@firduaklilu: የአዲስ አበባ ወሬ ከቴሌ ኔትወርክ ይፈጥናል። ሰሞኑን በየማኪያቶ ቤቱ እና በየቢሮው ኮሪደር ላይ እንደ 5ጂ ኔትወርክ ፈጥኖ የሚሰራጨው ሹክሹክታ የኢትዮ ቴሌኮሟን ዋና ሥራ አስፈፃሚ የወይዘሮ ፍሬሕይወት ታምሩን ቀጣይ ዕጣ ፈንታ የተመለከተ ነው። ነገሩ እንዲህ ነው... "ካቢኔ ሊሽከረከር ነው፤ በዚህ ሽክርክሪት ውስጥ ደግሞ ወይዘሮ ፍሬሕይወት አሁን ካሉበት ማማ ላይ ተነስተው ወደ ሚኒስትርነት ዙፋን ሊወነጨፉ ይችላሉ" የሚል ነው። አያችሁ አይደል... በእኛ ሀገር ትልቁ አደጋ ሥራ ሰርቶ ማሳየት ነው። ተቋምህን በስኬት ከቀየርክ "እንግዲያውስ ይሄኛው መስሪያ ቤትም ስለተበላሸ እባክህን እሱንም ጠግንልን" ተብለህ በሹመት ትቀጣለህ። ፍሬሕይወት ቴሌን ከእንቅልፉ አነቃችው። ድሮ ካርድ ስንሞጭር ጥፍራችን ያልቅ የነበረውን ህዝብ በ"ቴሌ ብር" አዘመነችው (አሁን አሁንማ ለማኝም "ቴሌ ብር ካለህ አጋራኝ" እስከማለት ደርሷል)። 5ጂን አመጣች፤ አሁን ደግሞ የቴሌን 10 በመቶ አክሲዮን ለህዝብ ቸበቸበች። ታዲያ ይህን ሁሉ ተዓምር ያየው የሹመት ሟርተኛ አፉን ከፍቶ፤ "ይቺ ሴት እዚህ ቦታ ላይ አንሳባታለች! ይህን በቴሌ ያሳየችውን የፈጣን አፈጻጸም ጥበብ፣ ለምን እንደ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ፣ ወይንም የገንዘብ ሚኒስቴር ሄዳ አትደግመውም?... ኸረ እንደውም ኢትዮ ኢንቨስትመንት ግሩፕን በሚኒስትር ማእረግ ትምራ" እያለ ማውጠንጠን ጀምሯል። ለነገሩ አንዳንዱ የኛ ሰው አንዴ ጀግና ካገኘ፣ "እባካችሁ እሳቸውን የመብራት ኃይልም፣ የውሃና ፍሳሽም፣ የትራፊክ ፖሊስም አድርጉልን!" ማለቱ አይቀርም። በሌላ በኩል ደግሞ "ተው እንጂ! እየሮጠ ያለን ፈረስ መሃል መንገድ ላይ ኮርቻ አንቀይርም" የሚሉ የውስጥ አዋቂዎች አሉ። ምክንያታቸው ደግሞ አሳማኝ ነው። ቴሌ አሁን ገና አክሲዮን ሸጦ ወደ ካፒታል ገበያ አዲስ ሙሽራ ሆኖ እየገባ ነው። ከሳፋሪኮም ጋር ያለው የገበያ ትንቅንቅ ደግሞ እንደ አውራ ዶሮ ፍልሚያ የጋለበት ሰዓት ነው። በዚህ መሃል ፍሬሕይወትን ነቅሎ ወደ ሌላ ሚኒስቴር መውሰድ፣ እየበረረ ካለ አውሮፕላን ላይ ሞተር ነቅሎ ለታክሲ እንደመግጠም ይቆጠራል። "እሳቸው ቢነሱ ይሄን የቴሌን ግዙፍ ጫማ ማን ይጫማዋል?" የሚለው ጥያቄ የመንግስትም፣ የህዝቡም ትልቁ ስጋት ሆኗል። ያም ሆነ ይህ የሴትዮዋ ስኬት የፈጠረው ጣጣ ነው። እንደ በፊቱ ኔትወርክ "አልሰራም፣ አይሰማም፣ ከሽፋን ውጪ ነው" ብላ ቢሆን ኖሮ ማን ጠይቋት! እሳቸው ወደ ሚኒስትርነት ቢያድጉም፣ የጀመሩትን ለማጠናቀቅ ባሉበት ቢቀጥሉም፣ በአዲስ አበባ የሹክሹክታ ገበያ ላይ ግን የተቋም ስኬት መለኪያ መሆናቸውን አስመስክረዋል። የዘንድሮው የፖለቲካችን ትልቁ የእንቆቅልሽ ጥያቄም፣ 'ወይዘሮ ፍሬሕይወት የቴሌን ኔትወርክ አቃንተው ወደ ሚኒስትርነት ኮሪደር ይሻገራሉ ወይስ አይሻገሩም?' የሚለው አይደለም። ዋናው ስጋት እሳቸው ድንገት ወደ ሌላ ኃላፊነት ቢዛወሩ፣ አዲሱ ተተኪ የቴሌን አሰራር ወደ ድሮው የ'ሚስኮል' እና 'ከሽፋን ውጪ ነዎት' ዘመን እንዳይመልሰው ነው። ሲጀመር የኛ ሀገር የሹመት ነገር ልክ እንደ ሞባይል ዳታችን ነው፤ ሳይታሰብ ይመጣል፣ ሳይታሰብ ደግሞ ድርግም ይላል። ብቻ ወይዘሮ ፍሬሕይወት ወደ ሌላ ከፍ ያለ ሀገራዊ ኃላፊነት 'አፕግሬድ' ቢደረጉም፣ የቴሌ ነገር ከእሳቸው መውጣት በኋላ ወደ ኋላ 'ዳውንግሬድ' ሆኖ... ኔትወርክ ፍለጋ እንደ ድሮው ዛፍ ላይ ወደ መውጣት አዙሪት እንዳንመለስ የሁላችንም የጋራ ጸሎት ነው!
ፍርዳወቅ የሕግ አገ/ት Firdawek legal
Region: ET
Tuesday 06 October 2026 17:05:23 GMT
Music
Download
Comments
Hau1294 :
esuwa kemetach bewala adellem ede tele yetebelashew netork belelebet hager zerefechen,besew account poseta yehonal enji slesuwa tiru yemiyaweraw zare yhen ayew,demo tele yezemenew bezemenu hedet new enji besuwa aydellem manm bihon besuwa bota bihon gedeta yemiyadergew new esketenesa chekuyealw gen behedechibetm tefat new enji yasaznal esum
2026-10-07 11:48:03
0
Tamuu :
min serta new silezerefech new
2026-10-07 05:39:24
0
Abele Mulugeta :
Awaw.ewnat.naw.esowvecha.nat..latile
2026-10-06 19:08:18
0
Guti :
ሲጀመር ኢትዮ ቴሌኮም ራሱን የቻለ የመንግስት ድርጅት ነዉ/ ባቅ ባጃት: ብቁ የሰዉ ኃይል አለው/ :: ሌሎች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ግን ባቅ ባጃትም ሆነ ንቀት ያለው የሰው ኃይል የላቸውም:: ስላዚህ ልዩነት አለው:: ቢሆንም ግን ሴትየዋ ጎበዝ ናት::
2026-10-07 07:29:12
1
Nati@ :
ህዝቡን በመዝረፍ ነዉ ቴሌን ያነቃችዉ የኔትወርክ ችግር ያለበት ድርጅት ቢሆን እሱ ነዉ ሳፉሪ በይመጣ የኢትዮጵያ ህዝብ ምንም መጠቀም አይችልም ነበር
2026-10-07 04:22:58
3
Ethiogate :
የትም ቢመደቡ የኢትዮጵያን ጉዳይ አይደለም። በዝባዥ ኮርፓሬሽን።[Embarrassed]
2026-10-07 07:47:11
1
Abebe Tadesse :
በጣም ጥሩ ነው የተሰራው ስራ ሳላመሰግን አላልፍም ዝርዝሩን ላለመድገም ብየ ነው ነገር ግን ሁሌ የምያናድደኝ ነገር የድምጽ ጥር ስንሞላ የለልት ቦነስ ስጦታ ተብለው ተጨማር የድምጽ ጥር ፉገራ ነው የሚመስለኝ ለምን ባል ማነው ለልት ደውሎ ቦነሱን የምጠቀምበት ምናልባት የለልት ጥበቃ የሆነ ሰው እርስበርሱ ካልተደዋወለ በስተቀር ይች ፉገራ ነች ብዙ ሰው እንደማይጠቀም ስለምያውቁ ነው ከቦነሱ ይልቅ በዋናው ላይ ብጨምሩልን ጥሩ ነበረ ባይጨመር እንኳ የፉገራ ቦነሱ ብቀር የነ ሃሳብ ነው
2026-10-07 03:36:27
2
Rich man :
ከእሷ የተሻለ ሰው በፍፁም አይገኝም።
2026-10-07 07:05:08
1
Amazing best ኢትዮጵያ :
የጥበቃ ሠራተኞች ባህርዳር ዲስትሪክት መብት ጉዳይ ቢታይንል 👍👍👍👍👍በዘራፊ እዬተጎዳን ነው
2026-10-07 05:18:21
1
yirga ayalew :
ምንም ኔትወርክ የሌለባቸው አካባቢዎች አሉ አይደል ስራው ገና አባይን በጭልፍ ነው
2026-10-07 03:33:52
1
user3730817610804 :
ተባለ እንዴ መሆኑ ነው።
2026-10-06 21:53:42
1
Shamil Abas :
enkon fire hiwat lamin anta minstar atonm lamin taklay minstar atonm ya ethiopa hizb mifalgaw badrjaw lik manor ena lamimolw card basrat matkam naw telbr bimatm lahizbu aydlm eko 1 birr lamlkm baw hulum yawkal eko Im sory
2026-10-06 19:19:34
0
beruk :
ስራም ሰሩ እኛንም ዘረፉ
2026-10-07 13:12:27
0
Alko Meloye :
ማለቅለቅም ልክ አለው
2026-10-07 13:06:55
0
DUNAMIS :
ብራችንን እያጠበች እድገት ትላለህ እንዴ
2026-10-07 10:09:11
0
ብርሌው ያባቱ ናፋቂ :
ሳንጠቀመው የሚአልቀው ብር እሳ
2026-10-06 19:10:58
0
M78 :
ወ/ሮ😳😂
2026-10-07 13:23:41
0
Abba Cabsa :
አበት ውሽት፣ ሁሉም ነገር በስም አለ፣ በተግበር ግን ዜሮ ነው፣ ለምሳሌ፡- ያልከው 5G በስም እንጂ በተግባሩ 0+ ነው፣ ሌላው ዳታ ገዝተን ምንም ሳንጠቀምበት ያልቃል፣ ታዲያ ይሄ ሌብነት ወይስ ስራ ነው የሚባለ ????
2026-10-07 14:19:28
0
Em :
እሷ ከገባች ኔት ወርክ ጠፋ እንደ መብራት ኃይል ለሰዓታት እየጠፋ ነው ሚመጣ
2026-10-06 17:17:55
10
nebasolos :
መብራት ሃይል ብትመጣ
2026-10-07 06:26:58
0
Balageru :
ምን ብታደርግልህ ነው እንዲህ 🥰🥰🥰 አልክ እኮ
2026-10-07 07:42:37
0
የማነሽ ይሉኛል🇪🇹🇪🇹❤❤ :
ባደረገው😭😭
2026-10-07 13:49:52
0
Akimi :
አጨብጫቢ ቴሌ በወረዳ ከቸሞችኳ የተሻለ አይደለም
2026-10-06 19:00:59
2
ሰይፉ ሺፎን :
ቴሌ ሼር የሸጡላቸው ግለሰቦች ምንም ሳያዩ 2አመት አለፈው ሻሻ እዚም አለ😂😂😂
2026-10-07 06:43:27
0
Mohammed Ali :
ሚንስትርነት ያንሳታል እንጂ አይበዛባትም ቴሌን መምራት ማለት ሀገር ከመምራት አይተናነስም
2026-10-07 09:14:30
0
To see more videos from user @firduaklilu, please go to the Tikwm
homepage.