@h9lull: حرفياً 😭😭 #fypシ #foryou #viral #مسلسلات_سورية #اكسبلور

H | ـبـَه🦢
H | ـبـَه🦢
Open In TikTok:
Region: TR
Sunday 06 September 2026 21:08:52 GMT
14729
1384
13
271

Music

Download

Comments

ry_.m7
la luna 🇮🇶 :
لقطة كاريس وليث يامسلسل؟
2026-09-06 21:49:12
2
a_if4o
- ` 𝐀َ𝐚ِ𝟑𓋜. :
حرفيا 😭😂.
2026-09-09 14:11:40
0
hinata.hiouga6
✧N🪽 :
@✨𝕭𝖑𝖆𝖈𝖐 𝕹𝖔𝖛𝖆✨ @🦢 𓂃 ࣪˖ ִֶָ ◌ @Joyla | INTP
2026-09-07 13:28:23
2
To see more videos from user @h9lull, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

“መስከረም ሁለት” የኔ ና የኔ ባቾች  ማስታወሻ  ( ክፍል አንድ )  መላኩ ብርሃኑ  ገና ጎህ ከመቅደዱ ቤት ለቤት እየዞርን በፉጨትም በድምጽም እንጠራራለን። መላ ! አሼ! ቡችላ ! ያይራድ! አሌክስ! ጭራሞ! ጢሊንጥ! ባምባ! ሚኬሌ! ሰዬ! ጋብሪ! ኡጁሉ! …. ለመሰባሰብ ደቂቃዎች ይበቁናል። አንዳንዶቻችን ከመቸኮላችን ፊታችንን አንታጠብም። ቁርሱን የሚበላ ማንም የለም። ብዙዎቻችን በኪሳችን ሳንቲሞች አይጠፉም። እንቁጣጣሽ አበባ ያዞርንበት አምሳም ሰባአምስት ሳንቲምም ይኖረናል።  ይቺ ቀን ከእንቁጣጣሽ ቀጥለን የምንናፍቃት ቀናችን ናት። መስከረም ሁለት እንዲህ በቀላሉ አይነጋልንም።  የኦሎምፒያ ልጆች ነን። 18 ቶች እንባላለን። የቀበሌያችን ስም ነው። ከላይ ሰፈር ታች ሰፈር ድረስ ተጠራርተን እንደተሰባሰብን ፈጠን ፈጠን እያልን ወደእስጢፋኖስ እናዘግማለን። ቀን ልናየው የምንችወለውን ትዕይንት እንገምታለን።  “ስማማ …የኛ ታንኮች እኮ ከእስራኤል ይበልጣሉ…”  “ጀቶቹስ ቢሆኑ! ደሞ እሪኮፍተር ባንዲራ ይበትናል ተብሏል”  “እየውላችሁ! ሌሊት ሚሳይል ተተኩሷል መሰለኝ ዛሬ” “እረ ባክህ አትዋሽ…መድፍ ነው እንጂ ሚሳይል ይተኮሳል እንዴ ደሞ!” “አየር ወለዶቹ ዛሬ ይገለባበጣሉ ተብሏል …እንዳያመልጠን”  ይህንን እያወራን …አንዳችን ከአንዳችን በላይ ለመደመጥ እየተሽቀዳደምን ቤተክርስቲያን እንደርሳለን። የእስጢፋኖስን በሮች እየተሳለምን ዙሪያውን እንዞራለን። ያደግንበት ደብር ነው...ብዙ ያየንበት...ከዚያም ተጣድፈን እንወጣለን።  ቦታ እንዳይያዝብን እየተራኮትን ፊት ከሚገኙት የድንጋይ መቀመጫዎች ላይ በተርታ ተደርድረን እንቀመጣለን። እፎይ! …ድንጋዮቹ አልተያዙም… ከዚህ በኋላ ብዙ መቶ ሺህ ሰዎች ከኋላችን ይደረደራሉ። ገና ቦታ ጠፍቶ ብዙዎች ይበሳጫሉ። እኛ ግን አንደኛ ደርሰናል። ሳቅ በሳቅ ሆነን ፊልም ቤት ገብቶ እስኪጀምር ድረስ ባዶ ስክሪን ላይ እንደሚያፈጥ ሰው በባንዲራ እና በዘምባባ ወዳጌጠው “ወደክብር ወደትቢዩኑ”  እናፈጣለን። እዚያ ላይ መንጌ ይመጣና ይናገራል። ሰላምታ ሲሰጥ ማየት እንፈልጋለን። በኋላ ሰፈር ስንመለስ እንደሱ ሰላምታ መስጠት እንለማመዳለን። ወደበኋላ ወላጆቻችን በቀበሌ በቀበሌ ተሰልፈው መምጣታቸው አይቀርም። እኛ ቀድመናቸዋል። ስንወጣ ቤተክርስቲያን እንሂድ ብለን አስፈቅደን ነው። እንዳትጠፉ ተያያዙ ተብለን ነው የተሸኘነው።አሁን ያለነው ግን አብዮት አደባባይ ነው። ከሰዓታት በኋላ የምንናፍቀው ትዕይንት ይጀምራል። አሁን ጸጥ ያለች የምትመስለው አብዮት አደባባይ በኋላ ቀውጢ ትሆናለች። ዝማሬ! የወታደር ሰልፍ ትዕዛዝና የከስክስ ጫማ ኮቴ ጩኸት …የጦር መሳሪያዎች ትዕይንት …በላይ የሚያንጃብበው ሄሊኮፕተር ….በምድር የሚርመሰመሰው ሰልፈኛ የምድር ሃይል…እነሱን እያሰብን ደስ ይለናል። ብርዱ እያንቀጠቀጠን በኋላ በምትወጣው ጸሃይ እንጽናናለን። አይርበንም። በዓመት አንድ ቀን በጉጉት ጠብቀናት የምትመጣው መስከረም ሁለት ቀን ከእንቁጣጣሽ እኩል ለኛ ሰፈር ልጆች የደስታ ቀናችን ናት። ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ሳይሞላ አብዮት አደባባይ ይሞላል። ግርግር ይሆናል። ዩኒፎርማቸውን አሳምረው የለበሱ ፖሊሶች ያስተናብራሉ። ሰፊው አስፋልት ጭር ይላል። ሰልፈኞቹ የሚያልፉት በዚያ ነው። በካርቶን ላይ የተጻፉና በአጠና የተሰቀሉ መፈክሮች እዚህም እዚያም ሰው ተሸክሟቸው ይወዛወዛሉ። መሃላቸው ለንፋስ ማሳለፊያ በተቀደዱ ጨርቆች ላይ የተጻፉ ረጃጅም መፈክሮች በሁለት ሰዎች ተወጥረው ይታያሉ።  እኛ ጊዜው እስኪደርስልን መፈክሮቹን ተሽቀዳድመን እናነባለን።  “አብዮታዊት እናት ሃገር ወይም ሞት!” ….“ከጓድ መንግስቱ ሃይለማርያም አብዮታዊ አመራር ጋር ወደፊት!” …”ኢትዮጵያ ትቅደም!” …
“መስከረም ሁለት” የኔ ና የኔ ባቾች ማስታወሻ ( ክፍል አንድ ) መላኩ ብርሃኑ ገና ጎህ ከመቅደዱ ቤት ለቤት እየዞርን በፉጨትም በድምጽም እንጠራራለን። መላ ! አሼ! ቡችላ ! ያይራድ! አሌክስ! ጭራሞ! ጢሊንጥ! ባምባ! ሚኬሌ! ሰዬ! ጋብሪ! ኡጁሉ! …. ለመሰባሰብ ደቂቃዎች ይበቁናል። አንዳንዶቻችን ከመቸኮላችን ፊታችንን አንታጠብም። ቁርሱን የሚበላ ማንም የለም። ብዙዎቻችን በኪሳችን ሳንቲሞች አይጠፉም። እንቁጣጣሽ አበባ ያዞርንበት አምሳም ሰባአምስት ሳንቲምም ይኖረናል። ይቺ ቀን ከእንቁጣጣሽ ቀጥለን የምንናፍቃት ቀናችን ናት። መስከረም ሁለት እንዲህ በቀላሉ አይነጋልንም። የኦሎምፒያ ልጆች ነን። 18 ቶች እንባላለን። የቀበሌያችን ስም ነው። ከላይ ሰፈር ታች ሰፈር ድረስ ተጠራርተን እንደተሰባሰብን ፈጠን ፈጠን እያልን ወደእስጢፋኖስ እናዘግማለን። ቀን ልናየው የምንችወለውን ትዕይንት እንገምታለን። “ስማማ …የኛ ታንኮች እኮ ከእስራኤል ይበልጣሉ…” “ጀቶቹስ ቢሆኑ! ደሞ እሪኮፍተር ባንዲራ ይበትናል ተብሏል” “እየውላችሁ! ሌሊት ሚሳይል ተተኩሷል መሰለኝ ዛሬ” “እረ ባክህ አትዋሽ…መድፍ ነው እንጂ ሚሳይል ይተኮሳል እንዴ ደሞ!” “አየር ወለዶቹ ዛሬ ይገለባበጣሉ ተብሏል …እንዳያመልጠን” ይህንን እያወራን …አንዳችን ከአንዳችን በላይ ለመደመጥ እየተሽቀዳደምን ቤተክርስቲያን እንደርሳለን። የእስጢፋኖስን በሮች እየተሳለምን ዙሪያውን እንዞራለን። ያደግንበት ደብር ነው...ብዙ ያየንበት...ከዚያም ተጣድፈን እንወጣለን። ቦታ እንዳይያዝብን እየተራኮትን ፊት ከሚገኙት የድንጋይ መቀመጫዎች ላይ በተርታ ተደርድረን እንቀመጣለን። እፎይ! …ድንጋዮቹ አልተያዙም… ከዚህ በኋላ ብዙ መቶ ሺህ ሰዎች ከኋላችን ይደረደራሉ። ገና ቦታ ጠፍቶ ብዙዎች ይበሳጫሉ። እኛ ግን አንደኛ ደርሰናል። ሳቅ በሳቅ ሆነን ፊልም ቤት ገብቶ እስኪጀምር ድረስ ባዶ ስክሪን ላይ እንደሚያፈጥ ሰው በባንዲራ እና በዘምባባ ወዳጌጠው “ወደክብር ወደትቢዩኑ” እናፈጣለን። እዚያ ላይ መንጌ ይመጣና ይናገራል። ሰላምታ ሲሰጥ ማየት እንፈልጋለን። በኋላ ሰፈር ስንመለስ እንደሱ ሰላምታ መስጠት እንለማመዳለን። ወደበኋላ ወላጆቻችን በቀበሌ በቀበሌ ተሰልፈው መምጣታቸው አይቀርም። እኛ ቀድመናቸዋል። ስንወጣ ቤተክርስቲያን እንሂድ ብለን አስፈቅደን ነው። እንዳትጠፉ ተያያዙ ተብለን ነው የተሸኘነው።አሁን ያለነው ግን አብዮት አደባባይ ነው። ከሰዓታት በኋላ የምንናፍቀው ትዕይንት ይጀምራል። አሁን ጸጥ ያለች የምትመስለው አብዮት አደባባይ በኋላ ቀውጢ ትሆናለች። ዝማሬ! የወታደር ሰልፍ ትዕዛዝና የከስክስ ጫማ ኮቴ ጩኸት …የጦር መሳሪያዎች ትዕይንት …በላይ የሚያንጃብበው ሄሊኮፕተር ….በምድር የሚርመሰመሰው ሰልፈኛ የምድር ሃይል…እነሱን እያሰብን ደስ ይለናል። ብርዱ እያንቀጠቀጠን በኋላ በምትወጣው ጸሃይ እንጽናናለን። አይርበንም። በዓመት አንድ ቀን በጉጉት ጠብቀናት የምትመጣው መስከረም ሁለት ቀን ከእንቁጣጣሽ እኩል ለኛ ሰፈር ልጆች የደስታ ቀናችን ናት። ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ሳይሞላ አብዮት አደባባይ ይሞላል። ግርግር ይሆናል። ዩኒፎርማቸውን አሳምረው የለበሱ ፖሊሶች ያስተናብራሉ። ሰፊው አስፋልት ጭር ይላል። ሰልፈኞቹ የሚያልፉት በዚያ ነው። በካርቶን ላይ የተጻፉና በአጠና የተሰቀሉ መፈክሮች እዚህም እዚያም ሰው ተሸክሟቸው ይወዛወዛሉ። መሃላቸው ለንፋስ ማሳለፊያ በተቀደዱ ጨርቆች ላይ የተጻፉ ረጃጅም መፈክሮች በሁለት ሰዎች ተወጥረው ይታያሉ። እኛ ጊዜው እስኪደርስልን መፈክሮቹን ተሽቀዳድመን እናነባለን። “አብዮታዊት እናት ሃገር ወይም ሞት!” ….“ከጓድ መንግስቱ ሃይለማርያም አብዮታዊ አመራር ጋር ወደፊት!” …”ኢትዮጵያ ትቅደም!” … "አንዲት እናት ሃገር ወይም ሞት! " … አንዱንም አንሳሳትም። በቃላችን ያጠናናቸው መፈክሮች ናቸው። እኛም አንረሳቸውም እነሱም በየዓመቱ ከዚያ ቦታ አይጠፉም። ማርክስ ሌኒን እና ኤንግልስ ጓደኛሞች መስለው ተደርድረው በተነሱት ግዙፍ ፎቶ ከኋላችን ከብደውናል። ከፊት ክቡር ትሪቢዩኑ ላይ የመንጌ ፎቶ ገጭ ብሎ ሁሉንም በአርምሞ የሚመለከት መስሏል። አካበባቢው አብዮት አብዮት ይሸታል...ደሞም አብዮት አደባባይ መግቢያ ላይ “ወዛደራዊ አለምአቀፋዊነት ይለምልም” የሚል የተጻፈበት ግዙፍ ሳይን ጌት ለዘመናት በቆመበት አለ። ዱርዬ የምንላቸው ልጆች እዛ ላይ ሁሉ ወጥተው ትዕይንቱን ይመለከታሉ። በጸሃይ ከስሎ የተጠራሞተ ገጽታ ያለው የምናውቀው ጭቁን ህዝብ ፣ የየቀበሌው ሰልፈኛ የካርቶን መፈክሩን እያነበነበ ግራ እጁ እስኪገነጠል ከመፈክሩ ጋ እየወነጨፈ ይመጣና አብዮት አደባባይን ይሞላዋል። “ያለሴቶች ተሳትፎ አብዮቱ ግቡን አይመታም” የሚል መፈክር የያዙ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ጥለት ያለው ሸማ የለበሱ አኢሴማዎችም እንዲሁ እየፎከሩ ይመጣሉ። አብዮት ጠባቂዎች በብርማ ቀለም ልብሳቸው ቆመህ ጠብቀኝ ጠመንጃ ይዘው በሰልፍ ይመጡና ህዝቡን ይቀላቀላሉ። አስፓልቱ ግን ጭር እንዳለ ወታደራዊ ሰልፈኞቹን ይጠብቃል። ጸሃይዋ መክረር ትጀምራለች። እኛም ሽንብራ ዱቤ ገዝተን መቆርጠም እንጀምራለን። ሸንኮራ አዟሪዎች አንድ አንጓ በአምስት ሳንቲም ይሸጡልናል። ውድ ነው። ግን መስከረም ሁለት ስለሆነ እኛም ሃብታም ስለሆንን ችግር የለም። ዝንብ በዝንብ ብንሆንም ደስ ይለናል። አይደክመንም አይርበንም አይጠማንም። 3 ሰዓት አካባቢ ሲሆን ስነስርዓቱ ይጀመራል። መንጌ ወታደራዊ ዩኒፎርሙን ለብሶ አንዲት ዘንግ ይዞ ትሪቢዩኑ ላይ የሚጠብቁት እንግዶች መሃል ድንገት ከች ይላል። እልልታውና ጭብጨባው ይጦፋል። ከዚያ በኋላ አስተዋዋቂው በማይክራፎን የሚለፍፈው ነገር ያደነቁረናል። “እዮሃ መስከረም ሁለት አዲስ ዘመን አዲስ ልደት “ የሚለው መዝሙር በሜጋፎን ይንቆረቆርልናል። አብረን እንዘምራለን። ዘፈኑ ደስ ሲል...የሆነ አመት ባል ነገር ይመስላል መንጌ በወታደራዊ ዩኒፈፎርሙ ደምቆና ኮስተር ብሎ ከዘለዓለም የረዘመ ንግግር ያደርጋል። እየተቆጣ! እየጮኸ! እየረገጠ! እየፈረከ …እኛ ግን አንሰማውም። ይሰለቸናል። እናወራለን። እንንጫጫለን። አጠገባችን ያሉ አዋቂዎች በኩርኩም ቆግተው ዝም እስኪያስብሉን ቂጣችንን ድንጋይ ላይ እየፈተግን ወሬያችንን እንቀዳለን። ጃኬት ያለው በጃኬቱ ጸሃይዋን ይከላከላል። የሌለን እንደሰም አንቀልጣለን። መንጌ ሲጨርስ ህዝቡን መፈክር ያስፈክራል። አብረን እንፈክራለን። ከዚያም ፉጨትና ሁካታ ይከተላል።

About