@semna_work: 🌹🌹🌹ዝምተዋ ገፋኝ❤❤❤ ዝምታዋ ገፋኝ አራቀኝ ከጎኗ፣ ፍቅሯን ለመናገር ቢዘጋ ልሳኗ፣ ፡ ባንኳኳው ደጃፏን ሚከፍትልኝ ባጣ፣ ከጎረቤት ዞርኩኝ ሚሰማኝ ከመጣ፣ ፡ ቃላትን ቀምሬ አስውቤ አሽቀርቅሬ፣ ዝምታ መልስ ሆነ ፍቅሬን በማብሰሬ፣ የውስጤን መከፋት በውስጤ ቋጥሬ፣ ለመሄድ ተነሳው ወደ መራኝ እግሬ፣ ፡ ወድሻለው ስላት መውደዷን ባትነግረኝ፣ ከሌላ እንድከጅል ዝምታዋ ገፋኝ፣ ፡ ነግሪያት ነበረ..... ልክ እንደፏፏቴ ድምፄን ብዙ አድርጌ፣ በበራቸው ደጃፍ አንገቴን አስግጌ፣ አባቷም ዘልፈውኝ ብለውኝ ባለጌ፣ አሳዲጊም የለህ መረን የልጅ ዋልጌ፣ ፡ እያሉኝ ሰምታለች እኔም ሰምቻለው፣ ፍቅሬን ተናገርኩኝ ግን ከቁብ ሳላየው፣ ፡ እሷ ግን አድምጣኝ አንዳችም አላለች፣ የኔን ማፍቀር ሰምታ ማፍቀሯን ደበቀች፣ አስር ጊዜ ሰምታ እንዳልሰማ ሆነች፣ ፣ ዝምታዋ ቢያል ደጋግሞ አስፈራኝ፣ አታፈቅረኝ ብዬ ልርቃት ወሰንኩኝ፣ ፡ በርሃ አቋርጬ ከደጋው ስገባ፣ ወዴት ነህ አለችኝ ስለኔ አስባ፣ ፡ የብርዱ ወር አልፎ ስሟሟቅ ስድላላ፣ ትከተለኝ ጀመር በሄድኩበት ሁላ፣ ፡ እወድህ ነበረ በድንገት ብትለኝ፣ የመፍራቷን ሚስጢር ደርሳ ብታዋየኝ፣ ያን ፍቅሬን አስቤ እንባ ተናነቀኝ፣ ግን ምንላርግ ርቄያለው ዳግም ላትመልሰኝ፣ ልቧ እየፈለገ ዝምታዋ ገፋኝ፡፡ Eyu negn follw#eritreantiktok🇪🇷🇪🇷habesha #CityTasteTest #ethiopiantiktok
እንባና ፊደል
Region: ET
Tuesday 06 October 2026 17:01:17 GMT
Music
Download
Comments
Solomon M :
ሀቅ ነዉ ብሮ
2026-10-07 13:52:30
0
Mubarek Yimer :
benath ye zefenun name ngreng
2026-10-07 16:16:04
0
user6341417614635 ተስፈኛዉ ነኚ :
አይዞህ
2026-10-07 09:15:46
0
❤አርሴ❤ ፍቅር❤ :
2026-10-07 09:23:49
0
ሀቢቦ የሱፍ 🖤🖤💔💔😭 :
2026-10-07 06:17:30
0
Jems :
2026-10-06 22:16:20
0
CR 7 :
🥰🥰🥰🥰
2026-10-07 11:22:19
0
selomin birhanu :
🥰🥰🥰
2026-10-07 15:29:20
0
Habtamu Aleligne :
🥰🥰🥰
2026-10-06 18:25:53
0
✧𝒯𝒽ℯ 𝒩ℴ𝓇𝓉𝒽🌍ሰሜናዊው🦅✧ :
😍😍😍
2026-10-07 19:16:39
0
To see more videos from user @semna_work, please go to the Tikwm
homepage.