@unatedstateofguraga: በነገው እለት በታላቅ ድምቀት የሚመረቀው የጉራጌ ዞን አስተዳደር ህንጻን አስመልክቶ የፌደራል ፖሊስ ማርሽ ባንድ በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ትዕይንቱን አሳይቷል። የጉራጌ ዞን አስተዳደር B+G+9 ህንጻ በነገው እለት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ተጋዥ እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ይመረቃል። በጉራጌ ዞን የተገነባው እጅግ ዘመናዊ የዞኑ አስተዳደር( B+ G+9) ህንጻ ነገ በታላቅ ድምቀት ለመመረቅ ዝግጅቱ ተጠናቋል። ስለሆነም የፌደራል ፖሊስ ማርሽ ባንድ ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ በመገኘት የሙዚቃ ትዕይንቱን በዛሬው እለት አሳይቷል። የምረቃ ሥነ-ሥርዓቱን አስመልክቶ ወደ ወልቂጤ ከተማ የገባውን የፌደራል ፖሊስ ማርሽ ባንድ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ላጫ ጋሩማና የዞኑ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በወልቂጤ ከተማ ተገኝተው በክብር ተቀብለዋል። የማርሽ ባንዱ በከተማዋ ያሳየው የሙዚቃ ትዕይንትም ለነገው የምረቃ ሥነ-ሥርዓት የበዓል ድባብን በማጠናከር የከተማዋን ድምቀት አሳድጎታል። ይህ ትልቁ የጉራጌ ዞን አስተዳደር ህንጻ በአጠቃላይ እስከ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የጨረሰ ሲሆን በዞኑ ይስተዋል የነበረው የቢሮ ጥበት ችግር በመቅረፍ ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጥ ያስችላል። በምረቃ ፕሮግራሙ የፌደራል፣የክልል የዞን የወረዳና የከተማ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን። የተንቢ#ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #ጉራጌ_ኩሩ_ነው_ሀገሩን_አይጠላም🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #viraltiktok #viral_video #100k

ወልቂጤ ሚዲያ   🌐
ወልቂጤ ሚዲያ 🌐
Open In TikTok:
Region: ET
Monday 07 September 2026 18:20:13 GMT
1010
103
9
6

Music

Download

Comments

hamel286
የጉራጌው ታኩር🤴🎬 :
ጀግናው
2026-09-07 18:25:19
0
fufuti76
feti የቸሀዋ 🇸🇦🌸 :
🥰🥰🥰♥️
2026-09-07 20:32:19
0
mekiyaalewi
መመመመመሠመመ :
🥰🥰
2026-09-07 19:40:48
0
wonde.man02
wonde man :
🥰🥰🥰
2026-09-07 19:39:23
0
danitamzen
danitam&zen :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-09-07 19:30:44
0
sami231065
@sami :
♥️♥️♥️
2026-09-07 18:33:53
0
mati52343
ⓂⒶⓉⒾ :
🥰🥰🥰
2026-09-07 18:26:12
0
officialneima
Official Kitfo Girl :
🥰🥰🥰
2026-09-07 18:26:08
0
hayat.lshetu
ስናር 💚በበሬታ ቅብሬ🐎💎👈 :
🥰🥰🥰
2026-09-07 20:41:41
0
To see more videos from user @unatedstateofguraga, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About