@eyerusa27: +++ዮሴፍና ኒቆዲሞስ+++ "እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል" ማቴ 25:40 ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ክርስቶስን ገንዘው ቀበሩት:: በእርግጥ ፈጣሪን መገነዝ እንዴት ያለ ክብር ነው? ሙታንን የሚያስነሣቸው አምላክሞቶ ፣ ደካሞችን የሚያጸናቸው አምላክ ደክሞ ፣ነፍሱ ከሥጋው ተለይታ ሳለ መለኮት የተዋሐደውን ቅዱስ ሥጋውን መገነዝ እጅግ ታላቅ ክብር ነው፡፡ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ጌታን ሲገንዙ ምንኛ ይንቀጠቀጡ ይሆን? ቅዱስ ኤጲፋንዮስ እነዚህን ሁለት ሰዎች እንዲህ ሲል ይጠይቃቸዋል ፡- ‹‹ከእጃቸው በላይ ከፍ አድርገው የሚሸከሙት ኪሩቤል በፊቱ የሚንቀጠቀጡለትን እርሱን ስታዩ ታላቅ ፍርሃት አልፈራችሁ ይሆን? አምላካዊ ሰውነቱን ስትገልጡና በፍታ ልብስን ስታለብሱት በእንዴት ዓይነት ፍርሃት ነበር? ከተፈጥሮ በላይ የሆነውን አምላክሥጋውን ስትመለከቱ አልተጨነቃችሁምን? የአርማትያው ዮሴፍ ሆይ ንገረኝ! የምሥራቆች ሁሉ ምሥራቅ የሆነውን ጌታ እንዴት እንደ አይሁድ ልማድ ፊቱን ወደ ምሥራቅ አዙረህ ቀበርከው? በንጹሕ ጣቶቹ የዕውሩን ዓይን ያበራውን አምላክ ዓይኖቹን እንዴት በጣትህ ከደንሃቸው? የዲዳውን አንደበት የከፈተውን አምላክ አፉን እንዴት ገጠምከው? የሽባውን እጆች የፈወሰውን ጌታ እጆቹን እንዴት አብረህ አጣመርካቸው? የሽባውን እግሮች ያራመደውንስ ጌታ እንዴት እግሮቹን አሰርካቸው? ራሱን ባዶ ባደረገውና ዓለምን በቀደሰው በሰማያዊው ከርቤ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እንዴት ከርቤን አፈሰስህበት? ሁሉን [ከኃጢአት] ያጠበውን እና ያነጻውን አምላክስ እንዴት ሰውነቱን በውኃመሠረተ ያሬድ ሰ/ት/ቤት ዘአሣሣ 38 መብራት አበራችሁለት ይሆን? እያልኩ እደነቃለሁ፡፡ የመላእክት ሠራዊት ሁሉ የሚዘምሩለትን እርሱን እንዴት ያለ ዝማሬ እየዘመራችሁ ቀበራችሁት ይሆን?›› ወዳጄ ሆይ ፣ አንተ ይህንን ዕድል ብታገኝ ምን ታደርግ ነበር? ጌታችን በሞተባት በዚያች በዕለተ ዓርብ የክርስቶስን ሥጋውን የመገነዝ ዕድል ቢያጋጥምህ ትተህ ትሔዳለህ? ያለ ጥርጥርመልስህ ‹ይህንን ዕድል ባገኝማ የጌታዬን ቅዱስ ሥጋውን ገንዤ ፣ በከበረ ሽቱና ልብስ እሸፍነዋለሁ› ማለትህ አይቀርም፡፡ መልስህ ይኼ ከሆነ በል አሁኑኑ ተነሥና ከቤት ውጣ ፤ ክርስቶስ በጎዳና ላይ ወድቆ ዝናብና ፀሐይ ሲፈራረቅበት ታገኘዋለህ፡፡ ሔደህ ተመልከተው ፣ ሞቶም ከሆነ ገንዘህ ብትቀብረው የዮሴፍና የኒቆዲሞስን ክብር ታገኛለህ ፣ በሕይወት ካለም ዕርቃኑን ሸፍነህለት ፣ ረሃቡን አስታግሰህለት ትመጣለህ፡፡ ክርስቶስ <<እውነት እላችኋለሁ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳን ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት›› ብሏልና፡፡ (ማቴ. ፳፥፵) ይህን ያስተዋለው ቅዱስ መርቅያኖስ የተባለ ቅዱስ በሌሊት ቀባሪ ያጣ ደሃ ሞቶ ከሆነ ብሎ በጎዳና እየዞረ ‹ጌታዬን ልቅበረው› እያለ ይፈልግ ነበር፡፡ ባገኘ ጊዜም ትልቅ ሀብት እንዳገኘ ሰው ይደሰት በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
✞︎𝗠𝗮𝗵𝗹𝗲𝗧-𝗭-ኦርቶዶክስ⛪️☦️🛐
Region: AE
Sunday 13 September 2026 10:30:12 GMT
Music
Download
Comments
editor :
አሜን አሜን አሜን🥰🥰🥰
2026-09-29 06:44:03
2
user2339227107930 :
አሜን🙏አሜን🙏አሜን🙏አሜን🙏አሜንንንን🙏🙏🙏🙏🙏
2026-09-28 08:37:00
4
ድክም ያለሒወት :
አሜንንንን
2026-09-28 06:38:06
2
ወዲ ለምለም ሓሸንገ🌹🌾🌽 :
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-09-27 21:15:07
1
user7952352049521 :
dngl marym tahaliki🙏🙏
2026-09-13 12:49:09
1
Abbee :
🙏🙏🙏🙏
2026-09-29 08:19:53
0
አሳድ ራያ :
🥰🥰🥰🥰
2026-09-27 09:14:11
1
birtukan :
@አሜን🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-09-16 08:42:31
1
ታዴ man :
አሜን
2026-09-29 03:46:42
0
Alex Gezahagn :
🥰
2026-09-13 12:35:35
1
የማረያም ልጅ(ደንግል እናቴ አትለይኝ) :
አሜን
2026-09-28 10:39:40
1
272112 :
🙏🙏
2026-09-13 17:19:52
1
Beti ❤️🩹🌹 :
2026-09-13 18:31:35
1
fanuu.arsii.waan.ofii :
🙏🙏🙏
2026-09-16 08:09:35
1
user2339227107930 :
አሜን🙏አሜን🙏አሜን🙏አሜን🙏አሜንንንን🙏🙏🙏🙏🙏
2026-09-28 08:37:56
1
ሚካኤል አባቴ ቅደም ከፊቴ 12🛐⛪️☦️ :
2026-09-28 18:12:24
1
geni yemaryam lji⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️ :
🙏🙏🙏
2026-09-28 18:35:26
1
☘️⓰ኪዳነ ምህረት የመኖሬ ምክንያት ናት⓰🕊 :
🙏🙏🙏🙏
2026-09-29 02:41:34
0
F.G :
2026-09-29 07:55:10
0
Mesel Besfat :
kale hiwot yasmalen🙏🙏🙏
2026-09-27 17:35:43
0
To see more videos from user @eyerusa27, please go to the Tikwm
homepage.