@worshipzonenews: በኤርትራ ጨለማ እስር ቤት የተረሳችው ሲሃም!🥹💔 የአስራ አምስት ዓመት ታዳጊ እያለች የነፃነት አየሯን የተነጠቀችው ፤ ዛሬ የ29 ዓመት ወጣት ሆናለች ፤ ሲሃም አሊ አብዱ። ሲሃም አሊ ፤ ላለፉት 14 አሰቃቂ ዓመታት ያለ ምንም የፍርድ ቤት ክስ፣ በወንጀል ሳትጠየቅ፣ እና የት እንዳለች እንኳ በውል ሳይታወቅ በለጋ እድሜዋ በእስር እየማቀቀ ትገኛለች ። የዚህች አሜሪካዊ ዜግነት ያላት ንፁህ ታዳጊ ወንጀል አንድ እና አንድ ብቻ ነበር፤ የኤርትራ ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩት አባቷ ከፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር በፈጠሩት የፖለቲካ ፀብ የቂም ሰለባ መሆኗ። አቶ አሊ አብዱ የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር እና የፕሬዚዳንቱ ቀኝ እጅ ነበሩ። ከትጥቅ ትግሉ ዘመን አንስቶ አብረው የዘለቁት አቶ አሊ፣ ምናልባትም ቀጣዩ የሃገሪቱ መሪ ሊሆኑ እንደሚችሉ በብዙዎች ዘንድ ይገመት ነበር። ነገር ግን፣ ሁሉም ነገር በአንድ አሳዛኝ ቅፅበት ተቀለበሰ። የጥል መንስኤው የዓለምን ትኩረት የሳበው ያ ታዋቂ የአልጀዚራ ቃለ-መጠይቅ ነበር። ጋዜጠኛዋ ፕሬዚዳንት ኢሳይያስን "አምባገነን ነዎት፤ አካባቢውን በሁከት እያመሱ ነው" ብላ ፊት ለፊት ስትሞግታቸው፣ ፕሬዚዳንቱ የደም ስሮቻቸው እስኪገተሩ እና ላባቸው እስኪጠምቅ ድረስ በንዴት ጦፉ። በካሜራ ፊት የታየው ይሄው አሳፋሪ ስሜታዊነት፣ በመሪው ልብ ውስጥ መርዝ ፀነሰ። ቃለ-መጠይቁ እንደተጠናቀቀም፣ ፕሬዚዳንቱ ሚኒስትራቸውን አሊ አብዱን አስጠርተው ቪዲዮው እንዳይተላለፍ ጥብቅ ትዕዛዝ ሰጡ። ሚኒስትሩ "ይህ የዓለም አቀፍ ሚዲያ ጉዳይ በመሆኑ ከእኛ አቅም ውጪ ነው" የሚል እውነታ ሲያስረዱ፣ ፕሬዚዳንቱ በቁጣ ገነፈሉ፤ ሚኒስትራቸውንም በቦክስ እና በርግጫ ደበደቡ። ከዚህች እጣ ፈንታ ቀያሪ ቀን በኋላ፣ አሊ አብዱ የፕሬዚዳንቱን በቀለኛነት ጠንቅቀው ስለሚያውቁ አገር ጥለው ለመሰደድ ወሰኑ። ለስራ ወደ ጀርመን በተጓዙበት አጋጣሚ ስርዓቱን ከድተው ወደ አውስትራሊያ ኮበለሉ። ይህ ውሳኔያቸው ግን በአስመራ ለቀረችው የ15 ዓመቷ ልጃቸው የሲኦል በር ከፋች ሆነ። አባቷ ልጃቸውን ለማትረፍ በሚል 7,000 ዶላር ከፍለው በህገ-ወጥ መንገድ በሱዳን በኩል እንድትወጣ ለማድረግ ቢሞክሩም፣ ሲሃም የሱዳንን ድንበር ልትረግጥ ጥቂት ሲቀራት በኤርትራ የደህንነት ኃይሎች እጅ ወደቀች። ከዚያች ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬዋ ሰዓት ድረስ፣ ሲሃም ያለችበት ቦታ በእርግጠኝነት አይታወቅም። ነገር ግን የተለያዩ የመብት ተሟጋቾች መረጃ እንደሚያሳየው፣ ይህቺ ምስኪን ወጣት የተጣለችው 'ኤራ ኤሮ' በተባለው፣ በበረሃ ውስጥ በሚገኝ እና ከሰው እይታ በተሰወረ የምድር ስር የኮንቴነር እስር ቤት ውስጥ ነው። ይህ ስፍራ የቀድሞ ከፍተኛ ባለስልጣናት ያለ ፀሐይ ብርሃን በስቃይ ህይወታቸው ያለፈበት የምድር ላይ ሲኦል ነው። የአባቷን የፖለቲካ ሸክም እንድትሸከም የተፈረደባት ሲሃም፣ የልጅነት ህልሟ፣ የወጣትነት ብሩህ ተስፋዋ፣ እና ነፃነቷ ሙሉ በሙሉ ተነጥቋል። ዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋቾች ድምፃቸውን ቢያሰሙም፣ የኤርትራ መንግስት ዛሬም ድረስ ስለ እርሷ ህያውነት ትንፍሽ አላለም። የ15 ዓመቷ ህፃን፣ አሁንም በጨለማ ውስጥ የፍትህ ደወል የሚደወልበትን ቀን እየጠበቀች ትገኛለች።😭

Worship Zone💎
Worship Zone💎
Open In TikTok:
Region: ET
Wednesday 16 September 2026 15:48:46 GMT
233536
9571
173
956

Music

Download

Comments

follow_807
follow :
ማዳን የሚያውቅበት ጌታ ከዕሷ ጋር ይሁን😭
2026-09-16 18:28:09
530
user7556799391006
ኢየሱስ ጌታ ነው። :
በህይወት ግን አለች
2026-09-16 17:01:41
172
izzycase48
izzycase48 :
የ ኢሳያስ ክፋት አልታየኝም አባቷ እራሱን ይወዳል ተመልሶ እጁን ሰቶ ልጁን ማስለቀቅ ይችል ነበር
2026-09-17 05:26:06
27
joshwa.boss
Joshua የኢየሱሴ ባሪያ :
ለኔ ለበደለኛው የደረሰልኝ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዚች ምስኪን እህቴ ይድረስላት ጌታ ሆይ ስለምትደርስላት አመሰግንሀለው
2026-09-16 19:38:29
181
ayutii2716
ayuti@27 :
beyesus sam geta hoyii derselate justice for our sister siham 🥺🥺
2026-09-16 17:36:59
63
abenenezererketo
abenezer erketo :
ፈጣሪ ይድረስልሽ
2026-09-16 16:49:24
52
samri_jesus
ሰሚራ የኢየሱስ 🥰 :
ጌታ ይድረስላት 😥
2026-09-16 17:47:35
28
t_girma
ᴛ♬⋆ :
አምላኬ ሆይ የዚች ብላቴና ስቃይ ተመልከት በቃ በላት እባክህ አምላኬ | የምር ዕንባ ተናነቀኝ 😣☹️😢
2026-09-16 18:23:55
30
user1345328590524
user1345328590524 :
justice for Siham
2026-09-17 05:12:06
14
yitagesdemissew
Yitages Demissew :
betam mtasazneg lij be ewnet justice for siham 😢😞
2026-09-16 17:36:10
13
asmamawassa
Asmamaw Assa :
በሕይወት ካለች በሁኔታዎች ሁሉ የማይገደብ ኢየሱስ ክርስቶስ ለነፍስ ለሥጋዋ ይድረስላት።
2026-09-16 17:57:16
30
mesfin.kebede212
Mesfin Kebede :
ጌታ እንደነጳውሎስ እስር ቤት ገብቶ እንዳስፈታት አሁን ግን በውስጧ ያለው ጌታ አብሮአት ነው ያለው እስከአለም ፍፃሜ ድረስ ከእናንተ ጋር ነኝ ያለው ጌታ የታመነ ነው
2026-09-16 17:56:54
20
dayenu1993
Dayenu (דַּיֵּנוּ) :
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነፃ ያውጣት🙏
2026-09-16 18:47:48
14
zuriashwerk
werka dase zdb1 :
ጌታ ይድረስልሽ
2026-09-16 20:46:15
13
sibabu51
ሓየት ፃዕዳ(ሰበቡ)💊💊💊🇪🇹 :
ታዲያ ምን እንጠብቃለን ለምን ከእግዚአብሔር ጋራ አንረዳትም ?????
2026-09-16 18:42:23
11
kasira706
kasira :
ፈጣር ይድረስላት🥺
2026-09-16 17:38:22
11
hana378760
hana :
ዉስጤ በጣም ተረበሽ ማርያምን😭😭
2026-09-17 14:55:53
7
abigu232
Abigu D :
abatuan asebkut bekumu skay wst new esum ay echi mdr😭
2026-09-17 02:26:43
5
amin_kono
king :
campaign yikefet yemitilu #free_siham
2026-09-16 16:59:36
7
elsabirru
Elsabirru :
እግዚሃብሄርን ታምኖ ማንም አያፍርም ጳውሎስን ሰንሰለት ፈትቶ ያወጣቸው አምላክ ይረዳታል መሞቷን ጠላት ሲጠብቅ እግዚሃብሄር ደሞ ሞቷን ሽሮ ያወጣታል
2026-09-16 18:57:56
7
yonatan20257
nathan 2025✝️ :
ይሔ ዘገባ ከዚህ አካውንት ጋር ምን ያገናኘዋል 🤔
2026-09-16 17:47:00
5
hela744
hela blessed :
ጌታ እየሱስ ይድረስላት so sad 🙏🙏🙏
2026-09-16 18:31:58
6
user385addisalem
addisalem :
justice for sihame🥺🥺🥺🥺😭😭😭😭
2026-09-17 15:28:23
7
ethiorica_1
✥ ዳስ ጣል ✥ 🫀꧁ አ .ን . ሳ .ው꧂ :
🌍 የመሪዎች አፀያፊ ነውር ከሰው አልፎ ለትውልድ ይተላለፋልና እናስተውል የሰው እምባ ማረፊያ እንዳንሆን ማስተዋልን ያድለን! ⚠️በኢትዮጵያም ሆነ በዓለም ላይ "የአባት እዳ ለልጅ" እየተባለ እንደ ሲሃም አሊ አብዱ ያሉ ንጹሃን በበቀልና በፖለቲካ ሴራ በጨለማ ወህኒ ሲማቅቁ ማየት ታላቅ ነውር ነው። ዛሬ ዓለም ሁሉ ሰላምን ይናፍቃል፤ ሰላም ማለት ደግሞ የንጹሃን መብትና ነጻነት መከበር ጭምር ነው። ✨ "ታስሬ ጠየቃችሁኝ" ያለው ጌታ በእስር ላይ ካሉ ንጹሃን ሁሉ ጋር እንዳለ እናምናለን! 🙏 የታሰሩትን የምትፈታ እውነተኛው ፈራጅ ጌታ ሆይ! ⚖️ያለ ጥፋታቸው በሰው እዳ በጨለማ ወህኒ የሚማቅቁትን ምስኪን ነፍሳት በምህረትህ አስባቸው። በዚያ እስር ቤት ውስጥ ሳሉ መልካም አድርገህ ስራቸው፣ ጠብቃቸውም! 🛡️ስጋቸው በሰው ሰንሰለት ቢታሰርም⛓️፣ ነፍሳቸውን ግን በአንተ መለኮታዊ እጅ አኑረው፤ ጥበቃህም እንደ እሳት ቅጥር ይሁንላቸው። 🔥 በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና 🌹 በቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት፤ ⚔️የክርስቶስ ተስፋና እውነተኛ ነጻነት ፈጥኖ ይድረስላቸው! 🔑✨ #FreeCiham #JusticeForInnocent #ኢትዮጵያ #ሰላም_ለሀገራችን #ፍትህ_ለንጹሃን #ኦርቶዶክስ #fyp #viral
2026-09-17 03:50:52
6
tareg0729
𝚃𝚊𝚛𝚎 𝙹. 🙏🥰🥰 :
ነፃ የምትወጣበት ቀን እሩቅ አይደለም
2026-09-17 14:33:54
3
To see more videos from user @worshipzonenews, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About