@solibro46: ❤️ አንዳንድ ሰዎች በትክክለኛው ጊዜ ይገለጣሉ፤ በሚገባው ሰዓትም ይሰናበታሉ የትም ቢሄዱ ግን የሰሩት ታሪክ እና ያበረከሩት ትልቅ ነገር ሁሌም የማይረሱ ትዝታ ሆነው ልባችን ውሥጥ ትልቅ ቦታ ይዘው ይቀራሉ። 🔴 ጃንዋሪ 2023 - አርሰናል ሚካይሎ ሙድሪክን ካሻካታር ወደ ኤምሬትስ ለማዘዋወር ከፍተኛ ጥረት አድርጎ የሙድሪክ ዝውውር በቸልሲ ተጠልፎ አርሰናል የሙድሪክ ዝውውር ከከሸፈ በኋላ ሌላ የመስመር አጥቂ ለማስፈረም ከ Bayer Leverkusen ሙሳ ዲያቢን ለማስፈረም ሞከረ። 💰ነገር ግን ባይር ሊቨርኩሰን ለሙሳ ዲያቢ ዝውውር የጠየቀው የዝውውር ዋጋ 100 ሚሊዮን ዩሮ ነበር አርሰናል እና አርቴታ ክለቡን ያጠናክሩልኛል ብለው ያቀዱትን ዋና የዝውውር ኢላማዎቹን ሙድሪክ ወይም ሙሳ ዲያቢን ለማስፈረም እያደረገ ይገኝ የነበረው ጥረት እየከበደ ሲመጣ የጃንዋሪ ዝውውር መስኮቱ ሊዘጋ 10 ቀናት ብቻ ቀርተው ነበር። ‼በዚያ ወቅት አርሰናል ወደ ሶስተኛው አማራጭ ማንም ሳይጠብቀው ፊቱን ወደ ሊአንድሮ ትሮሳርድ አዞረ ሊአንድሮ ትሮሳርድን በርካሽ የዝውውር ገንዘብ ከብራይተን አስፈረመ ከዚያ በኋላ ቤልጄማያዊው ክንፍ ተጫዋች ወደ አርሰናል እንደተዘዋወረ በቡድኑ ውስጥ ተጽእኖ መፍጠር እና ወሳኝ ተጫዋች እየሆነ ከግዜ ወደ ግዜ በቡድኑ ውስጥ ወሳኝ ሚና መወጣት ጀመረ። 🔰ሊዮ አርሰናል ቤት ጨዋታውን በቋሚነት ጀመረም ከተጠባባቂ ወንበር ይነሳ ብቻ ሜዳ ላይ ካለ የቡድኑ የጎል ምንጭ መሆኑን አስመሰከረ በተለይም በትልልቅ ጨዋታዎች ላይ ለቡድኑ የሰጠው ግልጋሎት ያስቆጠራቸው ጎሎች በደጋፊዎች ዘንድ የማይረሳ ነው። 👟በአርሰናል ቤት የውል ግዜው ማብቂያ አመት ላይ ባለፉት 2 የውድድር ሲዝን ከሳውዲ አረቢያና ቱርክ የተሻለ ደመወዝ እና ጥቅማ ጥቅም የሚያቀርቡ ክለቦች እሱን ለማስኮብለል ከፍተኛ ፍላጎት ማሳየት ጀመሩ ፣ አርሰናልም እሱን በክለቡ ማቆየት የ2 ዓመት የውል ማራዘሚያ ኮንትራት አቅርቦለት በአርሰናል አዲስ ውል ፈረመ። 🪪ሊዮ አርሰናል ከ22 አመታት በኋላ የሊጉን ዋንጫ ሲያሸንፍ መቼም የማይረሱ ወሳኝ ጎሎችን በማስቆጠር በተለይም የሊጉን ዋንጫ እንድናሸንፍ ያረጋገጠችልንን ጎል ዌስትሃም ላይ ያስቆጠራት ጎል ማንም የማይረሳት ጎል ነበረች የሊጉን ክብር ካጎናጸፉን ሌጀንዶቻችን አንዱ ቤልጄማዊው ሊዮ ጣፋጭ እና የማይረሱ ትዝታዎችን በልባችን አስቀምጦ ነገር ግን አንድ ቀን ከሚወደው ክለብ መለያየት እንደሚመጣ አይቀሬ ነበር። 🪫የመድፉ ጀግና ክለቡን ወደ ክብሩ መልሶ ከክለቡ ጋር መለያየቱ እውን ሆነ እሱን ለማስፈረም የሊጉ ክለቦች ፍላጎት ቢኖራቸውም እሱ ግን ይህን ክለብ ይህን ደጋፊ ተቃራኒ ሆኜ ከአርሰናል ጋር የመጫወት ሞራልም ፍላጎትም የለኝም ብሎ ወደ ቱርኩ ክለብ ፊነርባቼ ዝውውሩ በጸጥታ ተጠናቀቀ አርሰናል ለአዲሱ ሲዝን ቅድመ ዝግጅት ሊያደርግ ቡድኑ ወደ ካምፕ እየተመለሰ ጀግናችን ትሮሳርድ ግን ለንደንን ለቆ ወደ ቱርክ አመራ፤ ከቡድን አጋሮቹም ሆነ ከጫፍ ጫፍ ስሙን እየጠሩ የዘመሩለትን ደጋፊ በትክክል እና በክብር ሳይሰናበት ክለቡን ለቆ ሄደ... 🥹 ትናንት ግን የቀድሞ ቡድኑ በለንደን ደርቢ ከቸልሲ ጋር ጫወታውን ለሚመለከት እና የቀድሞ ቡድኑን ለመደገፍ ወደ Emirates ተመለሰ ታሪክ በሰራበት ስታድየም መቀመጫ ላይ ተቀምጦ የቀድሞ የቡድን ጓደኞቹ ዳግም ለንደን ቀይ መሆኗን ባስመስከሩበት ምሽት ጨዋታውን ስታድየም ተገኝቶ ተመለከተ፣ ከክለቡና ከቡድን አጋሮቹ እና ከደጋፊዎቹም በመጨረሻ የሚገባውን ስንብት አደረገ። ❤️ 🎯አስገራሚው ነገር ደግሞ ቅዳሜ ቡድኑ ቤሽኪታሽ ከ ፊነርባቼ በነበረው ጫወታ ሊዮ ትሮሳርድ ቡድኑ ቤሺክታሽ ፌነርባቼን 2–1 ባሸነፈበት ጫወታ አሲስት አድርጎ ቡድኑ እንዲያሸንፍ አግዟል። 🥁እሁድ ምሽት ደግሞ Emirates ተቀምጦ የተመለከተው አርሰናል፣ የእሱ አልጋ ወራሽ ሆኖ ወደ ኤምሬትስ የመጣው ክርስቶስ ዞሊስ አርሰናል የለንደን ደርቢውን በድል እንዲወጣ ያስቻለችውን ጎል ለማርቲን ኦዲጋርድ አሲስት በማድረግ ቼልሲን 2–1 ስናሸንፍ አልጋ ወራሹን ኤምሬትስ ተቀምጦ ተመለከተ በድሉም ተደሰተ። ♨ህይወት እንዲህ ናት አንዱ በአዲሱ ቤቱ ድል እያከበረ፣ ሌላው ደግሞ በቀድሞ ቤቱ የመጨረሻ ምስሉን እየተመለከተ ድሉን እያጣጣመ ተመለከትን አንዳንድ አጋጣሚዎች እንዲህ ናቸው ሊዮ ክለቡን የለቀቀው እንደተወደደ ነው እንዲህ አይነት ታሪኮች በምስጋና ይጠናቀቃሉ። ‼ከሊዮ ጋር አብረን ያሳለፍነው የማይረሳ ጣፋጭ ጊዜ ውድ ነበር። ለክለባችን ላረክልን ሁሉ እናመሰግናለን፣ Leandro Trossard. ❤️🔴
𝐀𝐫𝐬𝐞𝐧𝐥🎱ᵖᵃᵍᵉ Ø𝐝🇧🇷𝐅ዬ
Region: ZA
Monday 07 September 2026 19:39:15 GMT
Music
Download
Comments
𝗗𝗿.𝗘𝘀𝘁𝗶𝗳𝗮𝗻𝗼𝘀☆☆☆☆ :
Our Genius no 19🥰🥰
2026-09-08 04:45:16
3
Gundo mesqle 14🇪🇹🇦🇪 :
ፉቅርዬ ሊዮ❤️❤️❤️
2026-09-08 01:56:30
3
Abi@^<>"-kabera@90 :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-09-08 04:37:41
0
A B :
እንወደዋለን
2026-09-08 17:03:25
0
kiyya si ? :
2026-09-08 07:53:13
0
Haftom :
2026-09-08 11:49:31
0
kiyya si ? :
😭😭
2026-09-08 07:55:53
0
sami entchawi :
🥰🥺
2026-09-08 12:42:16
0
Kiyaye kiya Kiya :
mnale aresenal bet west bikoy eskiakom ders
2026-09-07 21:46:23
1
🎧🅜___ታጋሹ 🤳 :
🥰🥰🥰
2026-09-07 20:06:09
1
𝑻𝒆𝒎𝒆𝒔𝒈𝒆𝒏 ♠️💬 :
🥰🥰🥰
2026-09-08 11:23:39
0
MELU TESIFA💔🥀🥀🥀💔 :
🥰🥰🥰🥰
2026-09-08 08:17:11
0
MUller :
🥰🥰🥰🥰🥰
2026-09-08 09:29:59
0
To see more videos from user @solibro46, please go to the Tikwm
homepage.