@twoleftshoesclub: #madecaderma #madeca #fyppppppppppppppppppppppp #bestfriend #bestproduct

TwoLeftShoesClubA.I.
TwoLeftShoesClubA.I.
Open In TikTok:
Region: US
Tuesday 15 September 2026 04:18:37 GMT
18
7
0
0

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @twoleftshoesclub, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

ለቅድስት አርሴማ የተሰጣት ቃል ኪዳን (በአማርኛና በልሳነ እንግሊዝ) 👉“ነገር ግን ርቃችሁ አትሂዱ፥ ጸልዩልኝ አለ” ዘጸ. 8፥28  👉
ለቅድስት አርሴማ የተሰጣት ቃል ኪዳን (በአማርኛና በልሳነ እንግሊዝ) 👉“ነገር ግን ርቃችሁ አትሂዱ፥ ጸልዩልኝ አለ” ዘጸ. 8፥28 👉"አሁንም የሰማይ ቅዱሳን ሆይ፥ የሰዎች ነፍሳት ፍርድን ወደ እግዚአብሔር አግቡልን እያሉ እናንተን ይማጠናሉ።" መጽ. ሄኖ. 2፥30 "ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር ቃል፣ ቡርክትና ብፅዕት ቅድስት አርሴማን በመላእክቶቼ ሁሉ ፊት፣ በእናቴም በማርያም፣ በነቢያትና በሐዋርያት፣ በጻድቃንና በሰማዕታት፣ ዳግመኛም በተመረጡና ንጹሐን በሆኑ ደናግልና መነኮሳት ፊት ከአፌ የወጣውን እንዳልዋሽ ማልኩልሽ አላት። ቤትሽን (ቤተ ክርስቲያንሽን) የሠራውን፣ ወይም መታሰቢያሽን ያደረገውን፣ ስምሽን የጠራውን፣ ወይም የተራበውን በበዓልሽ ቀን ያጠገበ፣ የተጠማውን ያጠጣ፣ ወይም የተራቆተውን ያለበሰ፣ ወይም ከንቱ ከሆነ ምስጋና ሥጋውን በማራቅ በፍርሀትና በመንቀጥቀጥ በበዓልሽ ቀን የዘመረውንና ያመሰገነውን፣ በገድልሽ ታምኖ [ከማዩ] የጠጣውንና የታጠበውን፣ ወይም በመንገድሽ ድካም ይህንን ዓለም የናቀውን፣ እኔም የልቡን ምኞት እፈጽምለታለሁ ያለ ጉስቁልና በንጽሕና ድንግልናውን እጠብቅለታለሁ በመንግስተ ሰማያትም እንደ አንቺ የክብር አክሊልን እሰጠዋለሁ። ስዕልሽን አስሎ በቤትሽ ውስጥ ቢያስቀምጥ፣ ወይም በክብርና በንጽሕና በቤቱ ቢያስቀምጥ፣ ወይም [በስዕልሽ ፊት] የሰገደና የተማለደ፣ ወይም በላዩ መልካም የሆነ የናርዱ ሽቱ የረጨ፣ እኔ ልብን የሚመስጥ ጣፋጭ ከሆነ ከገነት መዓዛ አሸተዋለሁ። ወንድ ልጁንና ሴት ልጁን በአንቺ ስም የጠራውን፣ በመንግስተ ሰማያት የበለጠና የከበረ ስምን እኔ እሰጠዋለሁ። ዕጣንንና ቁርባንን [ቢያገባ/ቢሰጥ] ወይም መብራትን ቢያበራ፣ እኔ በሰማያት መብራትን አበራለታለሁ። ለቤተ ክርስቲያን ልብስን ወይም መጋረጃን ቢሰጥ፤ እኔ በሞቱ ቀን የብርሃን ልብስን አለብሰዋለሁ። እንደ መላእክት ክንፎች ከጎኖቹ አበቅልለታለሁ። ያለ ጭንቅ የእሳት ባህርን ይሻገራል። እንደ ወፍም ይበራል። የገድልሽን መጽሐፍ በእምነትና በጥንቃቄ ቢጽፍና ቢያጽፍ፣ ወይም በምድር ካለው ሀብት ይልቅ በገንዘቡ የገዛውን፣ የጽድቅ ብርሃን በሆነ ዓምድ በወርቅ ቀለም ከስምሽ ጋር ስሙን እኔ እጽፋለሁ አላት። ጌታችን ቡርክት አርሴማን ከመጀመሪያ እስከ ኋላ ያሰብናቸው ሁሉ በመንግስተ ሰማያት በግልጽ ይለፉ አላት። ቡርክት ቅድስት አርሴማም አሜን አለች።" +++አሜን+++ ሰላም ለጸአተ ነፍስኪ በጊዜ ኃላፊት ሰይፍ መንገለ ክሳድኪ ጽኑን ለአምሳለ መስዋዕት ውኩፍ እስእለኪ አርሴማ በከናፍር ወአፍ ረድኤትኪ ትሩፍ ላዕሌየ ያንጸፍጽፍ እስመ አርእየኒ ዘንተ ሞትኪ ትሩፍ። 👉“ነገር ግን ርቃችሁ አትሂዱ፥ ጸልዩልኝ አለ” ዘጸ. 8፥28 👉“እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን” ዕብ. 12፥1 👉“ዋጋዬን እስክትሰጠኝ ድረስ ጻድቃን እኔን ይጠብቃሉ” መዝ. 141 (142)፥7 👉“የጻድቃንን ማደሪያቸውንና የቅዱሳንን ማረፊያቸውን አየሁ። በዚያም ዐይኖቼ ከመላእክት ጋራ ማደሪያቸውን፥ ከቅዱሳንም ጋር ማረፊያቸውን አዩ። ስለ ሰው ልጆች ይለምናሉ፥ ይማልዳሉ፥ ይጸልያሉም።” መጽሐፈ ሄኖክ 9፥21-23 👉“በመንፈስ ነበርሁ . . . በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ . . . ሰማሁ” ራእይ 4፥2-5፥13 👉"አሁንም የሰማይ ቅዱሳን ሆይ፥ የሰዎች ነፍሳት ፍርድን ወደ እግዚአብሔር አግቡልን እያሉ እናንተን ይማጠናሉ።" መጽ. ሄኖ. 2፥30

About