@nejashi_media: #ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ! ሰይዱና ጫሌ ለዘምዘሙ ደግስ ተጠሩና መዲና ሐረም ተጥደው ተጋቱት። ጣም ጣም ቢላቸው ሐውዱን ከጀሉ። ዳሩ የእርሳቸው ዕጣ በመውጁ መስከር ሆነና በሐያት ወደ ሐገራቸው መለሳቸው። እነ አሕመደል ሐዲ ግን ፉት ያሉት የሸውቁን መርዝ ኖሮ ሩኃቸውን ነጥቆ ወደዚያኛው ሐገር ደበለቃቸው። እነ ሸህ ዳንግላ ዘምዘሙን ለጥም መቁረጫ ነይተው ቢጎነጩትም ዕድያቸው ለሐውዱ ድግስ ነውና እስትንፋሳቸውን ቆርጦ እዛው አጋደማቸው። ሰይድ ጫሌ "የኛማ ሙሐባ ምንድን አለው ለዛ እንደ አሕመደል ሐዲ ፍግም ታንል እዛ!" ብለው በትካዜ ያንጎራጎሩት ለዚሁ ነው። የካውካሶች ኸሊፋ፣ የነቅሸበንዲዮች ጌጥ ኢማም ሻሚል መዲና ሲገቡ ሰብሰብ ያሉ ሰዎች አግኝተው ተቀላቀሉ። ይህን ያዬ አንድ የአካባቢው ታላቅ ሰው ተጠጋቸውና ብስራት ሹክ አላቸው። ረሱሉሏህን ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም በዒሻራ አይቶ ነው። ሰይዳችን በመናሙ እንዲህ ነበር ያሉት። "ሻሚል የክብር እንግዳችን ነው። ሽር ጉድ ሊባልለት፣ ታላቅ መስተንግዶ ሊደረግለት ይገባል!" ኢማሙ ይህን ቡሽራ በሰሙ በጥቂት ቀናት ውስጥ እዛው መዲና ሞተው ጀነቱል በቂዕ ተቀበሩ። የሶሪያው ሸይኽ ዓብዱላህ ሲራጁዲን አል ሑሰይኒ በሰይዳችን ሙሐባ ክፉኛ የተነደፉ ነበሩ። ከኑራቸው ቀብቷቸዋል። በዚህም የተነሳ ሰዎች "ኑረል ሃላብ!" ይሏቸው ነበር። የአሌፖው ኑር። ስለ ነቢ ሲያወሩ ውለው ቢያድሩ አይጠገቡም። ስለ ትልቁ ሰው ሲፅፉ ልክ ሰይዳችን ከፊታቸው የተቀመጡ ይመስል ነበር። አንድ ጊዜ ሩቅ አገር የሚኖር ሰው ነቢን በህልም አይቶ ስለሳቸው እንዴት በደንብ ማወቅ እንደሚችል ሲጠይቃቸው "ሰይዱና ሙሐመድ ረሱሉሏህ የሚለውን የዓብደላህን መጽሐፍ አንብብ!" ብለው መልሰውለታል። ሸይኹን ነቢ ብዙ ጊዜ በመናም ዘይረዋቸዋል። በአንደኛው መናምማ "አንተ የኛ የምር አሽከር ነህ!" ብለው መሰከሩላቸው። በኺታማቸው መቃረቢያ ስለ ሶለዋት ፈዋኢዶች የሚያትት መጽሐፍ እያዘጋጁ ነበር። ማጠናቀቂያው ምዕራፍ ላይ እንደደረሱ ነቢን አዩ። ክፍላቸውን የሚስክና አምበር መዓዛ አጠነው። የመጡት እንግዳ ኑር ናቸውና ሊገልፁት የሚቸግር ብርሃን የሸይኹን ማረፊያ ሞልቶ የጀነት ጨፌ አደረገው። ጎረቤቶቻቸው እነ ሸይኽ ኢማዱዲን ወደ ክፍላቸው ገብተው የሆነውን ሲጠይቋቸው የኑሩ መገኛ፣ የሚስኩ መፍለቂያ፣ ጀነቱል ዑልያው ሰይዳችን መሆናቸውን ነገሯቸው። መቸስ ሶሪያ የሙሐባ ምድር ነበር። ይሄው ቀዬ ያበቀላቸው ሌላው ሸይኽ ኢሳ አል በይኑኒ ወዳጆቻቸውን ሰብስበው መውሊድ ማውጣት ጀመሩ። ሰኞ ለይሉን በአንዱ ተረኛ ቤት ይሀድራሉ። ታድያ አንዴ በዚህ መውሊድ ላይ አልፎ አልፎ በእንግድነት ይሳተፍ የነበረ ሰው ነቢን በመናም አዬ። በሺሩ "ለመውሊዱ ሰዎች ጥላ ከለላ እሆናለሁ!" ብለው አበሰሩት። ሰውዬው ከእንቅልፉ እንደነቃ ወደ ሸይኽ ኢሳ ሄዶ የመውሊዱ ቋሚ አባል እንዲያደርጉት ጠየቀ። እስከ እለተ ሞቱም ሲታደም ኖረ። ይህን መውሊድ ካወጡት ሙሒቦች አብዛኞቹ ነቢን በመናም አይተዋል። የሰርጉ ደጋሽ ሸይኽ ኢሳም ሐጅ ሲያደርጉ ነቢ በመናማቸው "በመዲና ቦታ ተይዞልሃል!" ብለዋቸው ነበር። ጉድ አትልም!? ቀኑ ሲደርስ ሞታቸው መዲና፣ ማረፊያቸው ጀነቱል በቂዕ ሆነ! ነቢ ሹመቴ ክብረት ማ’ረጌ ለዚሁ ብዬ ነው ሰርክ ማደግደጌ! #ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ! አሏሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!💚💚💚 #ለሌሎች_እንዲደርስ_ሼር #የእዉነት_ድምፅ #islamic_video
ነጃሺ ሚዲያ
Region: ET
Thursday 17 September 2026 18:18:02 GMT
Music
Download
Comments
abduselam abdu :
allhumosel weslimall allhumosel all ziynl wejuod
2026-09-18 17:44:13
0
Fetex fetex :
Alahumeseli ala seydina mewlana Muhammad selelahu aleyhi weselem
2026-09-29 08:07:00
0
user78107728184015 :
ኸ
2026-09-20 16:57:01
0
Miko Haftamu :
s.a.w
2026-09-29 22:27:38
0
fafilove82 :
Atiqa Ahmed🥰🥰🥰
2026-09-17 18:56:41
0
🤩neba afaru*** :
ፎቶው የሳቸው አደለም
2026-10-15 20:08:11
0
ቴምር :
ክፈችው በአሏህ
2026-10-20 09:30:19
0
Bilal Shafi :
🥰🥰🥰
2026-10-24 10:47:17
0
hanani :
💚💚💚💚
2026-09-18 13:19:01
0
sada🍫🦋💋 :
🥰
2026-10-22 18:43:50
0
Sadat abebe :
@muna @sada🍫🦋💋
2026-10-22 16:42:59
0
የሱፍ የጀሊል ባሪያ :
[Heartwarming][Heartwarming][Heartwarming]
2026-10-22 13:22:11
0
Hawwii Shariif :
🥰🥰🥰
2026-10-23 21:28:33
0
#£@ :
💚💚💚
2026-09-17 19:11:12
0
አፍሮ💈BARBE✂️💈 :
👌👌👌
2026-10-15 08:16:12
0
kedir :
🥰🥰🥰
2026-09-28 06:15:21
0
user3970188302285 :
😂😂😂
2026-09-27 20:51:18
0
Bilu kiya💚🔐❣️ :
🥰🥰🥰
2026-09-24 23:55:09
0
Bosena&Nun :
🥰🥰🥰
2026-09-22 21:18:52
0
kamer naser :
🥰🥰🥰
2026-09-18 13:41:15
0
nure muhamde :
🥰🥰🥰
2026-10-28 07:30:09
0
guyo :
🥰🥰🥰
2026-10-22 06:59:08
0
አብዱራህማን ቲጃኒ 🇪🇹 :
💚💚💚💚
2026-10-28 13:27:26
0
ፋጡማ :
[Red heart][Red heart][Red heart][Red heart][Red heart][Red heart][Red heart]
2026-09-18 12:29:49
0
To see more videos from user @nejashi_media, please go to the Tikwm
homepage.