@aschu_graphics: አከራካሪው ሞክሼ ፊደላትና አጠቃቀማቸው 🎯ሞክሼ ፊደላት እና ልዩነታቸው✨ ✍️ሞክሼ ፊደላት የሚባሉት ሀ' ሐ' ኀ ሠ' ሰ አ' ዐ ጸ' ፀ ናቸው፡፡ እነዚህ ፊደላት የድምፅም' የቅርጽም' የትርጉምም ልዩነት አላቸው👇 🔥የድምፅ ልዩነት:- 🟢ሀ-ሐ-ኀ ሀ - ላልቶ ይነበባል ሐ - ጠብቆ ይነበባል ኀ - በጉሮሮ ይነበባል 🟡ሠ/ሰ ሠ - እንደ ሸ ይነበብ ነበር ሰ - በጥርስ ይነበብ ነበር ለምሳሌ፡- ንጉሥ ብለን ነጋሽ እንላለን፡፡ ይህም ሠ እንደ ሸ ይነበብ እንደ ነበር ያስረዳል፡፡ 🔴 አ/ዐ አ - ላልቶ ይነበባል ዐ - ጠብቆ ይነበባል 🟢ጸ/ፀ ጸ - የራሱን ድምፅ ይይዛል ፀ - እንደ ጠ ይነበብ ነበር ለምሳሌ፡- ፀሐይ የሚለውን ቃል ጠሐይ ብለው የሚጽፉና የሚያነቡ አሉ፡፡ 🔥🔥የትርጉም ልዩነት✍️ 📍 ንሰሃ - ትርጉም የለሽ ንሰሐ - ፀፀት/ሐዘን ንስኃ - ክርፋት/ግማት 📍ድኅነት - መዳን/መፈወስ 📍ድህነት - ማጣት/መቸገር 📍ሐበ - ኮሶ 📍ኀበ - ወደ 📍ሠረቀ = ወጣ 📍ሰረቀ = ሰረቀ(የሰው ንብረት ወሰደ) 📍አመት = አገልጋይ 📍ዓመት = ዘመን 📍ሰዐለ = ስዕል ሳለ 📍ሰአለ = ለመነ 📍መሀረ = አስተማረ 📍መሐረ = ይቅር አለ 📍ኀለየ = አመሰገነ 📍ሐለየ = አሰበ 📍ፈጸመ = ጨረሰ 📍ፈፀመ = ነጨ 📍ማኅሌት = ማመስገን 📍ማሕሌት = ማሰብ በተጨማሪም ልክ እንደ እንግሊዝኛው ቋንቋ በድምጸት ተገናኝተው በትርጉም እንደሚለያዩ ቃላት ሁሉ ለምሳሌ 📍know, now, 📍write, right, 📍watt, what, እነዚህ የኢትዮጵያ ፊደላትም ተመሳሳይ ድምጸት ቢኖራቸውም በግዕዝ ቋንቋ ሁሉም የየራሳቸው ትርጉም አላቸው። ለምሳሌ በግዕዝ ቋንቋ 📍"መሀሪ = አስተማሪ" ፤ 📍"መሐሪ = ይቅር ባይ" ፤ 📍ዓመት = የዘመን 📍"አመት = ባሪያ፣ አገልጋይ፣ #አማርኛ #ሞክሼ_ፊደላት #aschugraphics #promo
Aschu graphics አስቹ
Region: ET
Wednesday 23 September 2026 07:51:50 GMT
Music
Download
Comments
𝑠𝑜𝑙𝑜𝑚𝑜𝑛፯ :
ማስተካከያ
👇
እሳቱ "ሰ"
ንጉሡ "ሠ"
ፀሐዩ "ፀ"
ሌላው ትክክል ነው እናመሰግናለን🙏
2026-09-23 10:02:08
21
Mohammed Abdu :
yet temrachhut new weys kager endewetan tekeyrual😅
2026-09-23 13:23:03
1
ዘ ብሔረ ኢትዮጵያ :
እሳቱ ሰ ይሄ ነው
ንጉሡ ሠ ነው ይሄ
2026-09-23 09:39:46
6
ሶፎር ሚድያ :
ተሳስቷልያስተካክሉት
2026-09-23 11:27:56
1
አረንዛው ቋሪቴ :
ሰ ውሸት
2026-09-23 17:34:27
1
ደሜ ዘጽንዐ ተዋሕዶ :
ፀሐይ, ሠ..ንጉሱ, ሰ...እሳቱ ቢሆን🙏🙏🙏
2026-09-23 15:19:52
1
M/R TSIGE SITOTAW :
ንጉሡ ሠ እና እሳቱ ሰ ይቀያየር
2026-09-23 13:08:00
2
naoszewdie :
ሰ አናሠ ተቀያይሯል
2026-09-23 15:37:26
1
ሰው ሞልቶ ሰው ጠፋ :
ቀልድ እንዳይሆን ምክንያትም እውነት ት.ት አድርገን ነው ምንወስደው ስለማናውቀው[Pray]
2026-09-23 17:05:32
1
I HOPE :
ንጉሡ ሠ ነው
እሳቱ ሰ ነው
2026-09-23 16:49:20
1
Aynalem D :
ዋሽንቱን አጥፉዉ
2026-09-23 10:06:52
1
Wondimu tamiru :
ኧረ እባካችሁ ።🤔
ንጉሡ 'ሠ'
እሳቱ 'ሰ'
ፀሐዩ 'ፀ'
2026-09-23 11:15:07
1
Selamawit Wondie :
@Selamawit Wondie:ፀጋዬ ሳይሆን ፀሑዩ ፀ ነው ንጉሡ ደግሞ በዚህኛው ነው የሚጻፈው ስ ይኸኛው እሳቱ ሰ ነው የባለው
2026-09-23 08:11:37
1
የዘለቀ ልጅ 444 :
ሰ ን አቀያይረኸዋል
2026-09-23 15:09:27
1
meko :
እኔ ግን የት ሄጄ ነው ጓደኞቼ እነዚህ ፊደላትን ስንማር የሆነ ያለፈኝ ትምህርትማ አለ ምንም ነው ልዩነታቸውን ማላውቃቸው ኸረ ባካችሁ በደንብ አስተምሩኝ የነዚህ ብቻ አይደለም የኔ ችግር ዲእና ድ አጠቃቀም ራሱ ግራ ያጋባኛል 🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-09-23 13:26:11
1
wase 32 :
በዚህልክ ስለፊደል አላውቅም ነበር
2026-09-23 15:21:49
1
ምህረት መላኩ :
ሠ እና ሰ?
2026-09-23 15:57:15
1
habtomghaweriat :
እሳቱ ሠ አላለም
2026-09-23 17:50:36
0
Fish :
"ኻ " ? ይሄንስ ማን እንበለው?
2026-09-23 18:56:04
1
ማርያም አማላጄ :
ፀሀዩ ፀ
2026-09-23 11:27:34
1
melegnawu :
አሳሳች ንጉሡ ሠ እሳቱ ሰ
2026-09-23 17:58:33
1
tefera016 :
Nic
2026-09-23 11:46:08
1
Arega :
👍
2026-09-23 11:28:52
1
To see more videos from user @aschu_graphics, please go to the Tikwm
homepage.