@sergioramos.fan.52381:

sergioramos
sergioramos
Open In TikTok:
Region: US
Friday 25 September 2026 12:30:48 GMT
354
18
0
0

Music

Download

Comments

There are no more comments for this video.
To see more videos from user @sergioramos.fan.52381, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

#ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ! ያጀማል መዝሃረል ጀማል! የዳንዮች ማሳ ተቅዋ ተዘርቶ ዒልም የበቀለበት፣ ዙህድ ተወቅቶ መደድና ሙሐባ የታፈሰበት ነው። የጌታው ሰይድ ዳንዩ ሳኒ መዝሃረል ጀማል ዓቅሌን ያሳጣኛል። ጅስሜን ያነደኛል። ከ’ነ ሩኄ አክንፎ ዓለማቱን ያስጠውፈኛል። ምንኛ የጠለቀ፣ ለጉድ የረቀቀ፣ የራቀ፣ የመጠቀ አሞጋገስ ነው ያሰኘኛል። በእንዴት ያለ የሹሁድ መሐዲር ቢጣዱ ነው እንዲህ ግለው ያጋሉት ያስብለኛል። ከዓሪፎቹ የመደድ ፎሌ ለጨለፈ፣ ከእጃቸው ፉት ላለ ቢሆን እንጂ ማዕናው እንዲሁ የሚዘልቅም አይደል። አጀብ እነሱ! መገን ሰዎቹ! ጌቶቹ  لَقَدْ مَنَّ اللَّهُ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ إِذْ بَعَثَ فِيهِمْ رَسُولًا ያለውን የጌትዬውን ከላም ጠልቀውበታል። መቸም ለጋሱ ጌታ በሰጠው ኒዕማ ሁላ ኸልቁን የሚይዝ ቢሆን ኖሮ ለሚዛንም ለፍርድም አንደርስም ነበር። ታዲያ ለሙእሚኖች ከዋለው ውለታ ሁሉ
#ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ! ያጀማል መዝሃረል ጀማል! የዳንዮች ማሳ ተቅዋ ተዘርቶ ዒልም የበቀለበት፣ ዙህድ ተወቅቶ መደድና ሙሐባ የታፈሰበት ነው። የጌታው ሰይድ ዳንዩ ሳኒ መዝሃረል ጀማል ዓቅሌን ያሳጣኛል። ጅስሜን ያነደኛል። ከ’ነ ሩኄ አክንፎ ዓለማቱን ያስጠውፈኛል። ምንኛ የጠለቀ፣ ለጉድ የረቀቀ፣ የራቀ፣ የመጠቀ አሞጋገስ ነው ያሰኘኛል። በእንዴት ያለ የሹሁድ መሐዲር ቢጣዱ ነው እንዲህ ግለው ያጋሉት ያስብለኛል። ከዓሪፎቹ የመደድ ፎሌ ለጨለፈ፣ ከእጃቸው ፉት ላለ ቢሆን እንጂ ማዕናው እንዲሁ የሚዘልቅም አይደል። አጀብ እነሱ! መገን ሰዎቹ! ጌቶቹ لَقَدْ مَنَّ اللَّهُ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ إِذْ بَعَثَ فِيهِمْ رَسُولًا ያለውን የጌትዬውን ከላም ጠልቀውበታል። መቸም ለጋሱ ጌታ በሰጠው ኒዕማ ሁላ ኸልቁን የሚይዝ ቢሆን ኖሮ ለሚዛንም ለፍርድም አንደርስም ነበር። ታዲያ ለሙእሚኖች ከዋለው ውለታ ሁሉ "ይሄንን ሰጠኋችሁ!" ብሎ ሊመፃደቅበት ያገነነው ሰይዳችንን ነው። ለዚህም ነው ዳንዩ ሳኒ ‹‹ أَصْبَغَ عَلَيْنَا النِّعَمْ ... بِبَعْثِ النَّبِيِّ الْكَرِيمْ ›› በማለት መቀኘታቸው። ቁጥርና ዲካን አልፎ፣ ሃድና ድንበርን ጥሶ ነቢን እንደሰጠን ያወሳሉ። እንዴታ! በሰይዲ መዝለቅ የምድር መቅሰፍቶች ተሷርፈዋል። በስማቸው በረካ ጭንቅ እና ሀዘን ገለል ይላል። በውዴታቸው ሲር ሙእሚን ያድጋል። ከፀጋዎች ሁሉ የተላቁ ለመሆናቸው ያረገደላቸው የሶሐባ አረዳ እማኝ ነው። ከፊሉ ጥቂት ሲርቅ በናፍቆት ይኮሰምናል። ገሚሱ እያያቸው በመውደድ ይሰምጣል። እልፍ ያሉት ደግሞ ደግሞ ለአብሮነታቸው የመለክ ነጋሪት ያስጎስማሉ። የነዚያ እንቁዎች ፋና ለኛም መተላለፉ፣ ኧረ ልቆ ደምቆ ማብራቱ በቀዲሞቹ ታይቷል። ሐበሻ ቀበሌ ለዚህ ዋቢ ነው። ሳንዩ በ መዝሃረል ጀማል ሲገማሸሩ "ቁሙ ነቢን ለማሞገስ!" እያሉ ወዳጅን ይጣራሉ። የሀገሬ አምራሪ ለማኝ "እስቲ አናዱኝማ!" ይላል ሃጃ ጠንቶበት ለዱዓ ሲቆም። ፍቅርም እንዲሁ አቋቋሚ ይከጅላል። "እንዴትስ አላወድሳቸው!?" ሲሉ ለደህኔ ምላሽ ያስቀመጡ ይመስላሉ። እያንዳንዱ ስንኝ ባሕር ሁኖ ሚስጥሩ ከመራቁ ጋር ጭራሽ በአንዳንዱ ላይ የጘይብን ያህል ይርቁበታል። كَيْفَ لاَ وَهُوَ نُورُ النُّورِ، وَنُورُ الحِجَابِ الأَعْظَمِ "የብርሃን ብርሃን" ብለው አሞካሿቸው። ጌትዬው ለካኢናቱ ለይቶ ያደመቃቸው ኑር መሆናቸው ታይቷቸው ነው። ቁርአኑም "ሲራጀን ሙኒራ!"ማለቱን አይተናል። ቁርአን ባሕር፣ ሳዳቶቹ ምንጭም ቀዛፊም ሁነው በአላህ መንጃ ፈቃድ ፈሰሱበት። ሰባ ሺው ግርዶ የጋረደው ኑር፣ ለጥቆም የራሱ የሒጃቡም ኑር መሆናቸውን በዚሁ ስንኝ ወቀሩት። ያዬ እንጂ ሚስጥሩን ማን አወቀ። እንደው በደፈናው "እንዴታ የሚስጥሩ ሚስጥር፣ የረቂቁ ዓለም ሚስጥር" ያሉት ሲሩ ቢጠናቸው ነው። ማዕናው ቢርቃቸው ነው ጠልቆ እንደሚማታ የባህር ወጀብ መስመጣቸውን «كَمَوْجِ الْبَحْرِ الْمُلْتَطِمِ» ያሉት። يَا أَيُّهَا الْحِجَابُ الْجَلاَلِ ... لَأَنْتَ رُكْنٌ لاَ يُهْدَمُ ገና ቀድሞ በአዘል ኑራቸው ከተኸለቀችባት ቅፅበት ጀምሮ ዓለም እስክትፈርስ ድረስ የማይናድ ምሶሶ፣ የማይናወጥ ተራራ፣ የአላህ አርማ ችካል ተደርገዋል። የወደዳቸው ጌታ በየዘመናቱ ስለ ክብራቸው የሚዋደቁ ደጎች ኸልቆላቸዋል። መንገዳቸውንም ጠብቀው የሚያስጠብቁ አካቢሮች ሹሞላቸዋል። ከዚያማ በኋላ غُصْنَا فِي الْبَحْرِ الطَّوِيلِ الْقَاعِرِ ... لَكِنْ مَا نَدْرِي لَهُ طَرَفًا ያሉትን ይዘን ብንነሳ ጥልቅ የሆነ ባሕር ውስጥ አገኘናቸው። ላኪን መድረሻ እና ማብቂያ ጫፉን ሲያጡት የተመለሱ ይመስል «يَا جَمَالْ مَظْهَرُ الْجَمَالْ» በማለት እዛው ሁነው ከቀኝ ወደ ግራ አረገዱበት፤ ሰማይ እና ምድር መሃል አረገረጉበት፤ በጀማልም በጀላልም ዋለሉበት፤ ከማላውን ዋኙበት፣ ኑሩን ደመቁበት፣ በሙልክ ሰጥመው በመለኩት ዳኑበት። መገን ዳና ኧረ እኛም እንዳን! የመዝሃረል ጀማል ነገር እንደዋዛ የሚቋጭ አይደለምና ሳምንት እንቀጥለዋለን ቢኢዝኒላሂል ከሪም! أَيُّهَا النُّورُ المَقَدَّمُ ... عَلَيْكَ الصَّلاَةُ وَالسَّلاَمُ وَعَلَى آلِكَ الكِرَامِ ... وَالصَّحْبِ أُولِي المَكَارِمِ #ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ! አሏሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!💚💚💚 #ለሌሎች_እንዲደርስ_ሼር #የእዉነት_ድምፅ @ነጃሺ ሚዲያ

About