@firduaklilu: በህጋዊ እና መንግስታዊ መረጃዎች (እንደ ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት - ኢዜአ፣ የክልል መገናኛ ብዙኃን እና የፓርቲ መግለጫዎች) መሰረት፣ የነዚህ አራቱ ክልሎች ፕሬዚዳንቶች እና ከፍተኛ አመራሮች ከስልጣን የወረዱበት ወይም የተነሱበት ዋና ምክንያት በፍላጎት ላይ የተመሰረተ የስልጣን ሽግግር፣ አዳዲስ ክልሎች ከመቋቋማቸው ጋር ተያይዞ የተደረጉ የመዋቅር ለውጦች፣ እና የፓርቲዎች ወቅታዊ የግምገማ አቅጣጫዎች የሚሉ ናቸው ። ከዚህ ውጪ ከህገ-ወጥ ድርጊቶች ወይም ከግል የአመራር ውድቀቶት ጋር የተያያዙ ናቸው የሚል ግልጽ ምክንያት በይፋ የገለጸ ሚዲያም ሆነ ተቋም የለም። ሆኖም በአራቱም ክልሎች ከመልካም አስተዳደር ,ከሰላምና ጸጥታ ወይም ከራሱ ከክልሉ የሚነሱ የገፉ የፖለቲካ ቅራኔዎች መፈጠራቸውን ማንም የሚክደው ሀቅ አይደለም። ሆኖም ይህ ሹም ሽር ግልጽ የሚሆነው በየክልሎቹ የተሾሙት አዳዲስ አመራሮች ሹመትና የስራ ልምድና ብቃት በመነሳት አመራሮች ከስልጣናቸው የተነሱት በራሱ በፓርቲው ጥልቅ ግምገማ አሳማኝ ሆኖ እንደሆነ በግልጽ መናገር ይቻላል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ሐገሪቷ መመራት ያለባት በተሻሉና ብቃት ባላቸው አመራሮችና ወቅቱን በጠበቀ መልኩ መሆን እንዳለበት በምርጫ ቅስቀሳ ወቅትና በኋላም በጥብቅ ሲናገሩ ነበር። አንድ አመራር በስራው ለመቀጠል የግድ ስራው ምስክር ማድረግ አለበት እንጂ የማህበራዊ ሚዲያ ሰራዊት በማሰማራት ስራ የተሰራ ማስመሰል ከፓርቲ ግምገማ አያስመልጠውም። አገሪቱ ከገባችበት የፌዴራሊዝም ማሻሻያ እና የአስተዳደር ሪፎርም ጋር በቀጥታ የተያያዘ ለውውና የአመራር ሹም ሽር ማድረግ ይጠበቅባት ነበር። ይሁን እንጂ አራቱም አመራሮች ደካማና ጠንካራ ጎን ያላቸው ሲሆን ክልሎቹ ከቀድሞው ደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት ተላቀው አዲሶቹን ክልሎች በመምራት በተለይ የበጀት እጥረት,የሰው ኃይል እጥረትና መሰል ተግዳሮትን ተቋቁመው ለአዲሶቹ ማስረከባቸው የሚናቅና ዝም ብሎ የሚታለፍ አይደለም። ለዚህም ይመስላል በሰላማዊ መልኩ የስልጣን ርክክብ ሲደረግ የነበረው። በሌላ በኩል አመራሮቹ በሕግ ተጠያቂ የሚሆኑበት አግባብ በተለይ የሙስና ወንጀል ካለ ወይም ወንጀል የተፈጸመ ለመሆኑ አስተማማኝ ማስረጃ ካለ ከስልጣን መነሳታቸው እንደ ጋሻ ሊያገልግል ካለመቻሉም በላይ በሩ የተዘጋ ነው ማለት አይደለም። ይሁን እንጂ አንድ ሰው በፍ/ቤት ጥፋተኛ ተብሎ ውሳኔ እስካልተሰጠበት ድረስ ነጻ ሆኖ የመገመት ሕገመንግሥታዊ መብት ያለው በመሆኑ አንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት ራሳቸው ወንጀል እየሰሩ ነው። በመሆኑም በአሁኑ ሰዓት አራቱም አመራሮች ምንም አይነት ወንጀል ስለመስራታቸውም ሆነ ከሰልጣን የተነሱትም በዚህ አግባብ ነው የሚል አንዳች ፍንጭ በሌለበት የአመራሮቹን ስም ለማጥፋት መሞከር ትልቅ ስህተትና ወንጀል በመሆኑ ከወንጀል ተግባር ልንታቀብ ይገባል። ውድ ተከታዮች የምትሰሙት የምታጋሩት መረጃ በተቻለ መጠን ከትክክለኛው ምንጭ መህኑን ወይም ምንጭ በአግባቡ የተጠቀሰ መሆኑን ሳታረጋግጡ የትኛውም መረጃ አታጋሩ ውይም አትቀበሉ

ፍርዳወቅ የሕግ አገ/ት Firdawek legal
ፍርዳወቅ የሕግ አገ/ት Firdawek legal
Open In TikTok:
Region: ET
Monday 05 October 2026 07:11:50 GMT
84663
810
19
29

Music

Download

Comments

user8597163393063
user8597163393063 :
ጥሩ ስራም ሰሩ መጥፎም ስራ ሰሩ ........ ህሊና የሚባል ነገር አለ ተከትሏቸዉ የሚዞር ፍርዱን ለራሳቸዉ መተዉ ነዉ
2026-10-05 14:27:05
5
jositikiokker
josi :
leochi nacewu
2026-10-05 12:30:48
1
.918259254
@ DEJENE GITA :
አልቻሉም ወይ ዘረፉ ደግሞ ደቡብ /4 ክልል አድሱ ክልሎች የእያንዳንዱ ጉዳይ የብልጽግና መራሹ እንድገልጽልን እንደ ቀድሞ ደቡብ ክልል ሆኜ ማወቅ እፈልጋለሁ
2026-10-05 13:03:09
1
teshome.zelalm
Teshome Zelalm :
ብልፀግናውሰጥ መን ሀህሊና አለው ከመሪው ጨምሮ
2026-10-05 16:52:57
0
hayileyesus.luta
BOGALE LUTA :
ስልጣን ለመስጠት ነው
2026-10-05 14:49:44
0
29fire
user2705017385066 :
ብልጽግና ላይ ህዝቡ አመኔታ እንዳይኖረው ስላደረጉ ነው።
2026-10-05 10:39:30
0
fanta.tadesse
Fan25 :
እንደ አንድ ክልል ስለሚታዪ ነው
2026-10-05 11:37:06
1
dagbek4
dagim thinker :
desta 1.3 billion birr alebet be kililu auditor temermiro ,,,lehig mekreb sinorbet lesiltan litach neeu
2026-10-05 13:18:50
0
user54614873450275
ቤተሰብ :
አንጀኛ በመተካካት ራሳቸውንና ዘመድ አዝማድ እንድያበለፅገ ነበር ከመቶ ፐርሰንት በላይ ስላሳኩ ቀጣይ ተረኛ ደግሞ የነሱን ተሞክሮ እንዲያስቀጥሉ ነዋ
2026-10-05 17:44:28
1
dagbek4
dagim thinker :
serkewu
2026-10-05 11:28:00
2
linear5552
Loranso :
ብወርዱ ባይወርዱ ምን የተለየ ነገር ይፈጠራል ያው ማንም እንደሚለቅ መጀመሪያ ከተሾሙበት ሥልጣን ተነስቶዋሉ በማለት ሥራ ፈቶች ጊዜ ማሳለፊያ ከመሆን ውጪ
2026-10-05 07:47:54
1
abush.assele
Abush Assele :
የመሩቱን ክልል በ.................ሚራክል በሚራክል ሰላደርጉ😭😁😂😳
2026-10-05 09:22:33
1
user1193666847629
user1193666847629 :
Tikikilenya Malkt Nawu Hulachinm Kemenger Bafit madamax,mastawal yasfaligal sawu kabota yeminasawu bexifat bicha sayihon Lehager edgatna ginbata man kaman yebalexe hagarin mashager yichilal tablo enjii badiro akahed adalemin hulachin balenbat bota hulu kane Egale yibalxal bilen lana gewu tiwuld masab alebin .
2026-10-05 19:41:52
0
edram.1027
Mafiosis :
ዳይፐር አይቀየርም ያለህ ማን ነዉ።
2026-10-05 14:09:57
1
abinetwendimu02
life :
ወደ ማሰልጠኛ ለሚኒሻ
2026-10-05 18:32:52
0
city2432
city :
the unfit
2026-10-05 16:22:06
0
tesso5891
tesso :
shemelis ? melkam hono new, yeketelewu,?????¿????
2026-10-05 19:44:37
0
kibru6184
kibru :
👍👍👍👍👍🥰🥰🥰🥰✅✅✅✅
2026-10-05 13:50:28
2
To see more videos from user @firduaklilu, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About