@getahunnigussu: *እንኳን ለውርሃ ጽጌ ሱባኤ በሰላም አደረሳችሁ!* ✝️ *ዘንዶው አሳደዳት* ✝️ *እነሆ በየዓመቱ ከመስከረም 26 እስከ ህዳር 6 ቀን ድረስ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የእመቤታችንን ስደት በሚገባ ትዘክራለች። የተጉ እና ሥላሴ ያበረቷቸው ምዕመናንም ወቅቱን በጾም፣ በጸሎት፣ በማኅሌት በማሳለፍ የማያልቅ በረከት ከእመብርሃን ይቀበላሉ። ዘንዶው እመቤታችንን እንዴት እንዳሳደዳት በእንባ እያሰቡ የእርሷን እና በእቅፏ የተሰደደውን የልጇን የጌታችን የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የስደት መከራ እያሰቡ በረከት ይቀበላሉ።** መልካም ንባብ! ✝️ ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች።.... የዮሐንስ ራእይ 12 : 1 ✝️ ዘንዶውም ወደ ምድር እንደ ተጣለ ባየ ጊዜ ወንድ ልጅ የወለደችውን ሴት አሳደዳት። የዮሐንስ ራእይ 12 : 13 ✝️ ከእባቡም ፊት ርቃ አንድ ዘመን፥ ዘመናትም፥ የዘመንም እኵሌታ ወደ ምትመገብበት ወደ ስፍራዋ ወደ በረሀ እንድትበር ለሴቲቱ ሁለት የታላቁ ንሥር ክንፎች ተሰጣት። የዮሐንስ ራእይ 12 : 14 ✝️ እባቡም ሴቲቱ በወንዝ እንድትወሰድ ሊያደርግ ወንዝ የሚያህልን ውኃ ከአፉ በስተኋላዋ አፈሰሰ። የዮሐንስ ራእይ 12 : 15 ✝️ ምድሪቱም ሴቲቱን ረዳቻት፥ ምድሪቱም አፍዋን ከፍታ ዘንዶው ከአፉ ያፈሰሰውን ወንዝ ዋጠችው። የዮሐንስ ራእይ 12 : 16 ✝️ ዘንዶውም በሴቲቱ ላይ ተቈጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ የዮሐንስ ራእይ 12 : 17 በባሕርም አሸዋ ላይ ቆመ። የዮሐንስ ራእይ 12 : 18 ✝️ እነሆ ከዛሬ መስከረም 26 እስከ ህዳር 6 ቀን ድረስ. ወቅቱ ወርኃ ጽጌ የእመብርሃንን የ3 ዓመት ከ6 ወር (አንድ ዘመን ዘመናትም የዘመንም እኵሌታ)ስደት የምናስብበት ታላቅ ወቅት ነው* :: ✝️ ወርኃ ጽጌ ወቅቱ ዘንዶው የ144 000 ህጻናትን ደም እንደ ወንዝ ውሃ በስደት ላይ ከነበረችው እናታችን በስተኋላ ያፈሰሰበት ድርጊት የሚታሰብበት የሀዘን ወቅት ነው። ✝️ ዘንዶው እርስዋን ስደተኛዋን እመቤታችንን ባያገኛት በእርስዋ ስደት ተቆጥቶ የቤተክርስቲያን ልጆችን ሊዋጋ የወሰነበት አስገራሚ ወቅት ነው ወርኃ ጽጌ! ✝️ ወቅቱ ዘንዶው የባህር አሸዋ በተባለ በመናፍቃን ልብ ላይ ተተክሎ እመቤታችንን ያለ እረፍት እንደሚያሳድድ ቤተክርስቲያንንም እንደሚዋጋ የምናስብበት ወርኃ ጽጌ ነው። እመብርሃንን የሚያሳደው ዘንዶ ዛሬም ድረስ በመናፍቃን እና ከሃድያን ልብ አድሮ እርሷን በአካል ባያገኛት ስዕሏን እና ስሟን ጭምር እንዴት እንደሚያሳድድ እያየን የምናዝንበት በብርቱ የምንጸልይበት ወቅት ነው ወርኃ ጽጌ። ✝️ በእውነቱ እመቤታችን ድንግል ማርያምን ከሚያሳድድ የዘንዶ መንፈስ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ሁላችንን ይጠብቀን:: ✝ እኛስ ከእግዚአብሔር የተላከው ብርሃናዊ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል እንዳስተማረን ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ እያልን ያለዕረፍት እመብርሃንን እያመሰግንናት፣ የሚያሳድዳትንም ዘንዶ በመስቀሉ እየቀጠቀጥን፣ ስደት መከራዋንም እያሰብን፣ በምልጃዋ እየተጠበቅን ወርኃ ጽጌን በሚገባ በፊቷ እየቆምን እንድንጠቀም እግዚአብሔር አምላካችን ይፍቀድልን። ✝ የእመብርሃን ረድኤት በረከቷ በሁላችን ላይ ይደር። የአቡነ ሀብተማርያም ጻድቅ በረከት፣ ከእመብርሃን ጋር አብረው የተሰደዱ የቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ እና የቅድስት ሰሎሜ በረከት በሁላችን ላይ ይደር። አምላካችን ቅዱስ አማኑኤል በጀርባዋ አዝላው፣ በክንዶቿም አቅፋው ስለተደደደችው እናቱ ብሎ ይማረን። አሜን ✝️ብሩህ ቀን ✝️ #ኢትዮጵያ_ለዘለዓለም_ትኑር🇪🇹🇪🇹🇪🇹ኩራቴ😘 #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ_ፀንታ_ለዘለዓለም_ትኑር✝️❤ #ጽጌጾም #protestantmezmur #backtoit
@gech2127
Region: ET
Tuesday 06 October 2026 04:23:16 GMT
Music
Download
Comments
Queen :
አሜን ቃለህይወት ያሰማልን
2026-10-06 09:02:25
1
me :
🥰🥰🥰
2026-10-06 06:20:25
0
tame :
🥰🥰🥰🥰
2026-10-06 06:29:50
1
Mule Amebachew :
😂😂😂
2026-10-06 10:42:15
0
To see more videos from user @getahunnigussu, please go to the Tikwm
homepage.