@my........55: #የባል እና ሚስት የሀላል ፍቅር ጨዋታ በግጥም 🌹ባል :― አንቺ የኔ ፍቅር የህይወት ጨረቃ ልቤ ይከፋዋል ሳጣሽ ለደቂቃ ሴቶች ብዙ ናቸው አንቺ ግን ልዩ ነሽ ህይወቴን አድሻት ካጠገቤ ሁነሽ 🌹ሚስት― አንተ የኔ ፍቅር የህይወት ነፀብራቅ ፍቅርክ ምግቤ ነው ከጎኔ አትራቅ ወንዶች ብዙ ናቸው አንተ ግን ልዩ ነክ ፍቅርክን መግበኝ ካጠገቤ ሁነክ። 🌹ባል:― የትዳር አጋሬ የልጆቼ እናት ደስታዬ አለሜ የሀላል ሚስቴ ነች ጌታየ ይመስገን እሷን አድሎኛል ውዴን የመሰለ ከቶ የት ይገኛል። 🌹ሚስት:― የልጆቼ አባት የትዳሬ አጋር ተስፋዬ ብሩህ እስካለሁ ካንተ ጋር መኖርክ መኖሬ መጥፋትክ መጥፋቴ ሳጣክ ቅር ይለኛል አትጥፋ ከፊቴ 🌹ባል:― የሽቶ መኣዛ የቴምር ጭማቂ ሁቢ ማር ወለላ ሁሌም ተናፋቂ ጣፈጭ ነገር ሁሉ አንቺን ይመስሉኛል ብቻ ምን ልበልሽ… ቃላቶች ያጥሩኛል! 🌹ሚስት:― የዐይኔ ማረፊያ የህይወቴ ፀደይ የፊትክ ብርሃን ይበልጣል ከፀሐይ የረህማን ፅጦታ የጀሊሉ ኒዕማ አንጀቴ ይርሳል ድምፅክን ስሰማ 🌹ባል:― ሚስቱን የሚመታ የትዳር አጋሩን የፍቅር አይደለም ሳስበው ነገሩን ውዷ ባለቤቴ ክብርሽ ይከበር አንቺን የመታው ቀን እጄ ይሰበር 🌹ሚስት:― እኔ እንክትክት ልበል እኔ ልሰባበር እሾክ አይውጋብኝ እንኳንስ መሰበር የፍቅር አርበኛ ፊትአውራሪ ጀግና አንተ መውድድ እንጂ ዱላ መች ታውቅና 🌹ባል: እኔ እዚህ ጎራ አንቺ ወዲያ ማዶ ልቤ አረረልሽ በፍቅርሽ ማገዶ የልቤ በረዶ መዳኒቴ ነሽ ውዷ ባለቤቴ ሁቢ እንዴት ነሽ 🌹ሚስት:― ፈረስ አይጋልበው በበቅሎ አይደረስ በርሬ እንዳልመጣ ያለክበት ድረስ ውዱ ባለቤቴ ፍቅርክ ለበለበኝ አሁንስ ከብዶኛል በዱአክ አስበኝ።
𝄢𝐋𝐢𝐉𝄢𝐇𝐄𝐘𝐔𝄢♥️🧕࿐
Region: AE
Thursday 17 September 2026 17:55:35 GMT
Music
Download
Comments
ሪችነኝ የወድሟ እርግብ R🌹🌹 :
ትክክክል ወላ👍👌🥰🥰
2026-09-18 03:06:24
0
𝄢𝐋𝐢𝐉𝄢𝐇𝐄𝐘𝐔𝄢♥️🧕࿐ :
ባለ ትዳሮች ብቻ አብቡት..😣ቁሞ ቀሮች አይዞን😁😭🤣...🙌
2026-09-17 18:06:51
2
نفيسه ❤️ :
[قلوب مرصعة بالنجوم][قلوب مرصعة بالنجوم]
2026-09-18 06:46:06
0
Yusuf :
😁😁😁
2026-09-17 18:11:00
0
ሀያት :
💕💕💕💕😍😍😍
2026-09-22 10:55:02
0
To see more videos from user @my........55, please go to the Tikwm
homepage.