@mulenigusse7: የሚካያ በኃይሉን «አንተ ልጅ የፊቱ» የሚለውን የሙዚቃ ግጥም የመተንተን ሥራችንን ቀጥለናል። በመቀጠል የሚመጣው አዝማች ደግሞ እንደ ናዳ የወረደ ነው! ስሜትን ለመግለጽ በቀረቡት ቃላት ከመደመም ውጭ አማራጭ የሚያጣበት ቦታ እዚህ ጋር ነው። የስነ-ግጥም ነገር የሚማርክህ ሰው ከሆንክ፣ ዘፈኑ የፈለገ ስሜትህን ቢነካውና አንተም ተመሳሳይ ታሪክ ኖሮህ በእንባ እየታጠብክ እየሰማኸው ቢሆን እንኳ፣ ልክ እዚሁ አዝማች ላይ ስትደርስ የግድ ከዘፈኑ ስሜት ወጥተህ ስለ ግጥሙ ጥበብ ትደመማለህ። «እንዴት! ሰው ራሱን በዚህ ደረጃ አሳልፎ ይሰጣል?» የሚለው ጥያቄህ እንዳለ ሆኖ፣ «ሰው እንዴት በዚህ ደረጃ ስሜቱን ይገልጻል?» የሚለው ደግሞ ያይላል። ላንተ ያልሆነ ገላ እንደ ቅጠል ይርገፍ ላንተ ያልሆነ ዕድሜ እንደ ጥላ ይለፍ !ገላዋ እንደ ቅጠል እንዲረግፍ፣ ዕድሜዋ ደግሞ እንደ ጥላ እንዲያልፍ ነውኮ ያለችው! ቃላቱ ከየት መጡ? «እንደ ጥላ ይለፍ» ይባላል? እንዲህ ዓይነቱ አገላለጽ ሌሎቹን ገጣሚዎች ማሳቀቅ አይሆንም? አጃኢብ ነው! አንተ ልጅ አንተ ልጅ የፊቱ... ደጄን ሞልቶ ተርፎ በሰው ተከብቤ ሰው ያለ አይመስለኝም አንድም አጠገቤ አስር ወዳጅ ይዤ አንድም ላይፈይዱ ፍቅርህን አባሱት ሲመጡ ሲሄዱ በምድር ወንዶች ላይ ተስፋ እንደቆረጠች ከላይ አይተናል። ነገር ግን ተስፋ የቆረጠችው ሳትሞክር ቀርታ አይደለም፤ ሞክራለች። ወጣትና ቆንጆ ሴት ናት፤ ወንዶች በዙሪያዋ የሚያንዣብቡባት፣ ደጇ በሰው ሞልቶ የተረፈ። ከአንዣበቡትም መካከል የተወሰኑትን አቅረባ ድጋሚ ማፍቀር ከቻልኩ ብላ ሞክራ ነበር። ግና አንድም የፈየደላት አልነበረም። የእነሱ መመላለስ ይልቁንም የእሱን የተዳፈነ ፍቅር እየቆሰቆሰ ከማባስ የዘለለ ጥቅም አልሰጣትም። የእነሱን የመቀያየር አታካች ሂደት አለዝባ ስትገልጸው፦ «ፍቅርህን አባሱት ሲመጡ ሲሄዱ» ትልሃለች። የእነሱ መመላለስ ምንም ስሜት እንዳልሰጣት በዚህ ዘበት በሚመስል «ሲመጡ ሲሄዱ» በሚለው አገላለጿ እንረዳለን። ለነገሩ ከላይ ባሉት ስንኞች ቀድማ፦ "...በሰው ተከብቤ ሰው ያለ አይመስለኝም አንድም አጠገቤ" ብላ ተናግራው ነበር። ለመጣ ለሄደው ስላንተ ሳወራ ቀረት ቀረት አለ ሁሉም እየፈራ በጨዋታ መካከል በየጣልቃ ወሬ ትዝታህ ትዳሬ፣ ሞያ፣ ቁም ነገሬ ከቧት የነበሩትን ሰዎች ሁሉ እንደ ሰው ካለመቁጠሯ የተነሣ፣ እነሱ ለእሷ ያላቸውን ስሜት ለማሳየት ሲጣጣሩ እሷ ግን የምታወራቸው ስለ እሱ ነው። ለእነሱ ስሜት ግድ አይሰጣትም። የእሱ ስም ከአፏ የማይጠፋ መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ ትዝታው ለእሷ በእያንዳንዱ ወሬዋ መካከል ሊነሳ የሚችል የትዳርን ያህል ዋጋ ያለው፣ የሙያን ያህል «እዩልኝ፣ ቅመሱልኝ» የምትለው፣ የቁም ነገርን ያህል ሰው ሰብስባ የምታወራው ጉዳይ መሆኑን እያረጋገጠችልን ነው። ይህ በጣም ከባድ ነው! ለዚህ ነው ሁሉም እየፈራ «ቀረት ቀረት» የሚለው። በገዛ እጁ ዋጋ ቢስነቱን ለመስማት ማን እሷ ጋር ይሄዳል? «ቆሜ ቀረሁ ብሎ...» እያለ ሙዚቃው ያበቃል። ራስን ለመስዋዕትነት (ለዛውም ለማይመለስ ሰው) አሳልፎ መስጠት ማለት ይህንን ይመስላል። መስዋዕትነት ቆሞ እስከ መቅረት! ሙሉ የግጥሙ ማጠቃለያ፦ አንተ ልጅ አንተ ልጅ የፊቱ... የመጡት የሄዱት ባንተ እየተለኩ እንኳን ሊደርሱብህ ሰልፍህን አልነኩ ባል አግቢ ይሉኛል ወዴት ላድርገው የሰውነት አካሌን ብቻህን ወርሰኸው ቆሜ ቀረሁ ብሎ ልቤ መች ይባባል ሺህ ሰው ይመልሳል ትዝታህ ያጠግባል ላንተ ያልሆነ ገላ እንደ ቅጠል ይርገፍ ላንተ ያልሆነ ዕድሜ እንደ ጥላ ይለፍ አንተ ልጅ አንተ ልጅ የፊቱ... ደጄን ሞልቶ ተርፎ በሰው ተከብቤ ሰው ያለ አይመስለኝም አንድም አጠገቤ አስር ወዳጅ ይዤ አንድም ላይፈይዱ ፍቅርህን አባሱት ሲመጡ ሲሄዱ ለመጣ ለሄደው ስላንተ ሳወራ ቀረት ቀረት አለ ሁሉም እየፈራ በጨዋታ መካከል በየጣልቃ ወሬ ትዝታህ ትዳሬ፣ ሞያ፣ ቁም ነገሬ...

muluken Nigusse
muluken Nigusse
Open In TikTok:
Region: ET
Tuesday 08 September 2026 16:21:42 GMT
2016
66
3
9

Music

Download

Comments

bamlak.sharew
Bamlak Sharew :
በልጅነቷ ያጣናት ጠንካራና ትልቅ ቦታ የም ደርስ አርቲስት ነበረች
2026-09-13 15:36:30
1
nuradinmahamed359gmail.c
COMMANDO :
🥰🥰🥰🤩🤩🤩
2026-09-09 03:55:38
1
user1048628429910
ቀይ መብራት አትለፍ :
😳😳😳
2026-09-14 02:24:14
1
To see more videos from user @mulenigusse7, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About