@chenchazukowebetekihnet: ✥ ብዙኃን ማርያም ✥ መስከረም 21 ×××× በቤተ ክርስቲያናችን ከሚዘከሩ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ በዓላት መካከል መስከረም ፳፩ ቀን የሚውለው በዓል ‹‹ብዙኃን ማርያም›› በመባል ይታወቃል፡፡ በዓሉ በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ይከበራል፤ የመጀመሪያው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ውሳኔ ለማዘጋጀት ከሩቅም ከቅርብም የተሰባበሰቡት ቀን፤ ሁለተኛው ደግሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል በግሸን ደብረ ከርቤ የተቀመጠበት ዕለት መኾኑ ነው፡፡ ብዙኃን ማርያም የተባለበት ምክንያት በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ፫፻፲፰ቱ ሊቃውንት በንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ጥሪ መሠረት አርዮስን ለማውገዝ ሚያዚያ ፳፩ ቀን ጉዞ ጀምረው መስከረም ፳፩ ቀን በኒቂያ ስለተሰበሰቡ ብዙኃን ማርያም ተብሏል፡፡ እመ ብዙኃን የሚለውም የሊቃውንቱን ብዛት ያመለክታል፡፡ እንዲሁም እመቤታችን የብዙዎች እናት ናትና እመ ብዙኀን ተብላለች፡፡ (መድብለ ታሪክ)፡፡ ስለዚህ መስከረም ፳፩ ቀን የሚከበረው የእመቤታችን በዓል የብዙኃን ማርያም ይባላል፡፡ ይህም የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግማደ መስቀል ወደ ግሸን ደብረ ከርቤ መግባቱን ተከትሎ ብዙዎች ኦርቶዶክሳውያን ከሰሜን ከደቡብ፣ ከምሥራቅ፣ ከምዐራብ ከሁሉም የሀገራችን ክፍሎች ቅዱስ መስቀሉን ለማክበር የሚሰባሰቡበት፣ እንዲሁም በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም የታነፀችው ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት በድምቀት የተከበረበት ቀን ነው፡፡ የእመቤታችን በረከትና ምልጃ ከሁላችን ጋር ይሁን። #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ፀንታ_ለዘለዓለም_ትኑር
የጨንቻ ዙሪያ ቆጎታ ወረዳዎች ቤተ ክህነት ሚዲያ
Region: ET
Thursday 01 October 2026 18:31:54 GMT
Music
Download
Comments
gobaze sefu :
🥰🥰🥰
2026-10-01 18:41:34
0
ባሻ ወርቅነህ :
❤️❤️❤️
2026-10-02 10:04:58
0
To see more videos from user @chenchazukowebetekihnet, please go to the Tikwm
homepage.