@melkamukassaw148: ጊዜ መስታውት እሁድ ጠዋት ቅዳሴ አስቀድሰው በነጭ አሸብርቀው መላዕክት የሰፈሩበት ይመስለል መንገዱን የሚያደምቁት ሙስሊሙ በመስጊድ ሁሉም በየ ሀይማኖቱ በዓል ሲደርስ ዘመድ አዝማዱን ለመጠየቅ ሁሉም በአቅሙ ያለውን ይዞ በየመንገዱ ሽር ጉድ የሚለው ትውልድ የት ገባ ? ሰኞ ጠዋት ልጆቹን ትምህርት ቤት ለማድረስ በግራ በቀኝ እጆቻቸውን ይዞየሚሄደው፣እረኛው እስኪወጣ ከብት ፍየሉን በአማጋው የሚቆረቁረው አባት የት ገባ? ከቤታችን ወጥ ሳይኖር ቀርቶ ሂድ አልማዝ ታርግልህ ተብሎ እንጀራውን በሳህን ይዞወጥ ለማስደረግ ጎረቤት ጋር የሚሄደው ወርቅ ትውልድ ምን ዋጠው? የቡሄ(ሆይላልየ) ቀን አብረውን ሆያሆየ ያሉት እነ ከድር፣ሙሀሙዴ ፣ሰይድ...የት ደረሱ? ጳጉሜን ስንጠመቅ ሌሊት አብረውን አራቱ ሻንዳ ፣ዋሴ መስክ የሚጠመቁት እነ ሲራጅ የት ናቸው? የቅዱስ ዮሀንስ (እንቁጣጣሽ) አበባ አየሽ ወይ ብላ የጨፈረችው መዲና ሰይድ ምን ላይ ሆና ይሆን የተበተኑት ጓደኞቻችን የት እና በምን ላይ እንዳሉ አስበን አናውቃለን ወይስ አብሮ ማደግ ብቻ ለመውሊድ ዳቦ እና ቴምር ለመብላት ሮጠን የሄድነው ትውልዶች የት ገብተን ነው ያ ሁሉ ጨዋታ ሳቅ ደስታ የሰፈሩ ወጣት ወደማታ በአንድ ላይ ቁጭ ብለን የምንስቀው ስልክ የለ ምን የለ ያልተበከለውን ትውልድ ምኑ አደነዘዘው? ትልልቅ ሰወች ከገበያ ዘምቢል አንጠልጥለው ሲመለሱ ስናይ ሮጠን ተቀብለን ቤታቸው አድርሰን ያሳድግህ ሰርግህን ያብላኝ .....ተብለን ተመርቀን ያደግነው ትውልዶች የት ነን? ሌባ እና ፖሊስ ፣አኩኩሉ ድብብቆሽ ፣አርጣባ አርጣባ ለመጫወት እነ መላኩ ሽባባው፣ እነእንዳልኬ፣እነ ማስተዋል ወንዴ ፣እነ ገነት ሽባባው ፣እነ መልካሙ አሰሙ ኧረ ስንቱን በተለይ ጨረቃዋ ስትወጣ ደስ ብሎን ያደግንባት ሰፈራችንእንዴት ሆና ይሆን? በዓል ሲደርስ በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ስራ እና ትምህርት ላይ የነበሩ ጓደኞቻችን በዓል ለማክበር ወደ ቤተሰብ ሲመጡ አይ የነበረ ድምቀት ከምግብ በኋላ ለመጨፈር በቡድን በቡድን ትልልቆቹ ከሌሉበት ሆቴል መርጠን ሻሸመኔ ሆቴል፣ዞዝ አምባ ሆቴል ፣ኦባማ ሆቴል፣የትዝታ ቅንጡ ሆቴል አይ ጉድ በቅቤ የታሸ ምግብ መጠጥ ፣ስጦታ ለመግዛት የፀጋየ አስፋው ሱቅ፣የእውነቱ ዋሴ ሱቅ የመንግስት እንደሻው ልብስ ቤት፣የወልዴ ቡቲክ የነዝናሽ ዋለ ምግብ ቤት ፣የማንደፍሮ በዜ ጠጅ ቤት ፣የጌጡ ካሳው ፊልም ቤት ፣እነካስየ መንግስት ከተማውን በብስክሌት ቅንጡ አነዳድ ሲያደምቁት ፣የደባሽ ፀጉር ቤት አይይይይይይይ በቀን በሌሊት ለመዝናናት አንዴ አርባያ፣ሀሙሲት ፣እብናት፣ ሄደን የምንደምቀው ትዝ ትዝ ይለኛል ይመለስ ይሆን ያ ወርቃማ ጊዜ? የአዲስ አመት ትክክለኛው የልጅነታችን የዋዜማ መልክ የተገዛልንን ልብስና ጫማ እንደለበስን የምንተኛው ፣ ድፎ ዳቦ በዳንቴል ተሸፍኖ ጠረጴዛ ላይ አለ (ለነገ ነው😁)፤ ችቦ የወጣበት ቤት ድባብ ቡናው ከፈንድሻው ጋር ፣ሶፋው ከእግሩ ጋ ዘርፈፍ ያለ ልብስ ለብሶ ዳንቴል ከላዩ ላይ ጣል ጣል ተደርጎበት በዋዜማው ( ለነገ ይቆሽሻል እሱ ጋ እንዳትቀመ😁) ቦርጫሙ ቲቪ፣National panasonic ቴፕ ፣ዴክ mayota cd player ሁሉም ዳንንቴል ይለብሳል። ቄጠማ ተጎዝጉዞ ቡና ሲፈላ ዙሪያውን ከበን ቁጭ ብለን የነበረው ደስታ ሊነጋ ሲል ኑ ዶሮ እረዱልን ተብለን ከጎረቤት የምንጠራው ኧረ ስንቱ ይህን ደግ ዘመን እንመልሰው እንፀልይ፣እንከባበር፣ከቂም እንውጣ እስኪ እንጠያየቅ እንፈላለግ ይን አይቶ ደጉን ዘመን ይመልስልናል ጌታ ሆይ ታረቀን!!! ያች በለሳ ኢትዮጵያ ናፍቃኛለች
@𝙈𝙚𝙡𝙠𝙖𝙢𝙪✔️
Region: ET
Monday 07 September 2026 12:08:07 GMT
Music
Download
Comments
@🦋🫅🦋 :
🥰🥰💕
2026-09-07 12:30:11
0
To see more videos from user @melkamukassaw148, please go to the Tikwm
homepage.