@weleteabew1: ይነበብ👇 የአንድ ሰው ውድቀት የቤተ ክርስቲያን ውድቀት አይደለም! በቅርቡ በትግራይ ክልል “መንበረ ሰላማ” ተብሎ ከኢትዮጵያ ሲኖዶስ የተለየው አካል ውስጥ አንድ ኃላፊ (ጳጳስ) በከባድ የሥነ ምግባር ጉዳይ መውደቃቸው በሚል የተለያዩ ወሬዎችና አስተያየቶች እየተሰራጩ ይገኛሉ። አንዳንዶች ግለሰቡን ይወቅሳሉ፤ ሌሎች ደግሞ ከግለሰቡ ውድቀት ተነስተው ቤተ ክርስቲያንን ይወቅሳሉ። ከዚህም በላይ “እነሆ ቤተ ክርስቲያን ወደቀች” በሚል የሚያቀርቡትም አሉ። እዚህ ላይ ግን አንድ ትልቅ መሠረታዊ ጉዳይ መለየት ያስፈልጋል፦ ሰውን ከቤተ ክርስቲያን፣ የአገልጋይን ውድቀት ከክርስቶስ ቅድስና ጋር ማደባለቅ አይገባም። አንድ አገልጋይ ቢወድቅ ቤተ ክርስቲያን አትወድቅም ✍️ቤተ ክርስቲያን የቆመችበት መሠረት ሰው አይደለም፤ ክርስቶስ ነው። '' ወአንሰ እብለከ ከመ አንተ ኰኵሕ፥ ወዲበ ዛቲ ኰኵሕ አሐንጻ ለቤተ ክርስቲያንየ፥ ወአናቅጸ ሲኦል ኢይኄይልዋ። “በዚች ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ የገሃነምም ደጆች አያሸንፏትም እንዲል።” — ማቴዎስ 16፥18 ጌታችን “ቤተ ክርስቲያኔን በእናንተ ፍጹምነት እሠራለሁ” አላለም፤ “ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ” አለ። ስለዚህ የአንድ አገልጋይ ኃጢአት የክርስቶስን ቃል ሊያፈርስ አይችልም።ምክንያቱም የማትሳሳት ቤተክርስቲያን እንጂ የማይሳሳት አገልጋይ አላት የሚል ዶክትሪን የለንምና። አገልጋዩ ሰው ነው፤ ቤተ ክርስቲያን ግን የክርስቶስ ናት። ሰው ይሳሳታል፤ ክርስቶስ ግን አይሳሳትም። ሰው ይወድቃል፤ ክርስቶስ ግን አይወድቅም። ሰው ይለወጣል፤ ወንጌል ግን አይለወጥም። ይህ አዲስ ነገር አይደለም በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የአገልጋዮች ውድቀት ዛሬ የተጀመረ አይደለም።እኛ ከላይ እንደጠቀስሁት እንደካቶሊክ የማይሳሳት አባት አለን የሚል አስተምህሮ ፈጽሞ የለንም። ይሁዳ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ነበር። ከጌታ ጋር ተመላለሰ፣ ትምህርቱን ሰማ፣ ተአምራቱንም አየ፤ በመጨረሻ ግን አሳልፎ ሰጠው። ጴጥሮስም ከዚያው ደቀ መዛሙርት መካከል ነበር፤ በአንድ ሌሊት ጌታውን ሦስት ጊዜ ካደ። ነገር ግን ይሁዳ ስለወደቀ ክርስቶስ አልወደቀም። ጴጥሮስ ስለተሳሳተ የወንጌል እውነት አልተለወጠም። ስለዚህ ዛሬም አንድ አገልጋይ በኃጢአት ቢወድቅ፣ ይህን ውድቀት በመጠቀም “ቤተ ክርስቲያን ወደቀች” ማለት የሰውን ውድቀት ከክርስቶስ ሥራ ጋር መደባለቅ ነው። 👉በወደቀው ላይ ማሾፍ የክርስቲያን ድል አይደለም። የአንድ ሰው ኃጢአት ተገልጦ ሲታይ ክርስቲያናዊ ምላሽ ሳቅና ማሾፍ አይደለም። እንዲሁ የተሳሳተን ሰው ስህተቱን ሳንነካ መሸፈንም አይደለም። ስህተት ስህተት ነው፤ ኃጢአትም ኃጢአት ነው። ነገር ግን ኃጢአተኛው ሰው ለንስሐ የተጠራ ወንድማችን ነው። ቅዱስ ጳውሎስ''አኀዊነ ለእመ ቦ ብእሲ ዘስሕተ እምኔክሙ፤ አንትሙ እለ በመንፈስ ቅዱስ አጽንዕዎ በመንፈሰ የውሀት እንዘ ትትዐቀቡ ለርእስክሙ ወኢትስሐቱ። “ሰው በአንዳች በደል ቢያዝ፥ እናንተ መንፈሳውያን የሆናችሁ እንደዚህ ያለውን በየዋህነት አስተካክሉት፤ እናተም ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።”ብሎናል — ገላትያ 6፥1 በወደቀው ሰው ላይ የምንስቅበት ምክንያት የለንም፤ ዛሬ እርሱ ወደቀ፣ ነገ እኛ ልንወድቅ እንችላለን። ስለዚህ የሚገባን መጸለይ፣ ለንስሐ መመኘት፣ ስህተቱንም በእውነት መጠቆም እንጂ በውድቀቱ ላይ ደስ መሰኘት አይደለም። ለሚያጨበጭቡትም አንድ ነገር ማለት ፈለግሁ 👈በተለይ ሞስሊም ወገኖቻችን👇 አንዳንዶች ከአንድ ሰው ውድቀት ተነስተው “እነሆ፣ ቤተ ክርስቲያን ወደቀች” በሚል ይደሰታሉ። ይህ ግን የማስረጃ አጠቃቀም ስህተት ነው። አንድ ሰው ወደቀ = ሁሉም ወደቀ የሚል ሕግ የለም። ይህን ለመቀበል ከፈለግን የሁሉንም ሃይማኖትና ተቋም በግለሰቦች ስህተት መፍረድ ይኖርብናል። ይህ ግን ፍትሐዊ የሆነ መመዘኛ አይደለም። እኛም እንደዚሁ እንጠንቀቅ፤ የሌላውን ወገን አንድ ግለሰብ ሲሳሳት በመያዝ ሃይማኖቱን በጠቅላላ እንደማንፈርድ፣ የእኛንም አንድ ግለሰብ ውድቀት በመያዝ ቤተ ክርስቲያንን በጠቅላላ መፍረድ አይገባም። በመጨረሻ የአንድ አገልጋይ ውድቀት ውድቀት ነው፤ እንደ ውድቀትም መታየት አለበት። ኃጢአትን በሃይማኖት ስም መቀበል የለብንም። ነገር ግን የአንድ ኃጢአተኛ ውድቀት በመያዝ የክርስቶስን ቤተ ክርስቲያን የወደቀች ማድረግም አይቻልም። ቤተ ክርስቲያን የግለሰብ ስህተት ማከማቻ አይደለችም፤ የክርስቶስ አካል ናት። “ክርስቶስ ደግሞ በራሱ ቤት ላይ እንደ ልጅ ታማኝ ነው፤ ቤቱም እኛው ነን።” — ዕብራውያን''3''6 ''ወክርስቶስሰ ከመ ወልድ ውስተ ቤቱ ወንሕነ ውእቱ ቤቱ እለ አመነ ለእመ ዐቀብነ ሞገሰነ ወምክሐነ ጽኑሕ ተስፋነ ለዝሉፉ።እንዲል ስለዚህ፣ የወደቀውን እንደግፍ እንጂ በውድቀቱ አንደሰት፤ ስህተቱን እንውቀስ እንጂ ሰውነቱን አንጥላ፤ እውነትን እንናገር እንጂ ሐሰተኛ ወሬን አንስራ። የሰው ውድቀት የክርስቶስ ውድቀት አይደለም። የአገልጋይ ስህተት የወንጌል ስህተት አይደለም። የግለሰብ ውድቀት የቤተ ክርስቲያን ውድቀት አይደለም። እግዚአብሔር የወደቀውን ያንሳ፤ የተሳሳተውን ወደ ንስሐ ይመልስ፤ እኛንም “የሚቆም የሚመስለው እንዳይወድቅ” ብሎ እንዳስጠነቀቀን በፍቅሩ በቸርነቱ ይጠብቀን። አሜን 🙏 ቀን 11 '1'2019 ዓ'ም 🙏 መምህር ኤፍሬም ምናለ🙏

ሕይወት
ሕይወት
Open In TikTok:
Region: SA
Monday 21 September 2026 21:23:36 GMT
522
48
3
3

Music

Download

Comments

eyesuskrstos7
ሃይሚ ዘክርስቶስ✝️🕊 :
እግዚአብሔር ልቦና ይስጠን🙏😌
2026-09-22 04:40:09
1
user599327986282
እማምላክ እናቴ አንች ጠብቂኝ :
አቤቱ አምላካችን ሆይ እንደሀፂያታችን ብዛት ሣይሆን እንደቸርነትህ ይቅር በለን 🙏🙏🙏🙏🙏
2026-09-22 18:22:55
0
To see more videos from user @weleteabew1, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About