@woreda13.media: የትውልድ ግንባታን ያማከለ የዴይኬር አገልግሎት የከተማ አስተዳደሩ ለትውልድ ግንባታ በሚያደርገው ሥራ ላይ ሕፃናትን በእንክብካቤ፣ በትምህርትና በአግባቡ በማሳደግ የሚከናወነው የማህበረሰብ ዴይኬር አገልግሎት ከፍተኛ ቦታ እንዳለው ተገለጸ። አገልግሎቱ የወቅቱን የከተማ ነዋሪዎች ፍላጎት ከማሟላት ባለፈ በጤናማ፣ በተማረና በኃላፊነት የተሞላ ትውልድ ግንባታ ላይ የሚያተኩር ሥራ መሆኑ ተመላክቷል። በተለይም የዴይኬር አገልግሎት ወላጆች የሥራ እና የቤተሰብ ኃላፊነታቸውን በሚገባ እንዲወጡ የሚያግዝ ሲሆን፣ ሕፃናትም በተገቢው እንክብካቤና አስተዳደግ ውስጥ እንዲያድጉ ዕድል ይፈጥራል። በዚህም አገልግሎቱ ለአሁኑ ትውልድ ጥቅም ከመስጠት ባለፈ ለመጪው ትውልድ ጠንካራ መሠረት በመጣል ረገድ ያለው ሚና የጎላ ነው። በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 አስተዳደር በሚገኙ ዴይኬሮችም ነዋሪዎች የሚሰጠውን አገልግሎት ተጠቃሚ እየሆኑ ይገኛሉ። አገልግሎቱን ያገኙ የከተማዋ ነዋሪዎች ከሚዲያ ጋር ባደረጉት ቆይታም የዴይኬሮቹ አገልግሎት ለልጆቻቸው እንክብካቤና አስተዳደግ ያለውን ጠቀሜታ በመግለጽ ያገኙትን ተሞክሮ አካፍለዋል። ተጠቃሚዎቹ የዴይኬር አገልግሎቱ የሕፃናትን እንክብካቤ በማሻሻል፣ ወላጆችን በሥራቸው ላይ በማበረታታትና ቤተሰቦችን በማገዝ የሚታይ ለውጥ እያመጣ መሆኑን መስክረዋል። ከዚህ በተጨማሪም ሕፃናት በአካባቢያቸው በተገቢ እንክብካቤና በመማር የሚያሳልፉበት ሁኔታ መፈጠሩ ለቤተሰቦች የሚሰጠውን ድጋፍ አጉልቶ ገልጸዋል። የዴይኬር አገልግሎቱ በአሁኑ ጊዜ ለከተማዋ ነዋሪዎች ጠቃሚ አገልግሎት ከመሆን ባለፈ በረጅም ጊዜ የትውልድ ግንባታ ላይ የሚያተኩር ሥራ እንደሆነ ተጠቁሟል። አዲስ አበባ በትውልድ ግንባታ ዙሪያ እያከናወነች ላለው ሥራ እውቅና ማግኘቷም የሥራውን አቅጣጫና ትኩረት የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል። #bolew13pp

Woreda13 Media
Woreda13 Media
Open In TikTok:
Region: ET
Friday 25 September 2026 12:02:57 GMT
4815
194
13
28

Music

Download

Comments

kin2409
kin :
እጅግ እናመሠግናለን ወረዳ 13 ተመስክሮላችኋል
2026-09-26 03:37:56
0
kamilmohammed_
Kamil Mohammed :
Huge appreciation to bole Wareda 13 leaders for the amazing work of taking care of babies for people! in Addis Ababa Caring for a child is hard, selfless work, and doing it for others shows true kindness, patience, and responsibility. You're not just watching babies you're supporting whole families and giving parents peace of mind. This is a beautiful example for others to follow. Thank you, Wareda 13, for your love and dedication. You are truly appreciated! 🙏❤️👏
2026-09-25 19:13:55
0
yibeltalyalew881
Yibeltal Yalew :
ቦሌ ወረዳ 13 ምርጥ ተሞክሮ በርቱ።
2026-09-27 10:39:29
0
yeshigxdfcl
yeshi :
አንዲነን
2026-09-25 13:30:31
0
wwwnnnlyy
ስለሰዉ ስለሰው ቀድጀ ልልበሰው???? :
enamesegenalen
2026-09-25 12:14:07
0
user55739872292258
hareg :
እናመስግአለን
2026-09-25 17:57:21
0
almi3969
almi :
2026-09-30 12:37:26
0
wwwnnnlyy
ስለሰዉ ስለሰው ቀድጀ ልልበሰው???? :
lemeseganache
2026-09-25 12:14:19
0
signorita80
signorita80 :
✌️✌️✌️✌️
2026-10-04 14:22:31
0
kbsha14
kbsha :
😳😳😳
2026-09-30 13:03:39
0
fetiii131
fetiii :
🙏🙏🙏
2026-09-25 13:08:24
0
bereka33
zehra zahra :
🥰🥰🥰🥰🥰
2026-10-05 13:09:09
0
To see more videos from user @woreda13.media, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About