@getasew.bantie0: እርሳቸው (ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ) "እኔን ሸኙኝ፤ ይህን ዓመት አላልፈውም" ብለው በይፋ ተማጸኑ። (ዕድሜዎትን አሁንም ለእኛ ሲል መድኃኔዓለም ያርዝምልን የኛ እንቁ አባት) እንደ ሽኝታቸው ይታይ ዘንድ ገድለ ሕይወታቸው የተከተበበት የሕይወት ታሪካቸውን የሚተርክ መጽሐፍ ተጽፎ መርኃግብር ተዘጋጀ። ከ42 በላይ ሀገር ውስጥ ከሚገኙ ሊቀነ ጳጳሳት 2ቱ ብቻ ተገኙ። (አይገርምም ወገን) ለዓለማዊ ጋብቻ ሽማግሌ ሆኖ የሚሄዱት የእኛው ጳጳሳት፣ ሆቴል ለመመረቅ በሰልፍ የሚጓዙት ብፁዓን አባቶች የአንድ ብፁዕ አረጋዊ አባት የሽኝት ቃልን ንቀት በሚመስል መልኩ ባልሰማ ሆነው ቀሩ። (ታዲያ ይሄ የእውነት ግን አያናድድም?😠) እርግጥ ነው ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ብዙዎች በሚወተፉበት የዘር ጥሻ ውስጥ አይቀረቀሩም። ከእግዚአብሔር በቀር ቄሳርን የሚሾሙበት ትከሻም አልፈጠረባቸውም። የልጆቻቸውን መከራ እያሰቡ ዕለት ዕለት ያነባሉ እንጅ ለልጆቻቸው እንባ ምክንያት ሆነው አያውቁም። በጠብ፣ በሙግት፣ በክርክር ውስጥ መኖርያ ስፍራ አይፈልጉም። ጸሎት እና እንባ ብቻ ነው ህይወታቸው። ስለዚህ ብዙዎች ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን አይመስሉም። ስለዚህ ለሽኝታቸው ደንታ የሚሰማው፣ ለጥሪያቸው የሚታዘዝ ጆሮ ላይኖራቸው ይችላል። ግን ቢያንስ እኝን የእንባ አባት የሆኑ አረጋዊን በክብር መሸኘት ማንን ገደለ? (((ብቻ የቅዱሳን አምላክ ለተገፉትና ለደከሙት መደገፊያ የሆነው ልዑል እግዚአብሔር እድሜዎን ያርዝምልን! እልፈትዎን ለሚመኙና ውደቀትዎን ለሚመኙ ሁሉ የሚያፍሩበትን እድሜ እርሱ ይስጥልን። ‘በቃ አረፉ’ ተብሎ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ በሚኮንበት ጊዜ ሁሉ፣ እርሱ የእድሜዎን ዘመን በፀጋው አድሶ ያስቅጥልልን። ቤተክርስቲያንን በሃይማኖት አፅንተው፣ እኛንም ልጆችዎን እንደ አባት በፍቅር እየገሰፁና እየቆነጠጡ በመንፈሳዊ ህይወት እንዲያሳድጉን የእግዚአብሔር ሰላም ከእርስዎ ጋር ይሁን!🙏))) #አሼ_ነኝ✌ #ቤቱን_like_share_follow_copylink_repost_ማድረጋችሁን_አትርሱ🙏 #ብፁዕ_አቡነ_ቀውስጦስ

Getasew Bantie
Getasew Bantie
Open In TikTok:
Region: ET
Monday 05 October 2026 17:00:13 GMT
3853
401
11
13

Music

Download

Comments

my21122313
Birhanu Desalegn :
እግዚአብሔር ብርታቱን ሰጥቶ ያቆይልን
2026-10-06 07:10:31
1
haymet.abrham
L/M/Abrham :
አባታችን እድሜዎትን ያርዝምልን
2026-10-06 01:38:27
1
adenrkushalene
nets :
የህዝቂያስ አምላክ የእድሜ ባለቤት ለእኛ ለኃጢያተኞች ስል እድሜዎን ያርዝምልን አባቴ
2026-10-05 23:27:45
1
user2856542157824
ሜትር :
እደሜወትን የኖሩበትን እዱሚ ሁለት እጥፍ የአርዝምልን
2026-10-06 02:38:39
1
user2279044574979
user2279044574979 :
እዉነትነዉ ወድሜ ይሰማል ጤናከድሜይስጣቸዉ 🥰🥰🥰🥰🥰🥰
2026-10-05 20:10:18
1
.168895
sif ze kidanemihiret🌹 :
ብፁዕ አባታችን ሺ ሊቃነ ጳጳሳትን ይተካሉ ሸኚን አይሹም ለመጡትም እግዚአብሔር ይጠብቅልን በረከታቸው ይድረሰን[Pray][Pray]
2026-10-06 10:51:45
1
abeneze062
ዲ/ን አሀዱ ዘደብረ መንክራት :
አሜን የፀጋ ባለቤት እርሱ ረጅም እድሜ ከጤና ጋር ያድልልን
2026-10-06 03:10:16
1
gery3485
Olver 🫶🫶🫶 :
🙏🙏🙏🙏
2026-10-06 01:26:28
0
la_mi_t_21_
@l_a_m_i 12 T :
🥰🥰🥰
2026-10-06 00:46:52
0
user6888840618205
user6888840618205 :
🙏🙏🙏
2026-10-05 18:56:06
0
user7476804826319
መታገስ ዋጋ አለው :
🙏🙏🙏
2026-10-08 18:51:48
0
To see more videos from user @getasew.bantie0, please go to the Tikwm homepage.

Other Videos


About