@cu.uoo:

ابراهيم عباس
ابراهيم عباس
Open In TikTok:
Region: IQ
Monday 14 September 2026 13:03:22 GMT
13
5
0
0

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @cu.uoo, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

እቴጌ 🥹💛 ✍️ንጉሱን በዙፋኑ ያደላደለው ከ21 አመት በፊት በዕለተ ሰኑይ (ሰኞ) ግንቦት 1/1997 ዓ.ም በኤሌክትራ የሙዚቃ አሳታሚ ድርጅት በኩል ገበያ ላይ የዋለው የቴዲ አፍሮ
እቴጌ 🥹💛 ✍️ንጉሱን በዙፋኑ ያደላደለው ከ21 አመት በፊት በዕለተ ሰኑይ (ሰኞ) ግንቦት 1/1997 ዓ.ም በኤሌክትራ የሙዚቃ አሳታሚ ድርጅት በኩል ገበያ ላይ የዋለው የቴዲ አፍሮ "ያስተሰርያል" አልበም በገበያ ላይ በዋለበት ወቅት ኃይለኛ የፖለቲካ ጡዘት ነግሶ የነበረበት ሰሞን ከመሆኑ ጋ ተያይዞ በወቅቱ ቤተ መንግስት ድረስ የደረሰ ቅሬታን ፈጥሮ የነበረ ሲሆን መንግስት ነገሩን ያየው ሆን ተብሎ አመጽ ለማስነሳት ታቅዶ እንደሆነና በነበረበት ፖለቲካዊ ውጥረት ላይ ሌላ ጥቃት እንደተፈጸመበት ነበር። በዚህም መንግስት በግልጽ አቂሞ ነበር። ለዚህም ጀብደኛው ቴዲ አፍሮ ዋጋ ከፍሎበታል 21 አመታትን ያስቆጠረው ጀብድ (ያስተሰርያል) አልበም በክቡር ደ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን🙌🥰 ✨ውድ ቤተሰቦቼ ቴዲ አፍሮ የአልበሙ እና የምርጫው መገጣጠም የሱ እቅድ እንዳልሆነ ይናገራል ። ምክኒያቱም አልበሙን ሊለቅ ያሰበበት ወቅት ቀድሞ የተቆረጠ ነበር። ይሄንንም ሲገልጽ ምርጫው ወደ አልበሙ ተጠጋ እንጂ አልበሙ ወደ ምርጫው ሰሞን አልተጠጋም ብሎ ነበር (ቃል በቃል የተወሰደ አይደለም) ደግሞም ሁሉንም ፖለቲከኞች ማመን ደግ እንዳይደለ ገብቶታልና የሁሉንም የምረጡኝ ቅስቀሳና ለሀገሬ ለወገኔ ይሄን አደርጋለሁ የሚለውን ቃላቸውን ከሰማ በኋላ ወደ አንዳቸውም ሳይወግን ይሄም በክፉ ቃል ይሄንን ሲወቅሰው፣ ይሄም በጥላቻ ይሄንን ሲወቅሰው፣ መለየት አቃተን የሚበጀንን ሰው” ሲል አዜመ። ሌላው ይህን አልበም ሰኞ የለቀቀበት የራሱ የሆነ ምክኒያት አለው። ሰኑይ ማለት ለፍጥረታት 2ኛ ቀን ማለት ነው። “ያስተሰርያል” አልበም ደሞ ቴዲ አፍሮ በፍቃዱ ከለቀቃቸው አልበሞች ውስጥ ሁለተኛው አልበም ነው። 1ኛው አቢጉዳ 2ኛው ያስተሰርያል። ሌቦ የተሰኘው አልበም አቦጊዳ አልበም ከመለቀቁ ከአመት በፊት ተገዝቶ ግን ለገበያ ሳይውል የተቀመጠ አልበም ነው። እሱም ደጋግሞ ልቀቁልኝ ቢላቸውም እነሱ አንዴ ገዝተንሃል ስንፈልግ እንለቃለን ካልፈለግን አንለቅም ነበር ያሉት። ከዛም አቦጊዳ የተሰኘውን አልበም ሲለቅ ያለውን ተቀባይነት አይተው ሌቦ የተሰኘውን አልበም ደርበው ለቀቁት። በዚህም ቴዲ አፍሮ ተበሳጭቶ ነበር። በአልበም ደረጃ ከሌቦ ይልቅ አቦጊዳ አልበም በጣም ከፍ ያለና ትልቅ የሙዚቃ ነውጥ ያመጣ አልበም ነበር። ቴዲ አፍሮ የሚለው ስም ከሙያ ባልደረቦቹ አልፎ የኢትዮጵያ ህዝብ የሰማው በአቦጊዳ አልበም ነበር። ታዲያ ይህ ተወዳጅ ብላቴና በያስተሰርያል አልበም ጥርስ ተነክሶበት ለዘመናት ዋጋ ከፍሏል። በወቅቱ የታፈነ የወገኑን ጩኸት ነበር የጮኸው። ከፖለቲከኞቹ በእድሜም በፖለቲካ እውቀትም ያነሰ ቢሆንም በጥበብ ግን ልቆ ነበርና ትንሹ ልጅ ሀገራችንን አደራ ሲል አዛውንቶቹን ተማጸነ። እውነት እንደምትሉት ከወደዳችሁን ልዩነታችሁን አጥብቡና እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ ያኔ እኛን እንደምትወዱን እናውቃለን ሲል ተማጸነ። 📌እንዲህ ሲልም በአልበሙ ጀርባ ይሄን ፅሁፍ አጋራ ታላቁ ጩኽት !!! ግንቦት 1/1997 ዓ.ም የኢያሪኮ ከተማ በጩኸት ፈረሰች ። አሁን ጩኸት በኢትዮጵያ አለች ። ጩኸት ክፋት፣ ጩኸት ቂም በቀል ፣ ጩኸት ግብዝነት እና ያለመግባባት ዝምታ ሁና በእርግጥ በዚህ አለች። ይህችም ጩኸት በራስ የተመካች በአዕምሮ የሆነች እና ፍሬዋም የመረረ ባዶ ናትና ባዶ እንዳታስቀረን ስል ፈራሁ ። ታላቁን ጩኸት ታናሹ እኔ እንዳልጮህ ደግሞ የማውቀዉ ራሴን ፈራሁት (ሃይጢያተኛ ነኝና) የማውቀው ራሴንም ለሚያውቃት አባቴ አሳሰብኩት ለመንኩትም ሰማኝ ። አሁን ሰዎች እንዲሰሙኝ እጮኻለሁ እለምናለሁ እንግዲ ስትሰሙኝ በማስተዋል ሁኑ ፤ ማስተዋላችሁም በቅን መንፈስ እንጂ በአዕምሮ ና በዕውቀት እንዳይሆን ተጠበቁ ። በቅን መንፈስ ውሰጥ ያለን ብርሃን እና ለእኛ መሬት የተፈቀደውን እውነተኛ የመዳኛ መንገድ በዕውቀት የተመኩ ኢትዮጵያዊያን እንዳያዩት ሆኗልና ። ስለዚህ በጨለማ የነበሩ ሰዎች ብርሃን ያዩ ዘንድ በቅን ልቦና ሆነን የምህረት አይኖቻችንን እንክፈት እንንቃ ያኔም መዳን ይሆንልናል ። መዳን እንዲሆነን ቃልኪዳን አለን ። ቃልኪዳኒቱም የዕርሱ ዕርሱም ቅዱስ ፈጣሪያችን ነው አሜን!!! የተማረ እንጂ የተባረከ መሪ ከለመንን ቆይተናል። የተማረ ከተገኘ በጣም ጥሩ ነው የተባረከ ይሁን እንጂ ። የተባረከ መሪ ከተገኘ ግን በጣም ጥሩ ነው ባይማርም እንኳን ። ብልህ ሰው ታናሹንም ይሰማል ፤ ጃ ያስተሰርያል! ቴዎድሮስ ካሳሁን ( ቴዲ አፍሮ )👌 ዛሬም ድረስ ይህ አልበም በሀገራችን ከተሰሩ ዘመን አይሽሬ አልበሞች ውስጥ ከምርጦቹ የሚሰለፍ አልበም ነው። ይህ አልበም የቴዲ አፍሮን ችሎታ የገለጸ ብቻ ሳይሆን ቴዲ አፍሮ ዘለዓለማዊ የኪነጥበብ ዘውድ ደፊ መሆኑን ያጸና አልበም ነው። በአቦጊዳ አልበም በሰው ልብ ውስጥ ሰርስሮ የገባው ብላቴና በያስተሰርያል አልበም መኖሪያውን አጸና። እነሆ 20 አመታት ተቆጥረውም እንደ ትላንት የተለቀቀ እስኪመስል ትውስታው ቅርባችን ነው። 🙏 ዛሬም ታዲያ እኔም ከዚህ አልበም ላይ ነፍሱ ይማረውና ሁሌም በምንቆጭበት ታላቁ ኤልያስ መልካ😥 የተበጀውን እጅግ ተወዳጁን "እቴጌ"ን ለትውስታ ጋብዤያቹ አበቃው 🗣️ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🫡 Musictube #fyp #ቴዲአፍሮ #እቴጌ #musictube369 #ethiopianmusic

About