@ayuzehabesha: 📣የኤስ.ቲ.ኤስ (STS) ቅድመ-ክፍያ ቆጣሪ የፍጆታ ሂሳብ እንዲጨምር የሚያደርጉ ሁኔታዎች የኤስ.ቲ.ኤስ (STS) ቅድመ-ክፍያ ቆጣሪዎች የኃይል ፍጆታን በትክክል የሚመዘግቡ ሲሆን፣ የፍጆታ ሂሳብዎ በፍጥነት እንዲጨምር የሚያደርጉ ዋና ዋና ምክንያቶች የሚከተሉት ሊሆኑ ይችላሉ፡- ✅ከፍተኛ ኃይል የሚጠቀሙ የቤት ውስጥ እቃዎች ➡️እንደ ውሃ ማሞቂያ (Boiler)፣ የኤሌክትሪክ ምድጃ (Stove)፣ ብረት እና ማቀዝቀዣ (Refrigerator) የመሳሰሉ መሳሪያዎች በብዛት ወይም ያለ አግባብ ስራ ላይ መዋል ከፍተኛ መጠን ያለው ኪሎዋት ሰዓት (kWh) ስለሚፈጁ ቶከኑን በፍጥነት ያቃጥሉታል። ✅የቤት ውስጥ መስመር ዝርጋታ ችግሮች እና የኃይል ፍሳሽ (Wiring & Leakage) ➡️ድብቅ የኃይል ፍሳሽ (Electrical Leakage): የዝርጋታ ገመዶች አሮጌ ሲሆኑ፣ እርጥበት ሲያጋጥማቸው ወይም ጥራት የሌላቸው ሲሆኑ ኃይል ወደ ግድግዳ ወይም መሬት ሊፈስ ይችላል፤ ቆጣሪው ይህንን ፍሳሽ እንደ ትክክለኛ ፍጆታ ቆጥሮ ቶከን ያስጨርሳል። 👉ቀጭን ገመዶች እና ልቅ ማያያዣዎች: ለከፍተኛ ኃይል እቃዎች አነስተኛ ገመድ መጠቀም ወይም ልቅ ግንኙነቶች መኖር የኃይል ብክነትን ይፈጥራሉ። ✅የኤሌክትሪክ መጠቀሚያ ቁሳቁሶች ዕድሜ እና ብልሽት ➡️ዕድሜያቸው የገፋ ወይም ጥገና የሚያስፈልጋቸው እቃዎች (ለምሳሌ ሞተራቸው ያለማቋረጥ የሚሰራ ፍሪጅ) መደበኛ ከሚገባው በላይ ኃይል ይጠቀማሉ። ✅ በተጠባበቂያ ሁኔታ (Standby Mode) የሚቆዩ እቃዎች ➡️ቴሌቪዥኖች፣ ዲኮደሮች እና የኃይል መሙያ (Charger) ኬብሎች ጥቅም ላይ በማይውሉበት ጊዜ ሙሉ በሙሉ ከሶኬት ሳይነቀሉ በሪሞት ሲጠፉ (Standby) የተወሰነ ኃይል መጠቀማቸውን ይቀጥላሉ። ውድ ደንበኞቻችን ከላይ የተዘረዘሩትን የፍጆታ ሂሳብ ሊጨምሩ የሚችሉ ሁኔዎችን በማስወገድ የፍጆታ ሂሳብዎ መቀነስ ይችላሉ፡፡ያልተለመደ ጭማሪ ካሳየ የኤሌክትሪክ መጠቀሚያ ቁሳቁሶችን የኃይል አጠቃቀም ያሻሽሉና ለውጥ ካልመጣ የቤት ውስጥ መስመር ዝርጋታ ችግሮችን ይፈትሹ፡፡ #SmartMeters #EnergyManagement #EnergyEfficiency #EthiopianElectricUtility

Ayu Zehabesha- አዩዘሀበሻ
Ayu Zehabesha- አዩዘሀበሻ
Open In TikTok:
Region: ET
Tuesday 22 September 2026 13:19:29 GMT
12590
224
4
54

Music

Download

Comments

gebremariambirhan4
Gebremariam Birhan :
ኮንታክት ሲያደርግ ቆጣሪው የማይመልሰው ለምንድንነው
2026-09-23 06:59:55
0
adane.bareyaw
Adane Bareyaw :
መፍቴውን ንገረን
2026-09-22 22:41:37
0
sssggg706
Sgc1 :
🥰🥰🥰
2026-09-23 14:33:25
0
To see more videos from user @ayuzehabesha, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About