@aureon.homes: 🚨 ቤት ሊገዙ ነው? የካርታውን ሰነድ ከማመንዎ በፊት ይህን ያድርጉ! አንድ ሰው የካርታ ሰነድ አሳይቶዎት፣ “ይሄ እውነተኛ ነው” ብሎ ብቻ አይተማመኑ። በአዲስ አበባ የካርታ ሰነድ ትክክለኛነትን በኦንላይን ማረጋገጥ ይችላሉ። 🔎 እንዴት? 1️⃣ ወደofficial የአዲስ አበባ መሬት አስተዳደር ድረገጽ ይግቡ። https://www.addisland.gov.et/am-et/ 2️⃣ የማረጋገጫ/ፍለጋ አገልግሎቱን ይፈልጉ። 3️⃣ በሰነዱ ላይ ያለውን QR Code ይስካን ያድርጉ። ወይም የንብረት ቁጥር ወይም የካርታ ቁጥር በእጅ ያስገቡ። 4️⃣ የሚመጣውን መረጃ ከሰነዱ ጋር ያነጻጽሩ። የምዝገባ ሁኔታ፣ የመሬት ደረጃ እና ተያያዥ የንብረት መረጃ ሊታይ ይችላል። ⚠️ ግን አንድ ነገር አትርሱ! QR Code መኖሩ ብቻ ሰነዱ እውነተኛ መሆኑን አያረጋግጥም። የሚያሳየውን መረጃ ከሰነዱ፣ ከሻጩ የባለቤትነት መረጃ እና ከሌሎች የንብረቱ ሰነዶች ጋር ማመሳከር አለብዎት። 💰 ከፍተኛ ገንዘብ ከመክፈልዎ በፊት… ሰነዱን ያረጋግጡ። ባለቤቱን ያረጋግጡ። የንብረቱን ሁኔታ ያረጋግጡ። የሕግ ጉዳይ ካለ ያረጋግጡ። ቤት ሲገዙ በቤቱ ውበት ብቻ አትደነቁ። በሰነዱ ላይ ይመርመሩ። 📌 ይህን መረጃ SAVE ያድርጉ። ቤት ለመግዛት ለሚያስብ ሰውም SHARE ያድርጉ። ለተጨማሪ ተግባራዊ የኢትዮጵያ ሪል እስቴት መረጃ፣ 09 79 69 55 23
Aureon Homes
Region: ET
Tuesday 22 September 2026 13:36:23 GMT
Music
Download
Comments
AbeniM.S :
sheger city kehones
2026-09-23 09:47:15
3
Sanyii Addisu :
የቱሉ ዲምቱ ይቻላል?
2026-09-23 18:24:05
1
Scarface :
aprtement QR code yelewem
2026-09-22 16:36:41
2
Nincho :
እውነት ነው ተባረኩ🙏
2026-09-23 13:11:30
1
እምይዬ እናቴ ልቤ ተሠበረልሽኮ😭😭😭 :
እናመሠግናለን ማህበራዊ ሚዲያ በዚህ መልኩ ስለ እውነት ሲነገር ደስ ይላል
2026-09-22 20:20:43
3
Kidus Joseph :
Er sawye😁😁😁
2026-09-22 21:35:05
1
keita :
ኦዲት ያልተደረገ የማህበር ቤትንስ ቼክ ማድረግ ይቻላል..?
2026-09-23 19:46:43
0
madiba 1 :
lela klls
2026-09-23 08:58:25
0
To see more videos from user @aureon.homes, please go to the Tikwm
homepage.