@mulu.zeresenay: የመጨረሻ ስንብት አምናለሁ— ላንገናኝ መሄዷን፣ ጨክና ከሌላ ሰው መልመዷን። እኔ በትዝታ ስቀር፣ እሷ በአዲስ ሕይወት መጓዟን። የሚያምመኝ መሄዷ ብቻ አይደለም፤ አብረን ያሳለፍነው የፍቅር ዘመን ዛሬ ትዝታ ሆኖ መቅረቱ ነው። እኔ ግን አልክድም— የወደድኩሽ ፍቅር የጊዜው ጨዋታ አልነበረም። ልቤን ሰጥቼ፣ ተስፋዬን ጥዬ፣ ከእውነት ነበር የቀረብኩሽ። ዛሬ ሌላ ሰው ቢሆንልሽ እኔ ልከልክልሽ አልችልም። ፍቅር ማለት የምትወጂውን ሰው ማሰር አይደለም፤ እንኳን ከእኔ ባትሆኚ ደስታሽን መመኘትም ነው። ስለዚህ ሂጂ… እኔም በዝምታ እሰናበትሻለሁ። የነበረንን በቁጭት አልቀብረውም፤ እንደ አንድ ውብ ትዝታ በልቤ እጠብቀዋለሁ። ምናልባት መጨረሻችን አንድ ላይ መሆን አልሆነም፤ ግን የነበረው ፍቅር በእኔ ውስጥ ሐሰት አልነበረም። ሰናበቺኝ… የተለየን ቢሆንም፣ የወደድኩሽን አልክድም። አንዳንድ ፍቅር ለዘላለም አብሮ ለመኖር አይደለም፤ አንዳንዱ ፍቅር ለልብ እውነትን ለማስተማር ይመጣል። አንቺም በሕይወቴ የተረሳሽ ሰው ሳትሆኚ፣ በእውነት የተወደድሽ ሰው ሆነሽ ትቀሪያለሽ።
Mulu ዘረ-ሰናይ
Region: ET
Monday 21 September 2026 13:14:32 GMT
Music
Download
Comments
መኖር ነው በተሰፋ :
000
2026-09-22 12:22:02
1
ttem🍫🍫 :
በትክክል 🙏🙏🙏
2026-09-22 22:41:10
1
Ibnu Hamdi Ferhan :
🥰🥰🥰
2026-09-25 23:38:52
0
Mohan🤴🥷 :
👑👑👑
2026-09-24 11:54:00
1
Bosaon :
👍👍👍
2026-09-25 04:44:55
0
Toltummaa yaddii :
🥰🥰🥰
2026-09-23 23:35:20
1
ሙሀመድ ሰይድ :
🥰🥰🥰
2026-09-23 20:57:36
1
Birahanu :
🥰🥰🥰
2026-09-23 20:40:47
1
kokii :
🥰🥰🥰
2026-09-23 19:54:15
1
@misge got :
🥰🥰🥰
2026-09-23 13:11:56
1
Anu love 💔🦋💔 :
🥰🥰🥰
2026-09-23 15:43:51
1
yefikir sawfikir :
🥰🥰🥰
2026-09-25 04:29:10
1
To see more videos from user @mulu.zeresenay, please go to the Tikwm
homepage.