@kasget61: ቅዱስ ሚካኤል የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ!!! በአዲሱ ዓመት ቅዱስ ሚካኤል የጎደለንን ይሙላልን፣ከክፉ ነገር ከልሎ የልባችንን መልካም መሻት ይፈጽምልን🙏 በጾርዓ ከተማ የሚኖር፣ ከዳን ወገን የሆነና ሚስቱም መካን የነበረች ማኑሄ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፡፡ የእግዚአብሔር መልአክም ለሴቲቱ ተገልጦ “እነሆ ትጸንሻለሽ፤ አሁንም ተጠንቀቂ፤ የወይን ጠጅን የሚያሰክርም ነገር አትጠጪ፥ ርኩስም ነገር አትብዪ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ልጁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር የተለየ ናዝራዊ ይሆናልና በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፤ እርሱም እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያን እጅ ማዳን ይጀምራል” አላት። ሴቲቱም ለባልዋ የሆነውን ሁሉ ነገረችው፡፡ ማኑሄም የተላከው ሰው ዳግመኛ ወደኛ ይምጣ፤ ብሎ ወደ እግዚአብሔር ለመነ። እግዚአብሔርም የማኑሄን ድምፅ ሰማ፤ መልአኩም ሴቲቱ በእርሻ ውስጥ ተቀምጣ ሳለች እንደገና ተገለጠላት፤ ማኑሄ ግን አልነበረም። ሴቲቱም ፈጥና ሮጠች፤ ባልዋንም ጠራችው። ማኑሄም “ከዚህች ሴት ጋር የተነጋገርህ አንተ ነህን? ቃልህ በደረሰ ጊዜ የልጁ ሥርዓት ምንድን ነው? አለው። መልአኩም ማኑሄን “ሴቲቱ ከነገርኋት ሁሉ ትጠንቀቅ፣ በማለት ለሴቲቱ የነገራትን ደገመለት፡፡ ማኑሔም “የፍየል ጠቦት እስክናዘጋጅልህ ድረስ፤ እባክህ ቆይ” አለው። መልአኩም የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ማዘጋጀት ብትወድድ ለእግዚአብሔር አቅርበው” አለው። ማኑሄም “ነገርህ በደረሰ ጊዜ እንድናከብርህ ስምህ ማን ነው?” አለው፡፡ መልአኩ “ስሜ ድንቅ ነውና ለምን ትጠይቃለህ?” ብሎ መለሰለት። ማኑሄም የፍየሉን ጠቦትና የእህሉን ቍርባን ወስዶ በድንጋይ ላይ ለእግዚአብሔር አቀረበው። መልአኩም በመሠዊያው ነበልባል ውስጥ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ማኑሄና ሚስቱም በግምባራቸው በምድር ተደፉ። ማኑሄም የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን አወቀ። ሶምሶን ከተወለደ በኋላም የእግዚአብሔርም መንፈስ በጾርዓና በኤሽታኦል መካከል ባለው በዳን ሰፈር ውስጥ ሊያነቃቃው ጀመረ። ይህ ሶምሶንና ወላጆቹን የረዳው ኃያሉ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ ታላቁ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ዛሬም ገዳማውያንን በተጋድሏቸው ሁሉ እየተራዳ አብሯቸው ይኖራል፡፡ ስለ ክርስቶስ ፍቅር ዓለምን ትተው ወጥተዋልና ጸሎታቸው ኃይልን ታደርጋለች፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡ #የኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_ሃይማኖት #መዝሙር_ዘኦርቶዶክስ_ተዋህዶ #ኦርቶዶክስ #መዝሙር #ሚካኤል_ሊቀ_መላእክት👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
ⓀⒶⓈⒼⒺⓉ
Region: ET
Friday 25 September 2026 10:40:07 GMT
Music
Download
Comments
solodan mak :
🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-09-25 11:56:43
0
To see more videos from user @kasget61, please go to the Tikwm
homepage.