@enduplus: ስትሄጂ💔 በቀዝቃዛ ለሊት ያነደድናት እሳት እንደዋዛ ስሌት ሃሳብ ካፈረሳት የከፈልናት እዳ ያሳለፍነው ፍዳ በሰው ምድረበዳ ትዝታሽ ከከዳ ናፍቆት ሲዘነጋ ፤ ማእዱ ሲጣፍጥ ቀን መሽቶ ሲነጋ ፤ አይን ሲቀላውጥ ድምፄ እልፍ ማዶ ፤ በር ማየት ሰልችቶሽ ጆሮሽ ሌላ ለምዶ ፤ እንቅልፍ እረፍት ሰቶሽ ያለ እኔ ከተኛሽ ...አስችሎሽ አፍሽ ብቻውን ጠጥቶ ጥምሽ ካለፈለት ወጥቶ ልብሽ... ስንብት ጦር ቢስል አንቺን እንዳይመስል ዘላለም ያልሽው ቃል ከጮኸ ይበቃል ያለእኔ ከሞቀ ቤትሽ ከደመቀ ፍቅሬ... የትላንቷ እንዳትቀሰቅሺኝ ካስጀመርሺኝ ህልም ውስጥ ለንፁህ ትላንትሽ ነገዬን ለሷ ልስጥ። እጅ ተያይዘን ከተሻገርነው ድልድይ በአይኖቻችን ፈዘን ካሳለፍነው ስቃይ በልባችን አለም አንድ ላይ ስንጠፋ ህይወት ስተቀለም በፍቅራችን ቀለም የምድር ገለመኔው ካለ እኔ ...ግድሽ አልነበረም። አይ የጊዜ ቅኔው ፤ የማይሻር የለም። ባንቺ ሰው ማፍቀር እንደምችል አየሁ ታዲያ በምን አንጀት በየትኛው ልቤ ልጠላሽ ችላለሁ። ልቤ እኮ አንቺጋ ነው ልብሽ ያባከነው ፍቅርሽ እያደማው ውስጥሽን ሲሰማው አይንሽን ሲማትር ሳቅሽን ሲጠማ መደበቂያ ቋቱ የትላንት ጨለማ ቀን ካደረቃቸው ጽጌረዳዋች ከወለቁ ሀብል ጌጦች ከተበታተኑ ፎቶ ከተቀደዱ አንሶላዎች ከወጣሁት ተራራ ከገባሁት ገደል ከጣፋጭ መራራ ካጠፋሁት በደል ከገፋሁሽ ቀኖች ዛሬ እንኳን ብትርቀን አንዷን የፍቅር ቀን አስታውሻት አደራ እኔ... ዛሬም ትላንት ላይ ነኝ ልብሽ እንዳመነኝ ውሀሽ እንደጠማኝ ፍቅርሽን ተንተርሼ ትዝታሽ ላይ ተኝቼያለሁ እሱንም ካጣሁኝ እሞትብሻለሁ። ይገ፟ባኛል ካልሽው ፤ ሰብስበሽ ስትወስጂ ንፁህ ትዝታሽን ፤ አንዴ ሳም አርገሺኝ ጥለሽልኝ ሂጂ።🏃🏽♀️ አደራ... በድቅድቅ ጨለማው ፤ ለሊት እንደመጣሽ በድቅድቅ ጨለማው ፤ በለሊቱ ልጣሽ። 💔 #foruyou #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #foryoupage #fyp #virall
ስቃዬ 💔
Region: ET
Monday 21 September 2026 10:55:41 GMT
Music
Download
Comments
zwd :
2026-09-21 10:59:09
0
mimi :
🥰🥰
2026-09-21 12:03:23
0
sena :
🥰🥰🥰🥰
2026-09-21 11:17:34
0
Dagim :
🥰🥰🥰
2026-09-21 11:08:20
0
JOYFUL :
😢 😭
2026-09-21 11:04:35
0
ስቃዬ 💔 :
💔💔💔💔💔💔
2026-09-21 10:57:22
0
masho Abrha :
🍀🍀🍀🍀🍀🌻🌹
2026-09-21 12:35:49
0
To see more videos from user @enduplus, please go to the Tikwm
homepage.