@daily.pulse.network: የጦርነት ሜዳው ኤርትራ ይሆናል-ጄኔራል ባጫ‼️ የኤርትራ አቋም በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ ትግራይ፣ አማራ ወይም አፋር የኤርትራ የጦር ሜዳ አይሆኑም-ጄኔራል ባጫ ደበሌ‼️ የአሁኑ አካሄድ ወደ ሙሉ ጦርነት ከሄደ ጦርነቱ ወደ ኤርትራ ግዛት መግባቱ አይቀርም ሲሉ ጄኔራል ባጫ ደበሌ ከሆርን ሪቪው ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ ተናግረዋል። ይህ ተራ ንግግር ሳይሆን የወታደራዊ አመክንዮ ጉዳይ ነው ያሉት ጄኔራሉ የሌላ ሀገርን ሉዓላዊነት በተደጋጋሚ የሚፈትን መንግስት ትዕግስትም ልክ እንዳለው መረዳት አለበት ብለዋል። ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ወታደራዊ ሰው ናቸው እና ይህንን መርህ ይረዳሉ። ጦርነቱ አንዴ ከተጀመረ፣ ከቁጥጥር ውጪ ሊወጣ እንደሚችል፣የኤርትራ ግዛት ሊቀየር እንደሚችል ያውቃል ብለዋል። ኢትዮጵያ ትዕግስትን ተግባራዊ አድርጋለች ምክንያቱም ትዕግሥት ስትራቴጂካዊ ፍላጎቶቿን ለማሟላት ስለሚጠቅማት በማሰብ ነው። ይህ የአቅም ማጣት ወይም የውሳኔ እጥረት ተደርጎ ሊወሰድ አይገባም። በእኔ እሳቤ የፅምዶ መነሻ መቀሌ ወይም አስመራ ሳይሆን ካይሮ ነው ብለዋል።
DailY Pulse Press
Region: ET
Sunday 27 September 2026 16:13:32 GMT
Music
Download
Comments
There are no more comments for this video.
To see more videos from user @daily.pulse.network, please go to the Tikwm
homepage.