@yayaye917: #ሐሙስ_መንኩሳ_ቅዳሜ_አረፈች አንዲት ወጣት ልጅ በጣም ትታመማለች፤ ከህመሟ ለመዳንም ወደ ገዳም ትሄዳለች። ገዳም ገብታ ህመሟን ተቆቁማ መነኮሳትንና ነዳያንን በጉልበቷ ታግዝ ነበር። ገዳም በገባች በሁለተኛ ዓመቷ ከህመሟ ትድናለች። እናም ከጓደኛዋ ጋር ሆና ዋሻ ከዘጉት አባት ዘንድ ይሄዳሉ። የዚያን ጊዜም አባ "ልጄ አንቺ መመንኩስ አለብሽ፤ ጓደኛዋን ደግሞ አንቺ ወደ ዓለም ተመለሽ፣ አግብተሽ ወልደሽ ፈጣሪን አገልግይ" ሲሉ… እሷ ማልቀስ ትጀምራለች። ለቅሶዋም "እኔ ሳልበቃ መመንኮስ አልፈልግም ነበር" የሚል ነበር። አባንም "እባክዎ ባይሆን ሰውነቴ እስኪደክም በጉልበቴ ላገልግል" ትላቸዋለች። አባ ብዙ ሊያሳምኗት ቢሞክሩም እንቢ ስትል፣ በመጨረሻም "አይሆንም፤ እመቤርሃን ተደጋጋሚ እንድትመነኩሽ መልእክቱን እንዳደርስሽ ነግራኝ ነው" በማለት በአባታዊ ተግሳጽ ያዝዟታል። እሷም ምርር ብላ እያለቀሰች፦ "እመቤርሃን እናቴ፣ የእኔ ጸሎት ይሄ ነበር? ምንኩስና ፈተና ነው። እኔ ደግሞ ፈተናውን መወጣት አልችልም። እባክሽ የማልወጣውን ፈተና አትስጭኝ። እባክሽ ልጅሽን ለምኝልኝ፤ በፈተና መውደቅ አልፈልግም። መመንኩስ አልፈልግም! ምንኩስናን ጠልቼው ሳይሆን ምንኩስና ስለማይገባኝ ነው" እያለች ከልቧ ታነባለች። ጊዜው ደርሶ "ከሰነፍ መስዋዕት መታዘዝ ይበልጣል" ነውና ለግላጋዋ ወጣት አምናበት ሐሙስ ትመነኩሳለች። ልመናን የማትረሳ ወላዲት አምላክም በፈተና እንዳትወድቅባት ወደ እሷ ያመጣት ዘንድ ልጇን ማልዳ ሐሙስ መንኩሳ በሦስተኛው ቀን ቅዳሜ ለታ መለስ አሸለበች፤ ከዚህ ዓለም ድካም አረፈች። ታሪኩ የተፈጸመው በ2016 ዓ.ም ነው፤ እኔ ደግሞ በ2017 ዓ.ም በዲማ ጊዮርጊስ ገዳም ጓደኛዋ የነገረችኝን ምስክርነት ሳልጨምር ሳልቀንስ እውነተኛ ታሪኳን አወራኋችሁ። ከታች ያለው ፎቶ ምሳሌ እንጂ ትክክለኛ የእሷ ፎቶ አይደለም። በሕይወቴ እንዲህ አይነት ቅናት ቀንቼ አላውቅም፤ የምር ብዙ ነገር የተማርሁበት ታሪክ ነው። ጓደኛዋ ስለልጅቷ ስትናገር "ደግ፣ ሩህሩህ የሚል አይገልጣትም፤ ሲበዛ በጣም ዝምተኛ ነበረች" ትላለች። ቀንም ማታም ብትሰራ አታክትም ነበር፤ በእሷ ልክ የበረከት ስራ የሚሰራ የለም። እጅግ ሲበዛ የክርስቶስ ፍቅር ነበረባት። ህመሟን ጉዳይ አትለውም፤ እረፍት የሚባል ነገር አይታይባትም ነበር። ቀን በሥራ፣ ማታ በጸሎት ትተጋ ነበር። "እኔ ይሄው ከቤቴ ከወጣሁ 7 ዓመት በየገዳሙ እዞራለሁ፤ ያተረፍሁት ነገር ግን የለም። እህቴ ሁሌም በአይኔ ትመጣለች" ነበር ያለችው። የምር በዚህ ዘመንም እኮ በየገዳሙ ትንግርት የሆኑ ሰዎች አሉ። መታደል እኮ ነው! እኛንም ለእንደዚህ አይነት የክብር ሞት ያብቃን።
🗣13🎉𝕪𝕒𝕪𝕒🎉21🌹
Region: ET
Thursday 17 September 2026 17:32:45 GMT
Music
Download
Comments
sol :
ታድላ ሰማያዊው ህይወት እንደሚበልጥ ሁላችንም ልናውቅ ይገባል እንደ እህታችን መንገዱን ይምራን
2026-09-18 06:32:26
430
🗣13🎉𝕪𝕒𝕪𝕒🎉21🌹 :
#ሐሙስ_መንኩሳ_ቅዳሜ_አረፈች
አንዲት ወጣት ልጅ በጣም ትታመማለች፤ ከህመሟ ለመዳንም ወደ ገዳም ትሄዳለች። ገዳም ገብታ ህመሟን ተቆቁማ መነኮሳትንና ነዳያንን በጉልበቷ ታግዝ ነበር። ገዳም በገባች በሁለተኛ ዓመቷ ከህመሟ ትድናለች። እናም ከጓደኛዋ ጋር ሆና ዋሻ ከዘጉት አባት ዘንድ ይሄዳሉ።
የዚያን ጊዜም አባ "ልጄ አንቺ መመንኩስ አለብሽ፤ ጓደኛዋን ደግሞ አንቺ ወደ ዓለም ተመለሽ፣ አግብተሽ ወልደሽ ፈጣሪን አገልግይ" ሲሉ… እሷ ማልቀስ ትጀምራለች።
ለቅሶዋም "እኔ ሳልበቃ መመንኮስ አልፈልግም ነበር" የሚል ነበር። አባንም "እባክዎ ባይሆን ሰውነቴ እስኪደክም በጉልበቴ ላገልግል" ትላቸዋለች። አባ ብዙ ሊያሳምኗት ቢሞክሩም እንቢ ስትል፣ በመጨረሻም "አይሆንም፤ እመቤርሃን ተደጋጋሚ እንድትመነኩሽ መልእክቱን እንዳደርስሽ ነግራኝ ነው" በማለት በአባታዊ ተግሳጽ ያዝዟታል።
እሷም ምርር ብላ እያለቀሰች፦ "እመቤርሃን እናቴ፣ የእኔ ጸሎት ይሄ ነበር? ምንኩስና ፈተና ነው። እኔ ደግሞ ፈተናውን መወጣት አልችልም። እባክሽ የማልወጣውን ፈተና አትስጭኝ። እባክሽ ልጅሽን ለምኝልኝ፤ በፈተና መውደቅ አልፈልግም። መመንኩስ አልፈልግም! ምንኩስናን ጠልቼው ሳይሆን ምንኩስና ስለማይገባኝ ነው" እያለች ከልቧ ታነባለች።
ጊዜው ደርሶ "ከሰነፍ መስዋዕት መታዘዝ ይበልጣል" ነውና ለግላጋዋ ወጣት አምናበት ሐሙስ ትመነኩሳለች።
ልመናን የማትረሳ ወላዲት አምላክም በፈተና እንዳትወድቅባት ወደ እሷ ያመጣት ዘንድ ልጇን ማልዳ ሐሙስ መንኩሳ በሦስተኛው ቀን ቅዳሜ ለታ መለስ አሸለበች፤ ከዚህ ዓለም ድካም አረፈች።
ታሪኩ የተፈጸመው በ2016 ዓ.ም ነው፤ እኔ ደግሞ በ2017 ዓ.ም በዲማ ጊዮርጊስ ገዳም ጓደኛዋ የነገረችኝን ምስክርነት ሳልጨምር ሳልቀንስ እውነተኛ ታሪኳን አወራኋችሁ። ከታች ያለው ፎቶ ምሳሌ እንጂ ትክክለኛ የእሷ ፎቶ አይደለም።
በሕይወቴ እንዲህ አይነት ቅናት ቀንቼ አላውቅም፤ የምር ብዙ ነገር የተማርሁበት ታሪክ ነው። ጓደኛዋ ስለልጅቷ ስትናገር "ደግ፣ ሩህሩህ የሚል አይገልጣትም፤ ሲበዛ በጣም ዝምተኛ ነበረች" ትላለች። ቀንም ማታም ብትሰራ አታክትም ነበር፤ በእሷ ልክ የበረከት ስራ የሚሰራ የለም። እጅግ ሲበዛ የክርስቶስ ፍቅር ነበረባት። ህመሟን ጉዳይ አትለውም፤ እረፍት የሚባል ነገር አይታይባትም ነበር። ቀን በሥራ፣ ማታ በጸሎት ትተጋ ነበር።
"እኔ ይሄው ከቤቴ ከወጣሁ 7 ዓመት በየገዳሙ እዞራለሁ፤ ያተረፍሁት ነገር ግን የለም። እህቴ ሁሌም በአይኔ ትመጣለች" ነበር ያለችው።
የምር በዚህ ዘመንም እኮ በየገዳሙ ትንግርት የሆኑ ሰዎች አሉ። መታደል እኮ ነው! እኛንም ለእንደዚህ አይነት የክብር ሞት ያብቃን።
2026-09-17 17:34:30
107
ማርያምን እናቴ አንቺ ጠብቀኝ 🙏🙏🙏🙏🙏 :
betam yesmal yamal gen memrit new😭😭😭😭
2026-09-19 03:28:09
0
Buchlaye :
መታደሉዋ ብርከቶ ይደርብን
2026-09-18 12:03:41
68
ዘመድንቃል 💔ነኚ 👉የጎንደሯቺ🙍ብቸኛ 👈🤫 :
አቤት እዴት መታደል ነው
2026-09-18 05:46:31
55
የልደትየ ልጅ :
egzyabhr simert endzh new🥰🥰🥰
2026-09-19 07:22:18
0
እስራኤል የማርያም ልጅ :
Amen Amen Amen yabqagn
2026-09-19 17:08:55
0
w ፡d ሓራስ ነብሪ :
እግዛቤሔር የሷን በረከት ያሳድርብን
2026-09-18 09:09:30
62
Alem♎️ :
ይሄኮ መታደል ነው ሞት እጣ ፈንታ ነው ከሁሉም ታጥቦ ነፅቶ መሞት መታደል ነው እሷ ግን እንደሰው ስናስበው ልጅ ነበረች ነብሷ በሰላም ትረፍ😢😢😢
2026-09-18 21:07:43
23
Oda Kuye :
betam new yetadelechiw🥰🥰🥰
2026-09-19 13:55:02
0
hiwi 12 :
Bemebetw sm 🥰🥰🥰🙏
2026-09-19 23:13:52
0
Mechbezu :
በረከቷ ይደርብን
2026-09-19 17:32:36
6
Aemro Belete :
ይሕ አለም እንደዉ ከንቱ ነዉ መታደል ነዉ የእሷ
በረከት በእኔም ላይ ይድር እንዴት መወደድ ነዉ
2026-09-18 07:04:40
22
ጊዜ ለኩሉ :
ድንቅ መመረጥ
2026-09-17 20:54:48
22
Tise :
የማይዘልቅ ፀሎት ለቅስፈት ብለዋል አበዉ ሲናገሩ።
2026-09-18 07:35:27
5
ሁሉ በእርሱ ሆነ :
መቅሰፍት ነው አድነን ጌታሆይ
2026-09-18 17:45:03
5
Sol best :
እመቤቴ የሷን ክብር ለኔም ስጪኝ
2026-09-18 07:51:36
7
enate arsema (6) :
memeret malet endik new
2026-09-17 20:54:42
7
ልዑል :
እግዚአብሔር ሲመርጥ እንደዚህ ነው🙏🙏🙏🙏🙏
2026-09-18 05:52:18
6
Ezop kam :
ምነኛ መታደል ነው.
2026-09-19 13:28:35
1
Endalk ፲፮ :
በረከቷ ይደርብን በእውነት፣ይህ ነው መመረጥ😭😭😭😭
2026-09-18 06:48:21
3
zelalem mersha :
መታደል
2026-09-18 04:44:42
1
Ayu Tesfa :
ወይ መታደል
2026-09-18 04:36:33
2
wudalem birhan :
baraikata ydareiben
2026-09-18 05:45:12
1
MEB&H :
አቤት መታደል አቤት የፀጋ መብዛት 🙏🙏🙏
2026-09-18 06:47:21
3
To see more videos from user @yayaye917, please go to the Tikwm
homepage.