@bilalby10: ከመሬትህ በታች ወርቅ ቢገኝ፡ “ከመሬቴ ሥር ስለተገኘ ወርቁ የኔ ነው!” ማለት ነው? አይደለም በኢትዮጵያ የማዕድን ሕግ መሠረት፡ ከምትጠቀምበት መሬት በታች ተፈጥሯዊ ማዕድን ስለተገኘ ብቻ ማዕድኑ የህዝብ እና የመንግስት እንጂ ያንተ ሊሆን አይችልም። የተፈጥሮ ማዕድናት ከመደበኛ ንብረት የተለየ የሕግ ማዕቀፍ አላቸው። አሁን ደግሞ ሁኔታውን እንቀይረው። ፖሊስ በግቢህ ሥር የተቀበረ ዕፅ ወይም ሌላ ሕገ-ወጥ ነገር ቢያገኝ፡ መንግሥት “ ከመሬት ሥር ስለተገኘ እንደ ወርቁ የኔ ነው” ሊል ይችላል? አይችልም ምክንያቱም ማዕድን እና ሕገ-ወጥ ዕፅ ሙሉ በሙሉ የተለያዩ ነገሮች ናቸው። • ወርቅ ወይም ማዕድን፡ ገና ከመጀመሪያው የመሬቱ አካል የሆነ ተፈጥሯዊ ግኝት ወይም ሀብት ነው። • ሕገ-ወጥ ዕፅ ግን በአንድ ሰው የተያዘ፣ ወደ ቦታው የመጣና የተቀበረ ሰው ሠራሽ ነገር ነው። ስለዚህ ዋናዎቹ የሕግ ጥያቄዎች ሊሆኑ የሚችሉት: • ማን ቀበረው? • ማን ያውቅ ነበር? • በነገሩ ላይ ባለቤትነት ወይም ቁጥጥር የነበረው ማን ነው? ከመሬትህ ሥር የሚገኝ ነገር ሁሉ አንድ ዓይነት የባለቤትነት ሕግን አይከተልም። ተፈጥሯዊ ማዕድን ከሆነ የመንግሥትና የሕዝብ ሀብት የሚሆንበት ሕግ አለው። ሰው ሠራሽ ወይም ሕገ-ወጥ ነገር ከሆነ ግን ሕጉ ሁኔታውን፣ የሰውን እውቅና፣ ቁጥጥርና ተጠያቂነት ይመረምራል። ታዲያ “መሬቴ ነው” ስትል መብትህ ምን ድረስ ነው? በኢትዮጵያ የፌዴራል ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 40 መሠረት፡ • መሬትና የተፈጥሮ ሀብት፡ የመንግሥትና የሕዝብ የጋራ ንብረት ነው። መሬት አይሸጥም፣ አይለወጥም። • አንተ የሚኖርህ 1. የመጠቀም መብት (Land use Right/Lease Right)፡ መሬቱን የመጠቀም፣ የመከራየት ወይም የማልማት መብት ይሆናል። 2. በመሬቱ ላይ ያፈራኸው ንብረት፡ በገንዘብህና በጉልበትህ የገነባኸው ቤት፣ የተከልከው ተክል እና የሰራኸው ነገር ሙሉ በሙሉ ያንተ የግል ንብረትህ ነው። ስለዚህ “መሬቴ ነው” ስትል ያንተ የሚሆነው መሬቱ ራሱ ሳይሆን በመሬቱ ላይ ያፈራኸው ንብረትና የመጠቀም መብትህን ነው። #bilal
Bilal
Region: ET
Monday 07 September 2026 17:36:29 GMT
Music
Download
Comments
Entrance Exam :
እጹን ያስቀመጥከው አንተ ወርቁን ያስቀመጠው ፈጣሪ ስለሆነ እና መንግስት የሚገኘውን ወርቅ ቀድሞ ባትጌ ብሏል የምን ማፋፈር ነው።
2026-09-08 02:18:25
22
Rohi Electronics Adama :
እሺ ጣልያን ጥሎት የሄደ ሀብስ ባገኝስ መሬቴ ውስጥ? የማን ነው 😁
2026-09-08 06:41:22
1
ABD የመርኬው 🇪🇹🍁🇯🇲 :
ዕፁ ይሁንልኝ 😁
2026-09-07 17:58:15
3
ⓎⓄⓃⒶⓉⒽⒶⓃ :
አያቴ የቀበረው ወርቅ ቢሆንስ? ሼ ኦጀሌ እዳረጉት??
2026-09-07 21:24:53
0
Lux reel :
ያው ነው ላወቀበት 😉
2026-09-08 06:22:18
1
fatey :
2026-09-11 01:21:52
1
ዑቃብ የመኪና ዕቃ መለዋወጫ :
2026-09-08 17:50:57
1
Navi 1221 :
አለምንም
2026-09-08 15:30:17
0
miss wollo 🦋 :
meretachn lay werq endale yawekut ene 😭
2026-09-07 17:46:32
1
KT bike :
huletum yelelegn ene😂
2026-09-07 19:10:11
1
Naif 📷 :
2026-09-07 18:35:50
2
Razika M :
🥰
2026-09-07 20:10:13
1
rk🤷♂️ :
brother እንዴት ነው ደፈር ብዬ ላንብበው
2026-09-07 17:51:43
2
Boss :
😂😂😂
2026-09-08 05:36:48
1
Habiba Kemal :
🥰🥰🥰
2026-09-07 19:23:11
1
dayyu :
😁😁😁
2026-09-07 17:41:48
1
Rabia/legal advisor :
👏👏👏
2026-09-09 04:20:29
1
To see more videos from user @bilalby10, please go to the Tikwm
homepage.