@musictube369: ሰሞኑን ☺️ ✍️አንዳንዶች በዘመናት ውስጥ የማይፋቅ የታሪክ ድርሳናትን በተሰጣቸው የተስዕጦ ጥግ ከ እለት ትምርታቸው ጋር ደምረው ዛሬም ለነገው ይወደሳሉ፡፡ እሱ በማይመሹ የሙዚቃ ጥበብ ይራቀቃል በማያረጁ ጆሮዎቹ የድምፅን ልህቀት ያበጃል ድምፃዊያኖቸን በሱ ጀርባ ላይ ብርሀን እያዩ ተሻግረዋል፡፡ በቅጡ ክብር አልሰጠነውም በቅጡ አላመሰገነውም ይህ የአንተ መድረክ ነው ብለን አላወደስነውም፡፡ እሱ ለአይምሮ የከበዱ ለመመርመር ሌላ ዓለም የሚሹ የሙዚቃ ስራዎች ሰቶናል፡፡ የማይቀዘቅዝ ሁሌም ትኩስ የሆነ ማንነት ፣ትሁትነት፣ግልፅነት በሁሉም የተሟላ ሙዚቀኛ ነው የሱ ስራዎች ዘመናዊትን እንደ መስታወት ያሳያሉ አመታትን እንደዘበት ተሻግረው በሞገስ ያበራሉ ከዳህላክ ባንድ እስከ ላንጋኖ ስቱዲዮ የትውልድ ማንነትን ቅርፅን ተከቶሎ ዛሬም ድረስ ሙዚቃ ላይ ነው የዚህ አልበም ፊትአውራሪ ትውልደ ጃፖናዊው እጅግ የምወደው የማከብረው ባለ ሙሉ ሙዚቀኛ ያልተዘመረለት አበጋዝ ክብረወርቅ ሽዎታ ስለ ሰጠከን ስለምትሰጠን ሙዚቃዊ ስራዎች እጅግ ከልብ እናመሰግናለን🙌🥰 ✨ውድ ቤተሰቦቼ ፀሐዬ ዮሐንስ በጥበበኞች አጅቦ ያኔ በ1999 ዓ.ም ይሄን "ሳቂልኝ አልበም ሲሰራ የመጀመሪያው አልነበረም 10ኛ አልበሙ ነበር😅 ከሱ በፊት  በ1986 የሐገርሽ ልጅ ነኝ ፣ ፌዘኛን 1978  በገነት የሙዚቃ ቤት በኩል /ሎጋ/ ሌሎችም ያሉበት …፣ ጡር ነውን -በ1979 ፣ ፍንጭቷን -1975 ፣ ሰላም አይለይን ... አይነት ተወዳጅ አልበሞችን በግሉ በጋራም ከነዋይ አረጋኸኝ ፀጋዬ ጋር በመሆን በነጠላ ዜማም ቢሆን ሳቂልኝ ሙሉ አልበም በአበጋዙ በቅንብር ፡ ሞገስ ተካ በግጥም ፣ ዘውዱ በቀለ በፊውቸር የገቡበት ነበር ፡፡ የተለያዩ ነጠላ ዜማ ሰርቷል … አዝነሽ አልይሽ ፣ ዛሬ ነው ፣ መተባበር ቢኖር ከ ንዋይ ደበበ እና ፀጋዬ እሸቱ የአበበ መለሰ ግጥም ዜማ ላይም ቢሆን ተሳትፎ ነበር አንጋፋው ፀሐዬ ዮሐንስ👌 📌ታዲያ ሁሌም ከምደረክ ጀርባ ከአያንዳዱ አልበም ጀርባ ከፊት ሳይመጡ ተረስተው የሚቀሩ ጀግኖች እንዳሉ እሙን ነው ልክ ዛሬ እንደምናከብረው የዚህ እና የበርካታ ተወዳጅ ሙዚቃዎች የዜማ እና ግጥም ደራሲ በኔ ግምት ይህ ሰው እንደ ሀገር ሊመሰገን ፣ እንደ ሀገር ሊሸለም ፤ ለሀገራችን ለኪነጥበብ ዕድገት ላስቀመጠው አሻራ ሀውልት ሊቆምለት የሚገባ ጉምቱ ብዕረኛ ነው የዘጠናዎቹ ትዝታችን ጌታ !! ያልተዘመረለት ባለቅኔ የዜማ እና ግጥም ደራሲ ሐብታሙ ቦጋለ 🙏🙏 የሚካኤል በላይነህ የነገን ማወቅ ፈለግኩኝ የታምራት ደስታ ሁሉንም ከ3ዘፈኖች በቀር የገረመው አሰፋ ንፁህ ነሽ አልበም ራሄል ጌቱ ክስቶ ጎሳዬ ተስፋዬ, ሄለን በርሄ, አብዛኛውን ማዲንጎ አፈወርቅ፦ ትዝታ ባጠቃላይ ከ500 በላይ ዘፈኖች በግጥም የደረሰ ብዙ ዜማዎችን አዋዶ የሰራ ፍፁም ያልተነገረለት ጥበበኛ ነው ሀብትሽ👌 📌ለፀሐዬ ይሄንን ሙዚቃ ጨምሮ ሩቅ አይደለም + ብቻ ነይ እንጂ +የዋሃ ልቤ+ አንዳንዴ . . . መታደል ነው + ተይ ብዬ ነግሬሽ ለኤፍሬም ታምሩ እናትዬ + የኔ ነገር + የግድ ሰው+ ተረጋጋሽ ወይ+ ዳኛ ዳኛ. . . ለጎሳዬ ተስፋዬ አንለያይም+ አልሄድም+ አይጠበቅም+ ሳያት ታሳዝነኛለች+ ካአንቺ አይበልጥም . . . (ታምራት ደስታ) ማያዬ+ ሊጋባ+ ልገለፅልሽ+ እንዴት+ንግስተ ሳባ . . . (ጥበብ ወርቅዬ) የፍቅር ምርጫዬ+ አንተ ጉዳና+ ሳላየው ልቀር ነው ..ለሚካኤል በላይነህ ትዝታ+ ማን እንደ እኔ... ለማዲንጎ አፈወርቅ ልቤ ልቤ፣ መታደሌ.. ለግርማ ተፈራ እሷን ሳያደርጋት+ ደግሞ ምን ቀረሽ+ አተረፈ ልቤ . . . (ይርዳው ጤናው) ጉዳዬ ነሽ + ከእሷ ሌላ . . .ለወንድሙ ጅራ ብሎ ብሎ + ማን አለው ሰው ...ለፍቅራአዲስ ነቃ ጥበብ ከደኛው (ሩቅ ሆኜ ሳለ) ለሄለን በርሄ እንዴት ብዬ + ደሞ ና.... ለሀይማኖት ግርማ ንፁህ ነሽ + ልዮ ...ለገረመው አሰፋ ግዴለም + ሸቀጥ.... ለደረጀ ዱባለ ስሜንህ+ አታስረጁኝ . . . ለአስቴር ከበደ ትርፌ +ሰረቅ+ የኔ ፍቅር + ነበር ...ለራሄል ጌቱ ዞሮ ዞሮ፣ ዝም አንልም... ለዳግማዊት ፀሀዬ . . . የሙዚቃው አለም ስጦታ የዜማ እና ግጥም ደራሲው ሀብታሙ ቦጋለ ክብር ይገባሃል እናመሰግናለን🙏🙏 🗣️ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🫡 Musictube #fyp #ፀሐዬዮሃንስ #ሰሞኑን #musictube369 #ethiopianmusic

🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
🅼🆄🆂🅸🅲 🆃🆄🅱🅴
Open In TikTok:
Region: ET
Friday 18 September 2026 19:30:32 GMT
35142
3064
10
305

Music

Download

Comments

oro1224567
oro12345678 :
🥰🥰🥰🥰
2026-09-19 07:13:23
0
bere19.0
birhanu agafari :
ሄደች እንጂ በቃ
2026-09-19 04:49:42
0
user1467239244812
Dubiso Bamud :
❤️❤️❤️
2026-09-18 19:52:03
2
ms937312
ms olds :
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-09-18 19:59:03
1
hailu.diriba
Hailu Diriba :
🥰🥰🥰
2026-09-19 06:01:46
0
ermiyas_t
Ermiyas_t :
🥰🥰🥰
2026-09-19 08:13:08
0
yaredmmmm
መናገር :
✌️✌️✌️✌️👌👌👌👌
2026-09-18 22:05:23
0
meazi770
meaza tsegaye :
❤❤❤
2026-09-19 05:25:28
0
ermiyas_t
Ermiyas_t :
👍👍👍
2026-09-19 08:13:11
0
bety.mofoetiopia
🤷‍♀️19 yelehubetm 🌬 :
🎧🔥🔥[Gesture OK]
2026-09-19 08:45:45
0
To see more videos from user @musictube369, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About