@414yayo: Chicago night ! #carlife #audi #audia6 #nightcruise #A6

414yayo
414yayo
Open In TikTok:
Region: US
Wednesday 30 September 2026 00:10:41 GMT
538
24
4
0

Music

Download

Comments

To see more videos from user @414yayo, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos

~
~"አልተሰናዳሁም"...ዘፈኑን ስሰማ ወደማላውቀው አለም፤ ፍቅር ፣ መከዳት ፣ ከዛም ጉዳትና ስቃይ ከቴዎድሮስ ታደሰ ድምፅ ጋር አብሬ እነጉዳለሁ ~ዘፈኑ በግጥም በዜማ በድምፅና በቅንብር ፍፁም የሆነ ዘፈን ነው ለኔ! ~ዘፈኑ በውስጡ የአንድን ሰው ያልወጣለትን ያላለቀን ፍቅር...በአንድ ሳይድ ብቻ የቀረን ስሜትና ጉዳት ይናገራል! ~እስከመጨረሻው አብረን ነን እያለ በፍቅር መንገድ ውስጥ ጉዞ አስጀምሮን በፍቅር ስንወድቅና ስንያዝ ድንገት ለሚሸሽ ሰው ነው ዘፈኑ ~ለብዙ የጠበቅነው ፍቅር ሜዳ ላይ ሲቀር ያኔ በፍቅርና በፀፀት ውስጥ ሽንፈትን ስንጎናፀፍ ..ጋደም ብለን ወይም በተምስጦ የምንሰማው ዘፈን ነው! ~በአጠቃላይ ዘፈኑ ስንሰማው በመበደል ፣ በፀፀት፣ በመከዳትና በመናፈቅ ስሜት ውስጥ ሁነን አብረን ከዘፈኑ ጋር እንሰምጣለን! ቴዎድሮስ ታደሰ ~”አልተሰናዳሁም”❤️ ቴዎድሮስ ታደሰም ፍቅርን አስጀምራው ከጊዜ በኋላ ለተቀየረችበት ወረት የለወጣትን ፍቅረኛው እንዲህ ይላታል አንድም ክደት ውስጡን ሲበላው አንድም መርሳት ያልቻለው ልቡ ዛሬም እሷን ሲናፍቅ "እኔ አይደለሁም ወይ ? የተበደልኩት ከፍቶኝ ሳድር አልችል ሲለኝ ልቤ ተከታይ ሆኖሽ ወጥቶ ሲኖር ፍቅርሽን ልብሽን ገላዬዋ አጥቶ ሲቀር አንቺን አንቺን ብሎ ሲቀር" ~ታዲያ ከላይ ባሉት ስንኞቹ እሷ ቆርጣ ጥላው ስትሄድ መቁረጥ ያቃታው የሱ ልብ መሆኑንና ...ልቡም ባለመቁረጡ እሱን ለጉዳታና ለበደል እንደዳረገውና....ከዛ በኋላ ልቡም እሷን እያለና ፍቅሯን እንዳለ በከንቱ እንደቀረ ይነገረናል . . ~ታዲያ እሱ ፍቅርን ብሎ ብዙ ነገር ሲሆንላት እሷ ግን ፍቅር ለሚለው ነገር ምምን ጊዜ እንደሌላት ገብቶት..ችላ ችላና ጣል ጣል ስታደረገው ...የሱ ጉዳይ እንደማያስጨንቃት ተረድቶ እንዲህ ይላታል "ለፍቅር አንቺ ዘበናዬ ጣል ጣል አረግሽኝ አይከብድሽ የኔ ጉዳዬ አሄሄ ..ለመውደድ ጊዜም የለሽ ወይ . . ለፍቅር ነበር መቸገሬ አንቺን አንቺን እያልኩ ስጨነቅ ሳስብ ማደሬ አሄሄ…ምነዋ ትላንት ወደሽ ዛሬ" ~ በላይኞቹ ስንኞች ይቀጥልና እሱ ለፍቅራቸው ብሎ ብዙ ሲደክምና ሲጨነቅ እሷን ብሎ ብዙ ነገር መሆኑን አስታውሶ..."ምነው ያኔ ስታስጀምሪኝ ፍቅር እንዳለብሽና የእውነተኛ አፍቃሪ መስለሽኝ ዛሬ ላይ ለምን ተውሽኝ ለምን ጥለሽኝ ሄድሽ.?"...ይላታል ፍቅሯ የወረት መሆኑን እያስታወሰም! . . ~ለመታየት ለሱ ያላት ፍቅር የወረት አድርጋው መንገድ ስታበዛ ..ደበቅበቅ ያለውን የሱን ፍቅር ንፋስ እንዲገባው አድርጋ ጥላው ሄዳለች..ነገር ግን የሷ ፍቅር ሱስ ሆኖበታል ልቡ እሷን ተክትሏ ሄዳል...ልበ ቢስ ሆኗልና "ልቤን አጥቼ ከሰውነት ጎድያለሁ...ሌላው ይቅር ግቢሽን ቤትሽን የለመዱኩት ልምጣ ልየው አትከለክይኝ" ይላታል..የለመደው ሲቀር እየከፋው! "ሰበር ሰካ ስትይ ኧኸነ ከመንገድ ትተሽው ሽፍንፍኑ ፍቅሬ ኧኸነ ንፋስ አስነካሽው ግቢሽን ቤትሽን ገላዬዋ ልየው ሁሉንም ልምጣ አትከልክይኝ ያለልብ ሰውም ሰው አልሆንም (2x)" . . . ~ይቀጥልና ከታች "በሆዴም አኑሬሻለሁ..እንደ ሀገር ሰፍቶ ሆዴም አንቺን ባኖረ ..ማን ነው ያየብኝ መኖርሽን ከደብቅኩሽና ሸሽጌ ካስቀመጥኩሽ ከሆዴ ስር..አንቺን ባስቀምጥም ልይዘው ልቆጣጠር ያልቻልኩት እጎረኛው ፍቅርሽ እንደወጣ ነው የቀረው?...እኔም ሁልጊዜ በሆዴም ሳስብሽ ነበር የምኖር ...አፍቀረሽኝ ከልብሽ ከኔ ጋር ፀንትሽ እንድትኖሪ ባልታደልሽም" ይላታል! "አሄሄ..እሱም አገር ሆኖ ዘመድዬ አሄሄ..ሆዴ አንቺን ባኖረን አሄሄ አሄሄ..ማን አየብኝና ማን ሰማብኝና ፍቅርሽ ወጥቶ ቀረ " . . ~ጠንካራ ከመሆኑ ለዱላና ለምርኩዝ የሚመረጠው ክትክታ ዛፍ ቢሰበረ አይታሽም ሰበራውን ይዞ ይኖራል እንጂ...እኔም ወድጀሻለሁ ስቃዬንም እየተቀጣሁ እኖራለሁ....ልቦና አገኝተሽ እስክትመለሽ ድረስ...ፍቅርሽ እንደሆነ ልክፍት ነው አይለቀኝም....ለነገሩ ሌላስ ምን አማራጭ አለኝ" ይላታል! "አሄሄ ..ክትክታ ቢሰበራ የኔ ቆንጆ አሄሄ... እይታሽም በሰው አሄ አሄሄ... እንዲያው መቻል ብቻ አይኔ የወደደውን ልብ እስኪ መልሰው " . . ~አለሁ ግማሽ ጎንህ የትዳር አጋርህ ነኝ...ብላ አደፋፍር ቅልጥ ያለ ፍቅር ውስጥ ሲገባ እንደራቀችውና...ልቡን ከአካሉ ነጥላ...ለጉዳት ፣ለሀሳብና ለጭንቀት ዳርጋው መሄዷን ደግሞ እንዲህ ይናገራል.. "ግማሽ ጎንህ ነኝ አለሁ ብላ ሽሽት ሽሽት ብትል ልቤንም ከኔው ነጥላ አሄሄ…ተበላን አጀቴን ተበላ . . ጠላቴ አልልሽ ወድጄሽ ወዳጄ እንዳልልሽ ዘወትር ህመሜ ነሽ አሄሄ..ሁሉንም ሆነሽ ተገኘሽ ~ታዲያ ስለሷ ለሰው ሲያወራና ምኑ እንደሆነች ለራሷ ሲያስታውስ መልስ ያጣል...ምክንያቱም ወዳጄ ናት እንዳይል ለህመም ለስቃይ ዳርጋዋለችና አይ ጠላቴ ናት እንዳይል ደግሞ በፍፁም ልቡ የወደዳት ሴት ናትና...ሁሉንም ይዛ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ኖሯት እሱም እንዲህ ናት ለማለት ግራ መጋባቱን ይናገራል በላይኛው ስንኝ! . . ~ታዲያ ከእሷ ጋር አንድም ቀን ስለመለያየት አስቦ አለማወቁንና የሷ መለየት ዱብዳ ሲሆንበት..የምትኖርበትን ለማየት መፈለጉን ሳይደብቅና እሷን ካላየ ሰው እንደማይሆንም ጭምር እንዲህ ይናገራል.. "አልተሰናዳሁም ኧኽነ ልለይሽ አልቻልኩም ዛሬም ሆነ ትላንት ኧኽነ ደህና ሁኝ አላልኩም ግቢሽን ቤትሽን ገላዬዋን ልየው ሁሉን ልምጣ አትከልክይኝ ያለ ልብ ሰውም ሰው አልሆንም " . . ~መውደዷን ፍቅሯን እንዳልጠገበውና በጅምረ እንዳቋረጠችው ሁሉ ሳይደብቅም ይናገራል...የፍቅር አምሮቱና ገላዋ የማይረሳ መሆኑንም ጭምር! "አሄሄ..መውደድ መች ጠግቤን የኔ ቆኔጆ አሄሄ ..ፍቅርሽ መቼ በቅቶኝ አሄሄ አሄሄ…አምሮቴ መች ወጥቶ ገላሽ መች ተረስቶኝ x2" . . ~እሱ ጋር ደርሶበት እያየው ስለሆነ ታዲያ በጅምረ የቀረ ያልወጣለት ፍቅር ያለበት አፍቃሪ ታቅፎት የሚኖረው ውርሱ ፀፀት ብቻ መሆኑን እስከመጨረሻው ያስታውሳል እንዲህ እያለ "አሄሄ ..ውርሱን ማሰብ ሆኖ ዘመድዬ አሄሄ... የመውደድ መካሻው አሄሄ ..ያልወጣለት ፍቅር ፀፀት አይደለም ወይ እስከመጨረሻው . . አሄሄ ..መውደድ መች ጠግቤን የኔ ቆንጆ አሄሄ…ፍቅርሽ መቼ በቅቶኝ አሄሄ አሄሄ…አምሮቴ መች በቅቶኝ x2 ገላሽ መች ተረስቶኝ ገላሽ መች ተረስቶኝ አምሮቴ መች በቅቶኝ ገላሽ መች ተረስቶኝ ገላሽ መች ተረስቶኝ ~በመጨረሻም የጀመረው ፍቅር እንዳልወጣለት እሷን እንዳልረሳት...ፍቅርን ተርቦ በጅምር ሳይጠግበው እንደቀረና..ገላዋም፣ ጠረኗም ፣ ሲሰሩት የነበረው ፍቅርም እንዳልተረሳው በላንኛቹ ስንኞች ይናገራል! . . ግጥም ~ይልማ ገ/አብ ዜማ ~ አበበ መለሰ አጃቢ ~ሮሃ ባንድ ✍️ Jah Mc #jahmc1 #teddytadesse #ethiopianmusic #ethiopian_tik_tok #fyp @gigi_shebabaw fans

About