@yoseftesfahun588: ማንኛውም የጤና ባለሙያ ከሚከተሉት ምክንያቶች በአንዱ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ ሚኒስቴሩ ወይም ክልል ተቆጣጣሪ አካላት የሙያ ስራ ፈቃዱን ሊያግድ ይችላል፦ 1. ከሁለት ጊዜ በላይ ከሙያ ትግበራው ጋር በተያያዘ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ተግቢውን ማስተካከያ ሳያደርግ ሲቀር እንደአግባቡ ከሶስት ወር ላልበለጠ ጊዜ፤ 2. ባለሙያው በሙያው ለማገልገል ብቃት የጎደለው መሆኑ አግባብ ባለው አካል ሲረጋገጥና ሲወሰን፣ ውሳኔው የእገዳ ጊዜውን የሚያካትት ይሆናል 3. ባለሙያው በአዕምሮ ህመም ምክንያት ሙያውን በሚገባ መወጣት ካልቻለ የጤና ሁኔታው እስከሚሻሻልና በሀኪም እስኪረጋገጥ፤ 4. ሆን ብሎ የሙያውን ስነ-ምግባር በሚቃረን ሁኔታ ከተሰጠው የሙያ ስራ ወሰን ወይም የጤና ተቋም ደረጃ በላይ ሲሰራ የተገኘ እንደሆነ እንደ አግባቡ ከአንድ ዓመት ላላነሰ ከሁለት ዓመት ላልበለጠ ጊዜ፤ 5. በተሰጠው የሙያ ስራ ፈቃድ መነሻ በኃላፊነቱ በከፈተው የጤና ተቋም ውስጥ ያልተመዘገበ ወይም የሙያ ስራ ፈቃዱ የታገደበትን ወይም የተሰረዘበትን ወይም የሙያ ስራ ፈቃድ ጨርሶ የሌለውን የጤና ባለሙያ ሲያሰራ የተገኘ እንደሆነ እንደአግባቡ ከሶስት ወር ላላነሰ ከስድስት ወር ላልበለጠ ጊዜ፤ 6. ለህብረተሰብ ጤና በሚያሰጋ ሁኔታ የሙያ ብቃት ችግር ወይም የሙያ ስነምግባር ግድፈት ምክንያት ክስ በሚቀርብበት ጊዜ ሚኒስቴሩ ወይም ክልል ተቆጣጣሪ አካላት ቀርቦ ውሳኔ እስከሚያገኝ፤ 7. ባለሙያው በሙያ ስነ-ምግባር ግድፈት ምክንያት አግባብ ባለው አካል እንዲታገድ ሲወሰን፣ ውሳኔው የእገዳ ጊዜውን የሚያካትት ይሆናል 8. ለስረዛ የሚያበቁ ግድፈቶች ሲፈጠሩ ጉዳዩ ለፍርድ ቤት ወይም ሚኒስቴሩ ወይም ክልል ተቆጣጣሪ አካላት ቀርቦ ውሳኔ እስከሚያገኝ፤ 9. ከጤና ባለሙያነቱ በታገደበት ወቅት ህገ-ወጥ ጥቅም ለማግኘት ሲል የእገዳ ውሳኔውን ጥሶ የጤና ባለሙያነት አገልግሎት ሲሰጥ የተገኘ እንደሆነ ለተጨማሪ አንድ ዓመት ሊታገድ ይችላል።
CPD Maker & Consultant
Region: ET
Tuesday 29 September 2026 17:44:18 GMT
Music
Download
Comments
There are no more comments for this video.
To see more videos from user @yoseftesfahun588, please go to the Tikwm
homepage.