@fanuel_zewold: @Elufan Events® | እሉፋን ኢቨንትስ አለም ሙሉ ስለሱ ያወራል፤ ሀገሩ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን 5 ፐርሰንት ህዝብ እንኳን የማያቀው። በ 156 ሀገራት ዘንድ ስሙ የሚጠራው ይህ አስደናቂ ሰው ቢኒያም ሽብሬ ይበላል። ቢኒያም ሽብሬ ተወልዶ ያደገው አዲስ አበባ ፈረንሳይ ሌጋሲዮን አካባቢ ነው። ምንም እንኳን ቤተሰቦቹ በወቅቱ በኢኮኖሚጥሩ አቋም ላይ የነበሩ ቢሆንም፣ ባጋጠማቸው ከፍተኛ የመክሰርና የውረስ አደጋ ምክንያት ብዙ ንብረቶችን ሊያጡ ችለዋል። ይህን ተከትሎ በመጣባቸው ከባድ ጭንቀት ምክንያት ሁለቱም ወላጆቹ ገና በሕፃንነቱ ከዚህ ዓለም በሞት የተነጠቀው። ቢኒያም ወላጆቹን ካጣ በኋላ ህይወቱን ከታላላቅ ወንድሞቹ ጋር አብሮ መግፋት ጀመረ። ነገር ግን ያጋጠማቸው የኢኮኖሚ መፈራረስ ህይወትን እጅግ ስላከበዳት፣ ገና በሕፃንነቱ ራሱንም ሆነ ታላላቅ ወንድሞቹን በገቢ ለማገዝ ወደ ሥራ ዓለም ለመቀላቀል ተገደደ። ከቤት ከወጣ በኋላ የነበረው ትግል እጅግ እየበረታ ነበር። የዕለት ጉርሱን ለማግኘት የሚቸገርበት፣ የሚበላው አጥቶ የሚርበውና በኪሱ ምንም ሳንቲም የማይይዝባቸው ከባድ ጊዜያትን አሳልፏል። በዚህ ሁሉ ስቃይና ችግር ውስጥ ሆኖም ቢኒያም ተስፋ ሳይቆርጥ የቲያትር እና የዳንስ ክህሎቱን ለማሳደግ ወደ ታዋቂውና አንጋፋው የኪነጥበብ ሰው ወደ ጋሽ አበበ ሞክሪያ ዘንድ ያለማቋረጥ ይሄድ ነበር።ለስኬቱ ሲል ያልከፈለው መስዋዕትነት አልነበረም። ቢኒያም ለህይወት ምርጫውና «እዚህ ጋ አዲስ ክህሎት አለ» ሲባል ለመማርና ራሱን ለማብቃት የማይገባበት ነገር አልነበረም። በማንኛውም ጥበብ ውስጥ ገብቶ መፈተሽ የሚፈልግ፣ እጅግ ሁለገብና ታታሪ ሰው ነበር።ቢኒያም ህይወቱን ለመቀየር ወደ ደቡብ ሱዳን በመጓዝ የራሱን የኤሌክትሮኒክስ ሱቅ ከፍቶ ሰርቷል። ከዚያም ወደ ሀገሩ በመመለስ የእንጨት ስራዎችን እና የተለያዩ ዘመናዊ የስቱዲዮ ግንባታ ስራዎችን በመስራት ጠንካራ ሰራተኛነቱን አስመስክሯል። ከዛም ቀስ በቀስም በተለያዩ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ቪዲዮዎች ላይ በውዝዋዜ መሳተፍ የጀመረ ሲሆን፣ በምሽት ክለቦች ውስጥም በዳንሰኛነት እና በኮሪዮግራፈርነት መስራት ቻለ። በታደለ ሮባ የሙዚቃ ቪዲዮ ላይም በዳይሬክተርነትና ኮሪዮግራፈርነት ሰርቷል። እንዲያውም በጥበቡ በመግፋት እጅግ ዝነኛ እና ተወዳጅ የሆነውን የራሱን "ዳንሴ ዳንሴ" (Dancey Dancey) የተሰኘውን የሙዚቃ ቪዲዮ ሰርቷል፤ቢኒያም በጥበብ ብቻ አልተወሰነም፤ ሰውነቱን ለማጠናከር በሰውነት ቅርፅ ግንባታ (Bodybuilding) ውድድሮች ላይ ጭምር መሳተፍ ጀመረ። የሰርከስ ባለሙያ በመሆንም በጂምናስቲክስ እና በሰርከስ ትዕይንቶች ላይ ሰርቷል፤ ከዚህ ጎን ለጎን የሰዎችን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ (Fitness) የሚያሰለጥን የግል ስፖርት አሰልጣኝ ሆኖ ሰርቷል። ወደ አሜሪካ ያቀናው በፍቅረኛው በአሪዬላ (Ariela Weinberg) ስፖንሰርሺፕ በተገኘው የ90 ቀናት የእጮኝነት (K-1) ቪዛ ነበር። በአሜሪካው TLC ጣቢያ በሚቀርበው "90 Day Fiancé" በተሰኘው እጅግ ታዋቂ የሪያሊቲ ሾው ላይ ከባለቤቱ ጋር በመቅረብ በ156 ሀገራት ዘንድ በሰፊው ታውቆ ከፍተኛ ዓለም አቀፍ ዝናን አተረፈ ። ቢኒያም በስፖርቱ ዓለም በታይኳንዶ 5ኛ ዳን ያለው ጥቁር ቀበቶ ባለቤት ሲሆን፣ በሩጫ ውድድር በ5,000 ሜትር ለሀገሩ ወርቅና ዋንጫ አስገኝቷል። በITF ታይኳንዶ በ2016 በብራዚል ሁለት ሜዳሊያ፣ በ2019 ደግሞ በህንድ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎችን በማምጣት የአለም ሻምፒዮን (Champion) ነው። ይህ ባለብዙ ተሰጥኦ አትሌት የራሱን የሰውነት ተገለባባጭነት እና የትግል ስልት በማቀናጀት ለታዋቂ የሆሊውድ አክሽን ፊልሞች ላይ እንደ Spider-Man፣ Green Goblin እና Black Panther ባሉ ገጸ-ባህሪያት ውስጥ በስታንት ማንነት (Stuntman) ሰርቷል። አልፎ ተርፎም ከአለም አቀፉ ታዋቂ ራፐር ኬንድሪክ ላማር ጋር በትልቁ የ'ሱፐር ቦል' (Super Bowl) መድረክ ላይ አስደናቂ ትርኢት በማቅረብ የኢትዮጵያን ስም በዓለም መድረክ አስጠርቷል። ቢኒያም በዓለም አቀፍ የኤምኤምኤ (MMA) 4 ውድድሮች ላይ ተጋጣሚዎቹን ከ6 ሰከንድ እስከ 4 ደቂቃ ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ በመዘረር ሀገሩን ወክሎ የሚፋለም ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ፋይተር ነው። አሁን ላይ ከአንድ ጓደኛው ጋር በመሆን «ዳይናሚክ» የተባለ ትምህርት ቤት የመሰረተ ሲሆን፣ ለህጻናት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣ የሰርከስ ጥበብ እና ዳንስ ያስተምራሉ። አሁን ደግሞ ይህ ዓለም አቀፍ ፋይተር ወደ እናት ሀገሩ ኢትዮጵያ ተመልሷል። መስከረም 9 ቀን ከማስተር ሀገረ ሰላም ጋር የሚያደርገው ታላቅ የፋይት ውድድር (Ethio Fight Night) በመላው ሀገሪቱ በጉጉት ይጠበቃል። እስካሁን ባለው ግምት አብላጫውን የህዝብ ድምፅ ያገኘው ቢኒያም ሽብሬ ነው። ታዲያ "ነብይ በሀገሩ አይከበርም" እንደሚባለው፤ እንዲህ አይነት የሀገር ባለውለታዎችንና ጀግኖችን ማወቅ እና ማክበር አይገባንም ትላላችሁ? ለመሆኑ በእናንተስ ግምት መስከረም 9 በሚደረገው በዚህ ታላቅ ፍልሚያ ማነው የሚያሸንፈው? ቢኒያም ሽብሬ ወይስ ማስተር ሀገረ ሰላም? ግምታችሁን በኮሜንት አስቀምጡልን ፋኑኤል ነበርኩኝ ፣ ክበሩልኝ ቀን፦ መስከረም-2019 ምንጭ ፦ seifu on ebs :www.imdb.com :www.mmafighting.com :የራሱ የሶሻል ሚዲያ አካውን @biniyam_shibre | @Ethio Fight Night 🇪🇹 #EFN #MMA #mmafighter #biniyamshibremanew? #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
Fanuel Zewold
Region: ET
Saturday 19 September 2026 11:00:46 GMT
Music
Download
Comments
🦋 🍫Ricco France🇫🇷🇫🇷16 :
never correct news ok
2026-09-19 15:33:35
1
🌴 Habታታ 🌴 :
ግነት በዛበት !
2026-09-19 12:07:28
6
Abu demeke :
ድል ለቢኒ
2026-09-19 18:07:42
2
sintayehu Hailemariam :
ተባረክ እውነት ነው
2026-09-19 12:20:49
6
derese d :
dili binami💪💪💪💪💪💪
2026-09-19 17:00:19
1
zelalem :
ጀግነ ፈታሪ ይታብክህ
2026-09-19 13:32:21
1
lidu🇫🇷 :
🥰😂
2026-09-19 11:38:26
2
tilahunabirham :
bin
2026-09-19 15:02:39
1
Abdulemejed :
እዳሰማ
2026-09-19 18:32:40
0
Ashu19 :
2026-09-19 18:25:20
1
🇫🇷𝙮𝙚𝙢𝙖𝙧𝙮𝙖𝙢🇫🇷🇫🇷 :
2026-09-19 16:07:45
0
misrak taddese :
ደግ እና ለሰው የሚረዳ መልካም አባት ነበረዉ ጋሽ ሽብሬ ጥሩ ሰው ነበር
2026-09-19 17:20:30
0
lala,lala :
ተባረክ
2026-09-19 17:08:16
0
emuye :
👍👍
2026-09-19 11:58:08
0
tilahunabirham :
bin je
2026-09-19 15:02:55
0
🆎DI :
ቀኑ ደርሷል
2026-09-19 13:56:06
0
yaki :
aweke are zim beal
2026-09-19 14:57:28
0
Natnel Teka :
💪💪💪
2026-09-19 11:05:08
3
kira 44 🇦🇹🇦🇹 :
❤️❤️❤️
2026-09-19 12:31:49
1
Ashagre Lagasa :
🥰🥰🥰
2026-09-19 18:49:31
0
መብት አለምዬ :
👌👌👌
2026-09-19 18:56:41
0
እዩኤል :
@biniyam_shibre
2026-09-19 13:17:17
1
abrish :
👌👌👌👌👌👌💪🏼💪🏼
2026-09-19 18:36:39
0
tashomaa :
❤️❤️❤️
2026-09-19 18:10:58
0
rawda sulemn :
[Heartwarming][Heartwarming][Heartwarming][Heartwarming]
2026-09-19 11:55:24
0
To see more videos from user @fanuel_zewold, please go to the Tikwm
homepage.