@aj.ethiopia: የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ከድር ጁሀር የስራ ጊዜያቸውን በማጠናቀቅ ስልጣናቸውን ለአዲሱ ከንቲባ አቶ አብዱላሂ አደን በክብር አስረከቡ። ይህ ርክክብ በከተማዋ የፖለቲካ ድባብ ውስጥ ያለፈው አመት ክስተቶችን ዳግም ወደ ትውስታ ያመጣ ነው። ያለፈው አመት ለአቶ ከድር ጁሀር እጅግ ፈታኝና በውጣ ውረድ የተሞላ ጊዜ እንደነበር አይዘነጋም። ለሙሉ አንድ ወር ያህል ከመቀመጫ ከተማቸው ድሬዳዋ ተነጥለው አዲስ አበባ ውስጥ ሲቆዩ፣ ከባድ ግምገማ ላይ እንደነበሩና ከስልጣን ሊነሱ በቋፍ ላይ መሆናቸው በስፋት ይነገር ነበር። የፖለቲካው ውጥረት እና ከስልጣን የመነሳት ስጋት ከንቲባውን በከፍተኛ የጭንቀት ድባቴ ውስጥ ከቷቸው እንደከረሙ የቅርብ ምንጮች ያስታውሳሉ። ሆኖም ያንን ከባድ የ"አዲስ አበባ ፈተና" አልፈው በሀላፊነታቸው እንደሚቀጥሉ ሲወሰን፣ ወደ ድሬዳዋ ሲመለሱ የተፈጠረው ድባብ እጅግ ደማቅና የተለየ ነበር። አቶ ከድር ስልጣናቸውን አስጠብቀው ወደ ከተማዋ ሲገቡ በተዘጋጀላቸው ከፍተኛ ድግስ ላይ በርካታ የእንኳን ደስ አሎት ስጦታዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ የደስታ ምኞቶች እንደ ጎርፍ ፈሰውላቸው ነበር። ያንን ሁሉ የፖለቲካ ማዕበል እና የድል አጥቢያ ፌሽታ አልፈው ከተማዋን ሲመሩ የቆዩት አቶ ከድር ጁሀር፣ አሁን የከንቲባነት ጊዜያቸውን በሰላም አጠናቅቀው መንበራቸውን ለቀጣዩ ከንቲባ ለአቶ አብዱላሂ አደን አስረክበዋል። አዲሱ ከንቲባ አቶ አብዱላሂ አደን የድሬዳዋን አስተዳደር በመረከብ ቀጣዩን የከተማዋን ጉዞ የሚመሩ ይሆናል።
AJ Ethiopia
Region: ET
Friday 02 October 2026 10:51:20 GMT
Music
Download
Comments
Asmika :
be neberu mirti sira seritewali
2026-10-02 17:11:37
0
dagi :
you are hero Kediro
2026-10-02 14:12:46
0
fidorya yared :
Goodbye behedbet yeknaw[Heartwarming][Heartwarming][Heartwarming]👋 👋
2026-10-02 19:39:17
0
Elroe :
ewddihalew kedire
2026-10-02 16:59:28
0
zak Weloyew :
የክፍለ ዘመኑ ምርጥ ከንቲባ
2026-10-02 14:16:40
14
ፔስኮ የናዙ :
ጀግናን ሁሌም ቢሆን ሀገሩ ትፈልገዋለች ሁሌም ቢሆን የድሬድዋ ከንቲባ አቶ ከድር ጀዋር እኔ በበኩሌ ሁሌም ቢሆን ለርሶ ከወበሬ ብድግ ከወገቤ ጎንበስ ከማለት አልታክትም ባሉበት ክብረት ይስጥልኝ ሰላም
2026-10-02 15:18:55
10
Lishane :
ለፌደራል የምጠብቀው መሪ
2026-10-02 14:52:51
5
birihan :
enwdhalen 🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-10-02 14:52:40
0
selamawit Girma :
የኛ ምርጥ መሪ🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-10-02 15:40:54
2
Zewde :
ባለህበት ፈጣሪ ይጠብቅህ
2026-10-02 19:08:40
1
teferaferede :
በእውነት በአመራር ሥ/ምግባር መርህ የሠራና የሚሠራ ፍቅር የሆነ ሰው ነው ገዥው መንግሥትም በቅርበት የሚፈልገው ወጣትአመራስለሆነ ቀጣይ ብዙ ይጠበቅበታል
2026-10-02 15:51:28
2
@ y.a.m.a.n.u.a.l t.e.m.u.2.8 :
እኔ በግሌ ደስ የሚለኝ ከንቲባ ነው
2026-10-02 14:28:38
3
ድሽቃው ምት ጎጃሜ :
የተከበሩ አቶ ከድር እባክዎ ኢትዮጵያን ከውድቀት ይታደጉልን🙏🙏🙏🙏
2026-10-02 15:26:35
2
Adino :
በጣም ይገርማል ከእሱ የተሻለ ኖሮ ይሆን
2026-10-02 14:59:00
1
መቅድም :
በስራ ዘመናቸው ባደረጉት ቆይታ ለድሬደዋ ነዋሪ መልካም ሰርተዋል በ ቀሪ ዘመናቸው መልካም ይግጠማቸው
2026-10-02 16:39:55
1
mg :
ጀግና መሪ ምክትልም ቢሆን ድሬን ከከቲባው ጋር ዳር ያደርሳል❤️❤️❤️🇪🇹❤🇪🇹❤🇪🇹
2026-10-02 12:05:37
2
Getahun :
መልካም ጊዜ ይሁልህ የተትካዉም እንደ እርሶ ስመ ገናና እንዲሆን እንመኛለን። ለእርሶም የተሻለ ሥራ እመኛለሁ።
2026-10-02 14:11:32
1
@bek :
ጀግና ነው ከድሬ 👍🥰👍 ስልጣንን ቀላል አድርጎ የሚስብ አይጠፋም
2026-10-02 12:38:16
1
kkkk :
የኔ ጀግና መልካም ቅን ሰው አይፈለግም የኔ መልካም መልካም ይግጠምህ
2026-10-02 15:26:51
5
Adu :
ዘመኑ ቀሪ እድሜውን ይደሰት እኔ በሚዲያ ነው የማውቀው ቅን ነው በጣም አከብርሃለሁ ምርጥ ኢትዮጵያዊ ነህ ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
2026-10-02 19:01:40
0
user6753814215824 :
ግን ለምን?
2026-10-02 19:42:03
0
Masi bark :
የኛ ምርጥ ሰው በሄርክበት ሁሉ እግዚአብሔር ይጠብቅክ 🥰🥰🥰
2026-10-02 19:28:09
0
Deme yaba boreda 🦋የኔታ🦋 :
ሃይማኖትን የግል አርጎ 1 አገር ላይ በጋራ መኖር
indemichal ያሳየን ምሳሌ መሆን የቻለ የዘመኔ ጀግና አቦ ተባረክ ዘርህ የለምልም እናት አንተን twuled
2026-10-02 19:25:48
0
Marta, Girmaa :
mirt.meri.new.yimechew.
2026-10-02 20:26:12
0
Deme yaba boreda 🦋የኔታ🦋 :
ቃላት አይገልፁህም አንተን ሳስብ ኢትዮጵያዊ መሆኔን እዎደዋለሁ ሀገሬም ተስፋ እንዳላት ይሰማኛል ይሄ ሁሉ ውጥንቅጥ ያልፋል እንድል ታረገኛለህ
ያንተ አይነቱን ያብዛልን
2026-10-02 19:15:52
0
To see more videos from user @aj.ethiopia, please go to the Tikwm
homepage.