@bilalby10: ቤቱን አንተ ገነባኸው… ገንዘቡን አንተ አወጣኸው… ሁሉንም ወጪ አንተ ቻልክ… ግን መሬቱ የሌላ ሰው ከሆነ፣ ቤቱስ የማን ነው? 🤔 ይህን ጥያቄ ለመመለስ በመጀመሪያ አንድ ነገር መረዳት አለብን። መሬት እና በመሬት ላይ የተገነባ ቤት የተለያዩ ጉዳዮች ናቸው። በኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት መሠረት፣ መሬት በግል ባለቤትነት አይያዝም። ሰዎች ግን በመሬት ላይ የይዞታና የመጠቀም መብት ሊኖራቸው ይችላል። በሌላ በኩል፣ አንድ ሰው በራሱ ገንዘብና ጉልበት የገነባው ህንፃ ወይም ቤት ላይ የተለየ የንብረት መብት ሊኖረው ይችላል። ነገር ግን… በሌላ ሰው ሕጋዊ ይዞታ ላይ ቤት መገንባት ብቻ፣ የዚያን መሬት የይዞታ መብት ማግኘት አያስችልም። ስለዚህ፦ ❌ “ቤቱን ገንብቻለሁ፣ እና መሬቱም የእኔ ነው” ማለት አይቻልም። ነገር ግን ይህ ማለት የገነባው ሰው ምንም መብት የለውም ማለትም አይደለም። ጉዳዩ እንደ ውሉ፣ እንደ ፈቃዱ፣ እንደ አገነባቡ እና እንደ ሕጋዊ ሁኔታው ይመረመራል። ይህ መረጃ ለምን ጠቃሚ ነው? ምክንያቱም በሪል እስቴትም ሆነ በግለሰብ ተገንብቶ የምታየውን ህንፃ ብቻ ማየት በቂ እንዳልሆነ እንድናስተውል ያኽል ነው። በዋናነት ከጀርባው ያለውን የባለቤትነትና የይዞታ መብት መረዳት አለብን። #PropertyOwnership #RealEstateTips #EthiopianLaw #bilal
Bilal
Region: ET
Sunday 06 September 2026 06:43:12 GMT
Music
Download
Comments
marvel :
ባልና ሚስት ላይ ሲሆንስ መሬቱ የ ሚስት ነበር እና ከተጋቡ በኃላ ቤቱ ተሰራ የትዳር ዉል ምናምን የላቸውም እና አይበለውና ቢፋቱ ምንድነው ሚሆነው
2026-09-06 16:38:55
1
Aelaf. :
ባልና ሚስት ከሆኑስ በ አንዱ ተጋቢ መሬት ላይ ቢሰራ?
2026-09-06 16:37:43
1
KT bike :
bayhon mezmuru temechtognal🔥
2026-09-06 17:41:09
1
kalina :
😏😏 enenja
2026-09-08 19:03:11
1
Hundaaol legus Benti :
ሰውየው ሳይፈቅድልህ እንዴት ትገነባለህ?
2026-09-06 16:01:35
1
Z red devil's :
enat abat behywet eyalu saykawemug serche .neber ahun abat enat simot akaflen alu ksm jemrewal wendm ena eht bestotam bemnm aydelem befkadegnet neber ::yemtawmku hasa stug beknnet
2026-09-06 18:56:28
1
wus :
[Heartwarming][Heartwarming][Heartwarming]
2026-09-08 17:25:01
0
Amar🇪🇹Maruf :
🔥🔥🔥
2026-09-06 07:13:05
1
Habiba Kemal :
🥰🥰🥰
2026-09-07 05:42:48
1
To see more videos from user @bilalby10, please go to the Tikwm
homepage.