@pctopersonalcomputer: ካገባች ከዓመታት በኋላ አፍራህ ጋር ተገናኘን ከጎኑዋ ነበር ምቀመጠው ግን ማንም አያቀኝም ነበር እሱዋ ካለች ማን ጊዜ አግኝቶ ወደጎን ያያል ድንገት መንገድ ላይ ነበር ያገኘሁዋት እሱዋ በመኪና እኔ በግሬ እየኳተንኩ አይታኝ ጠራችኝ ትንሽ ወፍራለች ግን አሁንም ውብ ናት ቤት ካልሄድን ብላ በሰፊው የሷ ቤት ሂደን እናውራ አለችኝ ሰው የራባት ትመስላለች ፤ ከብዙ ጊዜ ቡሀላ ስለነበር ምሄድበትን ትቼ ወደሱዋ ቤት ሄደን ግቢው ላይ 2 መኪና ቁሞዋል 3ተኛ የሷ ቆመ ''ልጆቹስ '' ''ትምርት ናቸው ካንድ ሰአት ቡሀላ ይመጣሉ '' አለችኝ። ቤቷ ደርሼ ከተጫወትንና ቡናችንን ከጠጣን በኋላ፣የትምህርት ቤት ትዝታችን ተነሳ። ከአፍራህ ጋር በወይዘሮ ስሂንና በእውቀት ጮራ ትምህርት ቤት የነበሩን ቀናት አይረሱኝም። እሷ የደሴ የቁንጅና ምልክት ነበረች፤ ወንዶች ሁሉ በየመንገዱ አይኗን ለማየት ይጓጉ ነበር። የትምህርት ቤት ትዝታችን ሲነሳ በወሬ ወሬ አላሚን ትዝ አለኝ በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ አፍራህን ሲከተላት፣ ጥቁር አይኖቿን ተክዞ ሲመለከትና በየቀኑ ሳያያት ወደ ቤት የማይመለስበት ያ የንጹህ ፍቅር ጊዜ ፤ ከዛ ሁሉ ተማሪ መካከል ያ ዝምተኛና ምስኪን ልጅ አላሚን የሚያያት እይታ ፈጽሞ የተለየ እንደነበረ ውስጤ ያውቅ ነበር። አላሚን ከልቡ ያፍቅራት እንደነበር አውቃለሁ፤ በዚያ ምስኪን ሁኔታው ውስጥ ሆኖ ያለውን ንጹህ ፍቅር ሳስበው ሁልጊዜ ያሳዝነኝ ነበር። አላሚንን ስም አነሳሁ ጠየኳት «አፍራህ... ግን እውነት አላሚን ያኔ በትምህርት ቤት እጅግ አብዝቶ ይወድሽ እንደነበረና የሱ ፍቅር ምን ያህል ጥልቅ እንደነበረ ታውቂ ነበር?» ብዬ ጠየቅኳት። አፍራህ ከንፈሯን ነክሳ፣ በሀሳብ ተዋጠች። ከዚያም ወደ ህንጻው መስታወት በር ዘወር ብላ እጇን እየጠቆመች ''እንዴት አላውቅም ነበረ ብለሽ ነው? አሁንም ቢሆን እኮ እሱ እኔን ለማየት ሁልጊዜም እዚህ ህንፃ መስታወት በኩል ይመጣል። እዚያጋ ቆሞ አይቼዋለሁ'' አለችኝ። ገረመኝ በጣም ተገረምኩ ''አሁንም '' አልኳት ''አላሚን ለኔ የነበረውነገር ይገርመኝም ያሳስዝነኝም ነበር፤ ትምህርት ቤት በነበርንበት ጊዜ ብዙ ወንድ እንደሚፈልገኝ አውቃለሁ እሱ ግን ተክዞ ሲመለከተኝ ሲደናበር ደግሞ ጎበዝ ነበር፣ ዝምታውና ጭንቀቱ ይለይ ነበር በጣም ነበር ሚያሳዝነኝ ሚስኪን።'' ''መች ነበር ግን ያወቅሽው '' ''መጀመሪያ የሆነጊዜ ትዝ አይልሽም መምህሩ ጠይቆኝ ተሳስቸ እሱ ሲያጨበጭብ ከዛ ቡሃላ አየው ጀመር ያሳዝነኛል። '' ''አንድ ቀን ግን በጭራሽ አልረሳውም። ከእናቴ ጋር በዘይት ቤቱ በኩል በጓሮ መንገድ ስናልፍ፣ ድንገት መንገድ ላይ ፊት ለፊት ተገናኘን። አላሚን ደንግጦ እንደ ክንፍ እጆቹን ዘርግቶ፣ ወዴት እንደሚሄድ ጠፍቶት ግራ ሲጋባ አይቼው በጣም አሳዘነኝ። '' አለችኝ ተከዝ ብላ ማውራቷን ሳይ ጨዋታውን ለመቀየር እየሞከርኩ ''ባለቤትሽስ ጋ እደት ናችሁ ''አልኳት ''ባለቤቴ ጥሩ ሰው ነው ግን በፍጹም ጊዜ አይሰጠኝም፤ ምንም ጊዜ የለውም አንዳንዴ ሰው በጣም ይናፍቀኛል።ምን አለ አላሚን ለኔ የሚኖረውን ያህል ጊዜና ትኩረት የሚሰጠኝ ሰው በኖረኝ ብዬ እመኛለሁ። '' አላሚን እዛው በቆምንበት ከነጫቱ ብቅ አለ ተቀያይሩዋል ባትነግረኝ አላውቀውም ወደኛ በኩል ያይ ነበር እኛ ከውስጥ ሁኖ ይታየናል። ስታየው ፈገግ አለች ''አሁን ልጆቸን ለመቀበል ምወጣበት ሰአት ነው። ለዛ ነው የመጣው እኔን ለማየት ነው '' አለች። ሲጋራውን ለኮሰ ''አያስዝንም '' አለች ''በጣም'' አልኳት ከዛም በሷ ፍቅር ምክንያት ቁጭ ብሎ እሱዋን በሚጠብቅበት ቦታ በኋላ ላይ የጫት ሱሰኛ እደሆነ። እሱዋም ይህን ስታይ ልቧ እደተሰበረና ፤ እሱን በዛ ሁኔታ ማየት ስለከበዳትና ለሰጣት ንጹህ ፍቅር ካላት እዝነት የተነሳ፣ አላሚን ሳያውቅ በድብቅ የጫት እና ለተወሰነ ነገር ብር እደምትልክለት ነገረችኝ። አዘንኩለት !!! መኪና ከግቢው በር ቆመ ክላክስ ተደረገ ልጆቾ ከትምርት መጡ። ወርዳ ተቀበለች ብቅ እያለ ካለበት በር ላይ ሁኑ አያት ፈገግ አለና ወደሚቅምበት ወደውስጥ ገባ። ኢንሻአላህ ደህና ይሆናል !!! አለችኝ አፍራህ

ደስታ የሆንኩ ሰው
ደስታ የሆንኩ ሰው
Open In TikTok:
Region: ET
Saturday 03 October 2026 12:24:48 GMT
29193
1960
85
310

Music

Download

Comments

yuti_nass
yuti_nass :
gobez derasi neh gn yenesun tarik atenka beka 😩
2026-10-04 06:02:38
59
asad962z
Asad :
አላሚን :- አልሀምዱሊላህ አፍራህ ደህና ናት አፍራህ፡- ኢንሻ አላህ ደህና ይሆናል 🙌
2026-10-04 05:49:31
108
fozy995
fozy562 :
Finally l got it🥰😭
2026-10-06 04:34:42
0
jack.fasil
Jack :
እኔ ደግሞ የመሀሪ ፍቅረኛ ሮሀ መሀሪ ጥፋተኛ እንዳልሆነ ስታውቅ ሚሰማትን ስሜት ነው ማወቅ ምፈልገው
2026-10-04 04:50:08
75
lil.maiko
lil.maiko :
Now i can sleep peacefully...
2026-10-04 16:43:35
1
trendethio
TREND ETHIO :
Lb weled new aydel? gn everybody ewnet new yemimeslew ena belju hulum aznual ahun afrah Endalechw Deha hono maseb felekugn. think about it please 🥺
2026-10-04 09:05:48
7
dagibaba12
dagi baba :
እናውቀዋለን ብለን ካሰብነው እውነት ጀርባ ብዙ እውነት አለ
2026-10-03 19:52:15
25
dagi_gagi1
@dagi :
ay alamin beka hule anjeten endebelaw
2026-10-04 00:06:29
20
huzu098
huzeyef :
እስኪ በነካ እጅህ ትርኳሽ ላይ የፊላዬን side of story ፃፍልን
2026-10-04 03:03:24
6
just_mira90
Mira🍂 :
Alamin😭
2026-10-03 13:53:16
14
marmawit_2322
𝖓𝖆𝖇 :
dersteh des yela gn menale yensun batnkaw 😞
2026-10-04 07:07:45
1
sudeys896
SUDEYS"""S :
seriously gn ehe tarik ewnet new ende??
2026-10-04 03:51:28
3
fromturab
AMD Combo :
እናመሰግናለን። የጎደለውን ስለሞላህልን
2026-10-04 04:37:12
4
ahmi...aladi
ahmi...aladi :
👏👏👏👏👏👏 ከዛው እንደቀጠለ አድርጌ ነው ያነበብኩት በጣም ጎበዝ 👏👏👏👏👏👏👏
2026-10-04 17:50:07
1
blacky0354
blacky :
ye filayen side of story please 🥺
2026-10-04 03:27:43
2
hermi.henok
Hermi Henok :
እንኳን ፆፍክ🙌
2026-10-03 20:33:05
2
milkiawel
Milki 🧔‍♂️ :
arif content nw ena qetelebet
2026-10-03 21:01:58
1
mikey_assefa
M¡<¡ :
🥺 ay alamin
2026-10-03 20:52:58
1
alemtsi1612
@Tsi🌸 :
ሲጀመር አሌክስ ልባችንንም ታሪኩንም ሰቅሎታል
2026-10-04 12:45:57
2
fuad.the.king
F🦢 Never give up bro :
2026-10-04 01:18:58
1
dimitros2
Dimitros birhanu :
ያበደ ነው🥺
2026-10-04 09:37:41
1
aurora_moon38
⚡ :
techelaleh nw meleh👏👏
2026-10-04 12:05:56
2
ebropic
EBRAHIM 🎥 :
2026-10-04 20:06:38
1
kedutin
kedria's way🍂 :
🥺
2026-10-04 11:12:54
1
zeeee7236
Zeeee :
ተባረክ
2026-10-04 17:16:13
2
To see more videos from user @pctopersonalcomputer, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About