@sarwitegetagiram: #ጾመ #ጽጌ #እንኳን #አደረሳችሁ ! ከመስከረም 26- ህዳር 5 👉የእመቤታችን ስደት በጾም በጸሎት የምታስቡ ወይም የምታሳልፉ የእመቤታችን የድንግል ማርያም የቃልኪዳን ልጆች ከወዲሁ እንኳን አደረሳችሁ 👉ጾመ ጽጌ ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ያለው አንድ ወር ከዐሥር ቀን ወይም 40 ቀን ወርኃ ጽጌ፣ ዘመነ ጸጌ፣ ተብሎ ይጠራል፡፡ 👉በነዚህም ቀናት በየቤተክርስቲያኑ የሚነበቡ ምንባቦች፣ የሚዘመሩት መዝሙሮች፣ የሚሰበከው ስብከት፣ የሚቆመው ማኅሌት በጠቅላላው የሚነገረው ስብሐት እግዚአብሔር ሁሉ ሰማይ በከዋክብት ምድር በጽጌያት አሸብርቀው የሚታዩ መሆናቸውን የሚገልጽ ነው፡፡ ወርኃ ጽጌ ለሚከናወነው መንፈሰዊ አገልግሎት መነሻው “መልአኩ ሕፃኑንና እናቱን ወደ ግብፅ ይዘሃቸው ሽሽ፣ የሕፃኑን ነፍስ ሊገድሉት ይፈልጋሉና” ሲል ለዮሴፍ በሕልሙ በነገረው መሠረተ ዮሴፍም ሕፃኑንና እናቱን ድንግል ማርያምን ይዞ ወደ ግብፅ መሰደዱና እመቤታችንና ሕፃኑ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ በስደት ከኖሩ በኋላ /ራእይ.12፣6/ ወደ አገራቸው ወደ ናዝሬት የመመለሳቸው መታሰቢያ ነው፡፡ /ማቴ. 2፣13-23፣ ት.ኢሳ.19፣1፣ እንባቆም 3፣6-7፣ መዝ.83፣3/፡፡ 👉ይህንንም በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሡ አባ ጽጌ ብርሃን ፍሬ ከአበባ አበባም ከፍሬ እንደሚገኝ ሁሉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስን በአበባና በፍሬ እየመለሰ በሚያስረዳው ድርሰታቸው እንዲህ በማለት ገልጸውለታል፡፡ “ አፈወ ሮማን ማርያም ጽጌ ቀናንሞ ወአበሜ፣ እስከ ተጸምሐየየ በጾም ዘመልክዕኪ ጊዜ ድክታሜ፣ እምተመነይኩ ተሳትፎ ከመ አኅትኪ ሰሎሜ፣ ወፍሥሓኪ ዘአልቦ ፍጻሜ”፡፡ ሲተረጎምም የሮማን ሽቱ የቀናንሞ አበባ የምትሆኚ ማርያም ሆይ፣ በርሃብ በጾም አበባ የመሰለ የመልክሽ ደም ግባት እስኪጠወልግ ድረስ በስደትና በልቅሶ የደረሰብሽን ችግርና ድካም መከራሽንም ሁሉ እንደ እኅትሽ እንደ ሰሎሜ አብሬሽ ብቀበል ምኞቴ ነበር፤ በዚህ ፍጻሜ የሌለውን ደስታሽን እሳተፍ ነበር፡፡ እንዲሁም አባ አርክ ሥሉስ በስደቷ የደረሰባትን ኀዘን ፣ ልቅሶና ሰቆቃ አስመልክተው በደረሱት ‘ሰቆቃወ ድንግል” በሚለው ድርሰታቸው እንዲህ አሉ፣ ፀሐይን የምትለብሽ የብርሃን ልጅ ቅድስት ድንግል ማርያም ከክፉ ከሄሮድስ ዘንድ ልጅሽን ባሸሸሽ ጊዜ የደረሰብሽን ችግሮች ጨረቃን የሚጫሙ እግሮችሽ በመንገድ ብዛትና በአሸዋ ግለት እንደ ጎበጎቡ ሲሰማ ሰው ይቅርና ድንጋዩም ባለቀሰ ነበር”፡ 👉የእመቤታችን የስደቷ መታሰቢያ ወር በቤተ ክርስቲያናችን የሚከበረው በማኅሌት፣ በቅዳሴና በዝክር ነው፡፡ በወርኃ ጽጌ ባሉት ሳምንታት ከቅዳሜ ማታ እስከ እሑድ ጠዋት አበው ካህናት የሚያቀርቡት ዝማሬ ከቅዱስ ያሬድ ድጓ፣ ከማኅሌት ጽጌና ከሰቆቃው ድንግል የተውጣጣና ሦስት ወገን ያለው ነው፡፡ ዝክሩም፣ በአሁኑ ወቅት በከተሞች አካባቢ እየተረሳ ቢመጣም፣ ዘወትር እሑድ የአንድ አካባቢ ሰዎች ማዕከላዊ በሆነ ቦታ ተሰባስበው በእመቤታችን ስም የሚዘክሩት ነው፡፡ ዐቅመ ደካሞች፣ ድሆችና መንገደኞች ተጠርተው በእመቤታችን ስም እንዲበሉና እንዲጠጡ ይደረጋል፡፡ 👉ይህም ትውፊት እመቤታችን ወደ ኢትዮጵያ በመጣች ጊዜ ኢትዮጵያውያን አባቶችና እናቶች ያደረጉላትን መስተንግዶ ለማሰብ ነው፡፡ ከእመቤታችን በረከት ያሳትፈን አሜን!!!
@sarwite Geta Giram የተዋህዶ ልጆ
Region: BH
Monday 05 October 2026 07:02:40 GMT
Music
Download
Comments
ETENESH GIRMA :
እልልልልልልልልልልልልልልል[Red heart][Red heart][Red heart][Red heart][Red heart][Red heart][Red heart][Pray][Pray][Pray][Pray][Pray][Pray][Pray][Pray][Pray]
2026-10-05 12:27:12
0
✝️የድግል ልጂ አተ ጠብቀኝ ❤ :
elllllllllllllllllllllllll🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-10-05 07:09:10
2
ብሬ 👍 :
እንዃን አደረሳችሁ
2026-10-05 09:06:26
4
samri :
elllllll🥰🥰🥰🥰
2026-10-05 07:50:12
0
Geni21# :
2026-10-05 10:18:51
3
user9451949912765TIGIST SASU :
🥰🥰🥰🥰🥰Amen amen amen🥰🥰🥰🥰🥰👏👏👏👏
2026-10-05 09:55:22
1
Hawaii arsii 🌺🫶 :
AMen AMen AMen AMen AMen AMen AMen AMen AMen 👏👏👏👏👏 Enifami Ebifami Ebifami Ebifami Ebifami Ebifami Ebifami Ebifami 🙏🤲🙏🤲🤲🙏🙏🤲
2026-10-05 09:01:06
1
Tg@1221 :
አሜን እንኮን አብሮ አደረሰን
2026-10-05 09:45:19
1
adis alem :
እንኳን አደረሳችሁ 🥰🥰
2026-10-05 09:45:45
1
ያቤ :
እንአደረሳቹበስደትያላቹእህትወድሞቼየመቤታችንየስደቷመታሰበያዋፆመፅጌ
2026-10-05 08:47:15
1
mskrm :
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🤲🤲🤲🤲🤲
2026-10-05 07:29:34
1
መሳይ የሚካኤል :
አሜን አሜን አሜን
2026-10-05 12:32:16
0
roza :
🥰🥰🥰❤️❤️❤️
2026-10-05 12:43:55
0
ሄርሚ :
እእእእእእእልልልልልል
2026-10-05 12:31:31
0
#እናቴ❤ማርያም❤እወድሻለሁ❤👏👏👏 / :
አሜን
2026-10-05 12:10:45
0
የዛሬን እንጂ የነገን ማን ያውቃል?? :
amen amen
2026-10-05 09:13:02
0
ወለተ ገብርኤል :
🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-10-05 12:28:20
0
Wዬ😘ነኝ የማክሰኝቷ🎶 :
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-10-05 12:21:00
0
የሐና :
እንኳን አብሮ አደረሰን
2026-10-05 11:38:05
0
እግዚአብሔርን ይመስገን :
ልልልልልልልልልልልልልል
ልልልልልልልልልልልልልልል🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-10-05 11:39:15
0
Belatu Zanena :
🙏🙏እልልልልልልልልልልልልልልል🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-10-05 12:48:21
0
kebron :
amen amen amen
2026-10-05 12:21:34
0
zd :
አሜን አሜን አሜን እንኳን አብሮ አደረሠን 🙏🙏🙏🙏🙏❤️❤️❤️❤️
2026-10-05 11:50:03
0
GENETKEBEDE :
እልልልልልል
2026-10-05 11:42:13
0
Mulu Tizazu :
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
2026-10-05 07:57:26
0
To see more videos from user @sarwitegetagiram, please go to the Tikwm
homepage.