@abdubookdelivery: ከመጽሐፉ የተወሰደ ✍️​ኢብራሂም አወል ሀገራዊ የኤ.አይ ባለቤትነት (Sovereign AI) እና የቋንቋ ጥበቃ ተነጣጥለው የሚታዩ ጉዳዮች አይደሉም። ቋንቋዎቻችን እና ባህሎቻችን በዲጂታል ዘመን ህያው ሆነው እንዲቀጥሉ፣ ቴክኖሎጂውን የራሳችን ማድረግ ግዴታ ነው። የውጭ ቴክኖሎጂዎችን ዝም ብሎ ተጠቃሚ ከመሆን በመውጣት፣ የራሳችንን የመረጃ ካዝና በራሳችን ባለሙያዎች ገንብተን ትውልዳዊ እና ሀገራዊ እሴቶቻችንን በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ማሳየት ይገባናል። ይህ ሂደት ውስብስብ እና ረጅም ቢሆንም፣ ዲጂታል ነፃነታችንን ለማረጋገጥ እና ባህላዊ ማንነታችንን ከዲጂታል መጥፋት ለመታደግ ያለን ብቸኛ አማራጭ ነው። ​"የAIን ውስብስብ ጽንሰ ሐሳቦች በቀላል አማርኛ በማቅረብ ትልቅ ክፍተት የሞላ መጽሐፍ ነው። ኢብራሂም ቴክኖሎጂውን ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ ያደረገውን ጥረት እያደነቅሁ፣ በማንኛውም ዘርፍ ላይ ያለ አንባቢ ሊኖረው የሚገባውን መሠረታዊ እና አስፈላጊ የAI ዕውቀት የሚያስጨብጥ ምርጥ ሥራ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።" ​ሶስና ጋሻው (ረዳት ፕሮፌሰር) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ #abdubookdelivery #abdubook #viral #BookRecommendations #newamharicbook

Abdubook 📚
Abdubook 📚
Open In TikTok:
Region: ET
Sunday 04 October 2026 13:55:37 GMT
79
10
2
1

Music

Download

Comments

moonjib0
Moooon :
🥰🥰🥰
2026-10-04 14:05:00
1
To see more videos from user @abdubookdelivery, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About