@respect12192123: . ዘመነ ጽጌ [ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6] "ልጄን ከግብፅ ጠራሁት" 《ት.ሆሴዕ 11፥1》 ከመምህር ዮሐንስ ለማ እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሕግና ስርአት መሰረት ከመስከረም 26 ቀን እስከ ሕዳር 6 ቀን ያለው 40 ቀን የእመቤታችንን እና የልጇን ስደት በማሰብ ወርኃ ጽጌን 《ዘመነ ጽጌን》ታከብራለች፡፡ ይህ 40ው ቀን የእመቤታችንና የጌታችን ስደት የሚታሰብበት ዘመን ነው፡፡ ወቅቱ የአበባና የፍሬ ወቅት በመሆኑ እመቤታችን በአበባ ጌታችን በፍሬ እየተመሰሉ ጌታችን በአምልኮት እመቤታችን በፈጣሪ እናትነቷ በተለየ ምስጋና ይመሰገናሉ ፡፡ በስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሳው ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ አምሥቱን ጸዋትወ ዜማ ሲደርስ በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሳው አባ ጊዮርጊስ ደግሞ ሰዓታትን ደርሷል፡፡ በዚሁ ዘመን ከአባ ጊዮርጊስ ጋር ጥልቅ መንፈሳዊ ፍቅር የነበረው አባ ጽጌ ድንግል ማኅሌተ ጽጌ የተባለውን ድርሰት ደርሷል፡፡ ማኅሌተ ጽጌ ግጥማዊ አካሄድ ያለው ድንቅ ኢትዮጵያዊ ድርሰት ሲሆን ይህ ድርሰት በማንኛውም ጊዜ የሚጸለይ ቢሆንም በተለየ ሁኔታ ወቅት ተለይቶለት በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ላይ የሚውለው ግን በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና በልጇ የስደት ዘመን ማለትም ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ቀን ድረስ ባለው ዘመን ውስጥ ነው፡፡ በዚህ ወቅት በየሳምንቱ እሑድ ሌሊቱን በሙሉ የእመቤታችንን ከልጇ ጋር ወደ ምድረ ግብፅ መሰደድና መንከራተት እየታሰበ በሊቃውንቱ የሚደርስ የምሥጋና ጸሎትም ነው ፡፡ ይህ ድርሰት በግጥም መልክ የተደረሰ ሲሆን በአብዛኛው አምስት ስንኞች ሲኖሩት ብዛቱም 158 ያክል ነው፡፡ እመቤታችን ጣዕሟንና ፍቅሯን እንዲሁም ምስጋናዋን ሲናፍቁ የነበሩትን ቅዱስ ኤፍሬምንና አባ ሕርያቆስን ውዳሴዋንና ቅዳሴዋን እንደገለጸችላቸው ሁሉ ለፍቅሯ ሲሳሳ ለነበረው ለአባ ጽጌ ድንግል ደግሞ ይህንን የማኅሌተ ጽጌን ድርሰት እንዲደርስ ምስጢርን ገልጻለታልች ። በቅድስት ሐገር ሐገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ የመስከረምና የጥቅምት ወራት የአበባ ወራት ወርኅ ጽጌ (ዘመነ ጽጌ) ናቸው፡፡ ይህም ወቅት ተራሮች በአበባ የሚያጌጡበትና ለዓይን ማራኪ የሚሆኑበት ጊዜ ነው፡፡ በዚህም ዘመን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ‘’ ስለ ልብስ ስለምን ትጨነቃላችሁ ? የሜዳ አበቦች እንዴት እንዲያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ፡፡ አይደክሙም፣ አይፈትሉም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፣ ሰሎሞንስ እንኳ በክብሩ ሁሉ ከእነዚህ እንደ አንዱ አልለበሰም፡፡ እግዚአብሔር፣ ዛሬ ያለውን ነገም ወደ እቶን የሚጣለውን የሜዳን ሣር እንዲህ የሚያለብሰው ከሆነ፣ እናንተ እምነት የጐደላችሁ፣ እናንተንማ ይልቁን እንዴት፡፡ እንግዲህ ምን እንበላለን፣ ምንስ እንጠጣለን፣ ምንስ እንለብሳለን ብላችሁ አትጨነቁ ‘’ 《ማቴ 5÷28-33》
prevent
Region: AE
Monday 05 October 2026 13:34:35 GMT
Music
Download
Comments
There are no more comments for this video.
To see more videos from user @respect12192123, please go to the Tikwm
homepage.