@enduplus: ዝምታዋ ገፋኝ አራቀኝ ከጎኗ፣ ፍቅሯን ለመናገር ቢዘጋ ልሳኗ፣ ፡ ባንኳኳው ደጃፏን ሚከፍትልኝ ባጣ፣ ከጎረቤት ዞርኩኝ ሚሰማኝ ከመጣ፣ ፡ ቃላትን ቀምሬ አስውቤ አሽቀርቅሬ፣ ዝምታ መልስ ሆነ ፍቅሬን በማብሰሬ፣ የውስጤን መከፋት በውስጤ ቋጥሬ፣ ለመሄድ ተነሳው ወደ መራኝ እግሬ፣ ፡ ወድሻለው ስላት መውደዷን ባትነግረኝ፣ ከሌላ እንድከጅል ዝምታዋ ገፋኝ፣ ፡ ነግሪያት ነበረ..... ልክ እንደፏፏቴ ድምፄን ብዙ አድርጌ፣ በበራቸው ደጃፍ አንገቴን አስግጌ፣ አባቷም ዘልፈውኝ ብለውኝ ባለጌ፣ አሳዲጊም የለህ መረን የልጅ ዋልጌ፣ ፡ እያሉኝ ሰምታለች እኔም ሰምቻለው፣ ፍቅሬን ተናገርኩኝ ግን ከቁብ ሳላየው፣ ፡ እሷ ግን አድምጣኝ አንዳችም አላለች፣ የኔን ማፍቀር ሰምታ ማፍቀሯን ደበቀች፣ አስር ጊዜ ሰምታ እንዳልሰማ ሆነች፣ ፣ ዝምታዋ ቢያል ደጋግሞ አስፈራኝ፣ አታፈቅረኝ ብዬ ልርቃት ወሰንኩኝ፣ ፡ በርሃ አቋርጬ ከደጋው ስገባ፣ ወዴት ነህ አለችኝ ስለኔ አስባ፣ ፡ የብርዱ ወር አልፎ ስሟሟቅ ስድላላ፣ ትከተለኝ ጀመር በሄድኩበት ሁላ፣ ፡ እወድህ ነበረ በድንገት ብትለኝ፣ የመፍራቷን ሚስጢር ደርሳ ብታዋየኝ፣ ያን ፍቅሬን አስቤ እንባ ተናነቀኝ፣ ግን ምንላርግ ርቄያለው ዳግም ላትመልሰኝ፣ ልቧ እየፈለገ ዝምታዋ ገፋኝ፡፡ ------------------------------ #fyp #foruyou #creatorsearchinsights

ስቃዬ 💔
ስቃዬ 💔
Open In TikTok:
Region: ET
Sunday 27 September 2026 11:48:29 GMT
2039
200
9
34

Music

Download

Comments

ggoytom
goytom ger :
wow
2026-09-28 19:08:08
0
semei370
Sami :
🥰🥰🥰
2026-09-27 18:11:29
0
abd85877
alfenur :
🥰🥰🥰
2026-09-28 20:16:47
0
lidiya.203
Lidiya :
🥰🥰🥰
2026-09-28 17:53:20
0
tame7948
M I R A C L E 💐 16 :
🥰🥰🥰
2026-09-27 18:02:49
0
mahi.love740
Mahi love :
🥰🥰🥰🥰🥰
2026-09-27 12:58:46
0
helen.abayneh
helen Abayneh :
🥰🥰🥰🥰❤️❤️❤️❤️
2026-09-27 12:33:48
0
user509907012818
ባለ ሀይባው...❤ :
🥰🥰🥰
2026-09-27 11:52:58
0
hkihkaa
ማን እንደ እነት :
👌👌👌
2026-09-29 10:05:22
0
To see more videos from user @enduplus, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About