@dagemawi.bizuye2: #የቅዱስ ሩፋኤል ታሪክ በአጭሩ አንብቡት#👇👇👇👇# በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን.. የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት፣ የፈለገ ሕይወት ሰላም በር ቅዱስ ሩፋኤል እና አቡነ ዘራቡሩክ ቤተ ክርስቲያን ነው። ይህ ታሪካዊ ቦታ ገብረ ተአምራት ወመንክራት በየደቂቃው፣ በየዕለቱ፣ በየሳምንቱ፣ በየወሩ፣ በየዓመታቱ ሁሉ ከአእምሮ በላይ፣ አንደበት ከሚገልጸው፣ በቃላት ሊገለጽ የማይችል፣ ግን በመንፈሳዊ ዓይን ብቻ ታይቶ እጹብ እጹብ በመባል ብቻ የምንይዘው ታሪክ የሚፈጸምበት፣ ልክ እንደ ሰለስቱ ደቂቅ እና እንደ ቂርቆስ እየሉጣ ዓይነት ተአምራት የሚፈጸምበት እጅግ በጣም ሰፊ ሕዝብ ነው። የሚመጣው ሕዝብ ደግሞ ይህንን አገልግሎት ለማግኘት በመጀመሪያ ከ... አምስቱን ቀን ነበረ የጀመርነው፣ ሕዝቡ በበዛ ቁጥር እና በላላቅ አባቶች እኛንም ጨምሮ አንድ ሱባኤ መሙላት አለበት ብለን፣ ከዚሁ አሁን ልናጠናቅቀው ስላለን ከነሐሴ ወር 30 ቀን በመውሰድ አምስቱን ጳጉሜን አድርገን ከአዲሱ ዓመት ደግሞ አንድ ቀን በመጨመር ሰባት ቀን ወይም ደግሞ አንድ ሱባኤ ይሆናል፤ እና ከነሐሴ 30 እስከ መስከረም 1 ቀን የበረከት የጸበል መጠመቅ ሥነ ሥርዓት ይካሄዳል፤ ወደ አምስት... ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል። ቁጥሩ በጣም ባለን ዳታ እና ባለን መረጃ መሠረት ከ500.000 ( አምስት መቶ ሺህ) እና ምናምን አገልግሎት እንደ አገኘ መረጃው አለን፤ ዘንድሮ ደግሞ ከ900.000 (ዘጠኝ መቶ ሺህ) አካባቢ ሕዝብ ይመጣል ብለን እንጠብቃለን። እና ከሌሎች ቦታ ልዩ የሚያደርገው ይህ ቦታ፦ ከታላቁ ወንዝ ደምበር ተሻጋሪ እና ዓለም አቀፍ ከሆነው ወንዝ ጠገብ በመሆኑ ከሌሎች የጸበል ቦታዎች ልዩ ያደርገዋል፤ በሌላ በኩል ደግሞ ቅዱስ ሩፋኤል (ሊቀ መላእክት ሩፋኤል) እና አቡነ ዘራቡሩክ በአንድ ላይ የተመሠረቱበት በመሆኑ፣ ሁለቱም ታሪካዊ ዳራቸው እጅግ በጣም ከባሕሩ ጋራ ሰፊ እንድምታ ወይም ደግሞ ታሪክ ካለው ጋር በመሆኑም ከሌሎች ዳራ ልዩ የሚያደርገው፣ ልዩ የበረከት ቦታ፣ ክብር የሚሰጥበት ቦታ፤ ብዙ ምዕመናን እና ምዕመናት ለዘመናት ልጅ ያጡ፣ ለዘመናት የልጅ እርሃብ የደፋቸው፣ እነዚህ ለዘመናት የቆዩ እናቶች እና አባቶች የልጅ አባት፣ የልጅ እናት የሆኑበት፣ እንባቸው የታበሰበት፣ ጥያቄያቸው የተመለሰበት ልዩ ቦታ መሆኑን ብዙ ምዕመናን በአውደ ምሕረት እየተገኙ የምስክርነት ቃላት ሰጥተዋል፣ እየሰጡም ይገኛሉ። ቤተ ክርስቲያኗም እንደዚሁ እየጻፈች በታሪክ እየመዘገበች አስቀምጣዋለች። አንድ ቀን በመጽሐፍ ሊሆን ይችላል፣ በተለየ ነገር ለሕዝብ ይፋ፣ አስተማሪ ሊሆን የሚችል በመጽሐፍ የተደገፈ ልናወጣ እንችላለን። ባጭሩ ከረጅም ባጭሩ የቦታው ታሪክ ይህንን ይመስላል። ቦታው ከተመሠረተ ስድስት ዓመት አስቆጥሮ፣ ሰባተኛ ዓመቱን ልክ በ2019 ሕዳር 12 ቀን ሦስት ዓመት ሞልተዋል፤ በ2012 ነው የተመሠረተው ወይም ደግሞ ታቦተ ሕጉ ገብቶ ለባሕር ዳር እና አካባቢዋ ሕዝብ፣ እና እንዲሁም ለአጎራባች ዞኖች ሕዝብ የቦታውን ታላቅነት እየተረዳ፣ እየሰማ፣ እየመጣ ይህንን ፈውስ አግኝተናል። ከማዕከላዊ ሀገርም ሳይቀር ባለን መረጃ መሠረት፣ ከማዕከላዊ ሀገር ከአዲስ አበባ፣ ከተለያዩ የሀገሪቱ ታላላቅ ከተሞች እና ከሀገሪቱ ከአራቱም አቅጣጫ ምዕመናን እና ምዕመናት እየመጡ ልዩ የድኅነት ከተማ መሆኑን፣ የድኅነት ቦታ መሆኑን እየተረዱ ሰፊ ምዕመናን እና ምዕመናት እየተጠቀሙበት ነው። ባጠቃላይ ባጭሩ የቦታው እንትን ይህንን ይመስላል።🙏🙏🙏የቅዱስ ሩፋኤል በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን።🙏🙏
Dagi📽ባለማህተቡ💒💒
Region: ET
Monday 07 September 2026 13:32:53 GMT
Music
Download
Comments
🅰️🅱️ ዘ ደብረምህረት⛪️☦️ :
ሩፋኤል አባቴ🥰🥰
2026-09-07 14:02:38
2
የአምር እግዚአብሔር ☦️☦️☦️ :
🥰🥰
2026-09-07 18:40:00
1
ወይኩን ✝️ ፈቃድከ 🤲❤❤💖💐 :
ሩፋኤል አባቴ🙏
2026-09-07 14:19:21
1
Miss_Bemi👑 :
🥰🥰🥰
2026-09-07 13:45:47
1
kalua👸✨ :
🥰🥰
2026-09-07 14:08:34
0
eskedar :
🙏🙏🙏🙏🙏
2026-09-07 15:30:45
0
e.r.m.i.y.a.s._ :
🥰🥰🥰
2026-09-08 03:44:47
0
To see more videos from user @dagemawi.bizuye2, please go to the Tikwm
homepage.