደቀ መዛሙርት ግን በሌሊት ወስደው በቅጥር ላይ አሳልፈው በቅርጫት አወረዱት።❤️ https://kedusbible.com
𝐀𝐋𝐄𝐌_𝐉𝐄𝐒𝐔𝐒♥️
Region: ET
Saturday 05 September 2026 07:31:03 GMT
Music
Download
Comments
Andualem Abera :
አሜን ❤️❤️❤️
2026-09-20 03:03:58
0
king king :
እውነት ነው ሁሉ በእርሱ ነው አሜን🥰🥰🥰🥰🥰
2026-09-05 08:34:13
0
Badhane Odaa :
Amen
2026-09-07 15:17:13
0
malsachi :
🥰🥰🥰🥰ameeeeen.ameeeenn
2026-09-23 21:05:28
0
marsolfil 🍒🌽🍍🌸ሰብሏ :
2026-09-05 18:41:18
0
አብት ዳስተ :
🥰🥰🥰
2026-09-26 06:34:52
0
Leli :
🥰🥰🥰
2026-09-24 08:05:43
0
selam Eshtu :
🙏🙏🙏🙏
2026-09-22 19:02:56
0
beruk :
🙏🙏🙏
2026-09-19 21:41:05
0
ማሂ :
[Pink heart][Pink heart][Pink heart]
2026-09-19 17:09:31
0
rahelmekasha :
🥰🥰🥰
2026-09-05 16:03:33
0
hafite :
🙏🙏🙏
2026-09-05 07:34:49
0
Hemen traditional clothes :
🥰🥰🥰
2026-09-28 10:52:55
0
To see more videos from user @alemjesus0, please go to the Tikwm
homepage.