@imaging_gurus: የብዙ ወንዶች ድክመት የሚታየው ስለ ሴቶች ባላቸው አመለካከት ላይ ነው። ልክ እንደ ትልቅ ኃይል፣ በስሜት ላይ የምታሴር፣ ወደእኛ የምትመጣው ህይወታችንን ለመበጥበጥ ነው ብለው ያስባሉ። ይህ ለአንተ ለወንዱ በስነ-ልቦና ደረጃ ምቹ ግዜያዊ ዶፓሚን ፈጥሮልሃል። ምክንያቱም ውስጥህ የተፈጠረውን ብጥብጥ ከመቀበል ይልቅ ይህን በሴት አሳቦ እና ምሳሌ አድርጎ ማለፍ ቀላል አድቫንቴጅግ ነው። ነገር ግን እውነቱን እናውራ ከተባለ ሴት ምንም ያደረገችህ ነገር የለም፤ ከእሷ የሚጠበቀው አንተ በትኩረት ማየት ብቻ ነው። ከዛ በጥቂት ደቂቃዎች የደፈንከው ጉርጓድ መሰነጣጠቅ ይጀምራል። እስቲ አስተውል ሁልጊዜ ማረጋገጫ የሚፈልግ ወንድ፣ ሁልጊዜ እንዲደነቅ የሚፈልግ እና ሁልግዜ ተፈላጊነት እንዲሰማው የሚፈልግ ወንድ የሴት ሰለባ ብቻ አይደለም፤ የውስጡ ባዶነት ባርያም ጨምር ነው። ሴት ይህን ፈጣን ስሜት ትረዳዋለች። ምናልባት ድክመትን የማሽተት የቆየ ተፈጥሯዊ ችሎታ ስላላት ይሆናል፤ ሴቶች የመሬት መንቀጥቀጥን ከመከሰቱ በፊት እንስሳት አስቀድመው እንደሚታወቃቸው ያህል የወንድ ስሜት መናወጥን የፈጠነ የማወቅ ድንቅ ችሎታ አላቸው። ለዛም ነው አንዳንድ ስድብ ካስተናገዱ በላይ ዝም የተባሉት ወንዶች ቀድመው የሚፈርሱት። ምክንያቱም የሞከሯት ሴት ላይ መልሱ ዝምታ ከሆነ መጨረሻው የራሳቸውን ውስጥ እንዲሰሙ ያስገድዳቸዋል። ውስጣቸውም በፍላጎት ጥማዓት ተቃጥሎ እርካታ ያጣ ድምፅ ይሆናል!። ብዙ ግዜ እገረማለሁ አዝናለሁም ጭምር። ለምን መሰላችሁ አንድ ወንድ ምርጫውን፣ ፐርሰናሊቲውን፣ የፖለቲካ አመለካከቱን ብቻ ሳይሆን ትንንሽ ልምዶቹን በጠቅላላ ወዲያው ሲቀይር ማየት፤ ይህ ሁሉ ለውጥ ሌላ ሰው ለመሆን ከማሰብ ሳይሆን በአንዲት ሴት ተቀባይነት ለማግኘት የሄደበት እርቀት ነው። ሲጋራ ማጨሱን ያቆማል፣ ከሚገባው በላይ ፈገግ ይላል፣ የተባለውን ሁሉ ይስማማል። እንዲህ ያለ ወንድ ሰላም ባለው ግንኙነት ውስጥ የመቆየት አድቫንቴጁ አጭር ነው፤ ከዛ በተለየ ወደ አሳዛኝ የስሜት ዲፕሎማሲ ውስጥ ይገባል። ቀን በቀን በሞላ ጎደል «ትተወኛለች» በሚል ፍርሃት ውስጥ ይናወጣል። ምክንያቱም ከመጀመርያውም ይሄ ወንድ ችግሩ እሷ አልነበረችም። ችግሩ እሱ እና እሱ ብቻ ነው!። ደህንነት የምናገኘው ከሴት ጋር ስለሆንን አይደለም፤ እሷ በሌለች ጊዜ የማንፈርስበት ማንነትን በመገንባት ውስጥ ነው። ለዚህ ነው የሶቅራጥስ አስቸጋሪ ማንነት የሚያስደንቀኝ። ሀብቱን፣ ቤተሰቡን፣ እራሱንና ሁሉንም ነገር ሊያጣ አንድ ደቂቃ ቀርቶት በሃሳቡ፣ በማንነቱ የፀና እና የማይደራደር ፈላስፋ ነው። ማህበረሰቡ በጠቅላላ እንዲገደል ተስማምተውበታል፤ ነገር ግን እሱ ከአንድ ነገር ብቻውን ቆሟል። ከጽናት ጋር። ሴቶች ሁሌም በእንዲህ አይነት ወንድ ይማረካሉ። ይህ የሆነበት ምክንያት ለስላሳ ወይም ሮማንቲክ ስለሆኑ አይደለም፤ ጽኑና ቆራጥ ስለሆኑ ነው። ሴት ብዙ ግዜ ወንድን የመፈተን ባህሪያዊ ባህል አላት። ይህ ግን የሶሻል ሚድያ ሞኝ ወንዶች እንደሚያስቡት ከክፋት የመነጨ አይደለም፤ ይልቁንስ «ጠንካራ መሬት ላይ ነኝ ወይስ በጭቃ ረግረግ ነው የቆምኩት?» ብላ ማጣራት ስለምትወድ ነው። ብዙ ግዜ ወንዶች ከመጀመሪያው የፍቅር ግጭት በኋላ ይፈራርሳሉ። ያኔ ላለፈችው እና ለምትመጣው ሴት ጭምር ክብር መስጠት ያቆማሉ። ይህ የሚሆነው ካለማስተዋል ነው። ከውጭ ለመጣ ግፊት በውስጣዊ ስሜት የሚፈጠርበት ግጭት ትክክለኛውን ውሳኔን ያሳጣል። ሴት ሰውነቱ ጡንቻማ የሆነ ወንድ ሳይሆን እራሱን የሚሸከም ወንድ ነው የምትፈልገው። ለዛም ነው ቆንጆ ቃላት እየመረጥክ ብትጠቀም እራሱ ጥቅም የሌለው። ውድ እራት፣ የፍቅር መልዕክቶች፣ ቃል ኪዳኖችን ጨምሮ ሁሉም የሳይኮ ግዜያዊ ሜካፖች ናቸው። ይህ ሁሉ ብታደርግ ከሴቷ የሚተርፍህ እነዚህ ጥያቄዎች ብቻ ናቸው፦ «ብርቀው ይጎዳል?» «ዝም ብለው ይጨንቀዋል?» «ያለኔ እኮ ህይወቱ ባዶ ናት?» ጤናማ ግንኙነት ማለት እነዛ የሀዘን ዘፈኖች እንደሚሉት በሌላው ውስጥ ቀልጦ ማለቅ አይደለም። ያ በፍቅር ስም የተሰየመ ራስን የማጥፋት ስትራቴጂክ ነው። ብዙዎቸ እንዲህ አይነቱን «ፍቅር» ብለው ይጠሩታል። «ጥገኝነት» ብለው ለመጥራት ግን ድፍረት የላቸውም። ይህን የምታደርግ ከሆነ ሴት አስፈሪ መስታወትህ ሆና ትቀራለች። አስፈሪነቷ አንተን ስላፈረሰችህ አይደለም፤ ምናልባት ለመጀመሪያ ጊዜ «እኔ እኮ ይህ ነኝ» ብለህ የምትጠራውን በፍርሃት እና በተቀባይነት ጥማት የተገነባ ደካማ ማንነትህን አንጸባርቃ ስላሳየችህ ነው!። አዲዮስ..🤙 #weakness #weakmen #alpha #sigma #viral #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #habeshatiktok
ሞገስ ዘአምድ Gυrυ🪽
Region: ET
Wednesday 16 September 2026 13:53:21 GMT
Music
Download
Comments
Iamme :
mejemeriya FB never yemawukh ahun be TT memtath desblognal
2026-09-20 13:02:05
2
calafiori :
negeru new alu
2026-10-06 03:50:59
0
ሁሉንም ነገር ለገብርኤል አባቴ ትቸዋለሁ :
🙏🙏🙏
2026-10-04 18:41:00
1
To see more videos from user @imaging_gurus, please go to the Tikwm
homepage.